ዶክተር ሙሉ ነጋ ወደቀደመው ሚኒስትር ዴኤታነታቸው ተመልሰዋል
ዶክተር ሙሉ ነጋ
ትናንት ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚነታቸው ተነስተዋል
ኢዛ (ሐሙስ ሚያዝያ ፳፰ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. May 6, 2021)፦ ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚነታቸው የተነሱት ዶክተር ሙሉ ነጋ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ከመሾማቸው ከኅዳር 4 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በፊት ወደነበሩበት የኃላፊነት ቦታ ላይ በድጋሚ ተሹመዋል።
ዛሬ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የወጣው መረጃ ዶ/ር ሙሉ ነጋ የሣይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ በመኾን መሾማቸውን አስታውቋል።
ዶ/ር ሙሉ ከሚያዝያ 28 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በሚኒስትር ዴኤታነት ወደሚሠሩበት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ሲመለሱ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚነታቸውን ደግሞ ለዶ/ር አብርሃም በላይ ያስረክባሉ። (ኢዛ)



