ኢትየጵያዊያን ከ60 ዓመታት በኋላ በሮም ድጋሚ ድል ተቀዳጁ

Athlet Siraj Gena አትሌተት ሲራጅ ገናሲራጅ ገና በባዶ እግሩ በመሮጥ የአበበ ቢቂላን ስም በድጋሚ አስጠራ

Ethiopia Zare (ሰኞ መጋቢት 13 ቀን 2002 ዓ.ም. March 22, 2010)፦ በዓለም ታሪክ ኢትዮጵያን በመወከል በአትሌቲክስ ታሪክ በባዶ እግሩ በመሮጥና በማሸነፍ ተወዳዳሪ ያልተገኘለትን አትሌት አበበ ቢቂላን በመተካት ከአምሳ ዓመታት በኋላ አትሌት ሲራጅ ገና 500 ሜትር ሲቀረው በባዶ እግሩ በመሮጥ አሸነፈ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከስምንቱ ቦምባርዲየር ኪው 400 አውሮፕላኖች አንዱ አዲስ አበባ ገባ

Ethiopian Airlines Bombardier Q400 / የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦምባርዲየር ኪው 400 አውሮፕላንEthiopia Zare (እሁድ መጋቢት 12 ቀን 2002 ዓ.ም. March 21, 2010)፦ በ192 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመግዛት ካዘዛቸው ስምንት ቦምባርዲየር ኪው 400 አውሮፕላኖች ውስጥ የመጀመሪያው አንድ አውሮፕላን ዛሬ መጋቢት 12 ቀን 2002 ዓ.ም. አዲስ አበባ ገባ። አውሮፕላኑ ዘመናዊ፣ ባለሁለት ሞተርና 78 መቀመጫዎች ያሉት ሲሆን፣ ስምንቱም አውሮፕላኖች ለሀገር ውስጥ በረራ የሚውሉ ናቸው።  ሙሉውን አስነብበኝ ...

መድረክ የልዑካን ቡድኑን ወደ ውጭ ሀገር ሊልክ ነው

ዶ/ር መራራ ጉዲና አሜሪካን ሀገር ገብተዋል

Ethiopia Zare (ዓርብ መጋቢት 10 ቀን 2002 ዓ.ም. March 19, 2010)፦ መድረክ በሚሳተፍበት የመጭው 2002 ዓ.ም. ምርጫ የገንዘብ ማሰባሰብና ከደጋፊዎቹ ጋር ለመወያየት አንድ የልዑካን ቡድን ሊልክ በዝግጅት ላይ መሆኑን የድርጅቱ አመራር አባል ዶ/ር መራራ ጉዲና በተለይ ለኢትዮጵያ ዛሬ ገለጹ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

መኢአድ በአራተኛው ዙር የፓርቲዎች ክርክር ለመጀመሪያ ጊዜ ተሳተፈ

Ethiopia Zare (ዓርብ መጋቢት 10 ቀን 2002 ዓ.ም. March 19, 2010)፦ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሲካሄድበት የቆየው የፓርቲዎች ክርክር አራተኛው ክፍል ዛሬ ዓርብ መጋቢት 10 የተጀመረ ሲሆን፤ በቀደሙት ሦስት የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በክርክሩ ያልተሳተፈው የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ለመጀመሪያ ጊዜ ተሳታፊ ሆኗል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሃሳብን በነፃ የመግለጽ ሽልማት ሥነሥርዓት ተካሄደ

(ከግራ ወደ ቀኝ) አና ኦተርሆልም እና ወ/ሮ ሶፊያ ብርሃነ Ethiopia Zare (ረቡዕ መጋቢት 8 ቀን 2002 ዓ.ም. March 17, 2010)፦ ባለፈው እሁድ መጋቢት 5 ቀን 2002 ዓ.ም. (ማርች 14 ቀን 2010 እ.ኤ.አ.) በኖርዌይ ኦስሎ ከተማ በተካሄደው የኖርዌይ ደራሲያን ማኅበር ዓመታዊ ጉባዔ ላይ የእ.ኤ.አ. 2009 ሃሳብን በነፃ የመግለጽ ሽልማት ሥነሥርዓት ተካሄደ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

አርቲስት ሌ/ኮሎኔል ሣህሌ ደጋጎ በ79 ዓመቱ አረፈ፣ ሥርዓተ ቀብሩ ተፈፀመ

Artist Sahele Degago's Funeral, 15th March 2010“ሞተዋል” የተባሉት አትሌት ዋሚ ቢራቱ በሌ/ኮሎኔሉ ለቅሶ ላይ ተገኝተዋል

አርቲስት ሌ/ኮሎኔል ሳህሌ ደጋጎ, Sahle DegagoEthiopia Zare (ሰኞ መጋቢት 6 ቀን 2002 ዓ.ም. March 15, 2010)፦ አንጋፋው የሙዚቃ መሣሪያ ተጫዋች፣ ገጣሚ፣ የዜማ ደራሲ እና የሙዚቃ አቀናባሪ ሌተናል ኮሎኔል ሣfህሌ ደጋጎ የቀብር ሥነሥርዓት ዛሬ መጋቢት 6 ቀን 2002 ዓ.ም. ከቀኑ በዘጠኝ ሰዓት በአዲስ አበባ ከተማ ፈረንሣይ ለጋሲዮን በሚገኘው በገነተ-ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ዛሬ ተፈፀመ። ሌ/ኮሎኔል ሣህሌ በ79 ዓመቱ በትናንትናው ዕለት ነበር ያረፈው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢንጂንየር ግዛቸውና አቶ ስዬ ወደ መቀሌ ያመራሉ

‘ዘመቻው ተጧጡፎ ቢቀጥልም መድረኩም ሆነ ዓረና ከምርጫው አይወጡም’ አቶ ገብሩ አስራት

Ethiopia Zare (ረቡዕ መጋቢት 1 ቀን 2002 ዓ.ም. March 10, 2010)፦ ኢንጂንየር ግዛቸው እና አቶ ስየ አብርሃ ወደ መቀሌ የሚያመሩት እሁድ መጋቢት 5 ቀን 2002 ዓ.ም. መድረክ በትግራይ በሚያደርገው የምርጫ ቅስቀሳ ላይ ተሳትፎ ለማድረግና በትግራይ ክልል የድርጅታቸውን የምርጫ ሂደት ለመከታተል መሆኑን በአዲስ አበባ የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች ጠቆሙ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

አቶ ስየ አብርሃ ለቢቢሲው ዘገባ ምላሽ ሰጡ - ‘ዝም ብዬ አልቀመጥም’ ሲሉ ተደምጠዋል

“ባይጫኑን! ባይገፉን! ጥሩ ነው፤ ከተጫኑን ግን ሁሉን ነገር ይፋ እናወጣዋለን!” አቶ ስየ አብርሃ

Ethiopia Zare (ረቡዕ መጋቢት 1 ቀን 2002 ዓ.ም. March 10, 2010)፦ አቶ ስየ አብርሃ እና ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ አሁንም በመከላከያ ሚኒስትርነትና በፕሬዝዳንትነት ሲያገለግሉት የነበረውን የህወሓት/ኢህአዲግ አገዛዝ ከመንቀፋቸውም በላይ አቶ ስየ አብርሃ ከፍተኛ ትኩረት ለሳበው የቢቢሲ ዘገባ ምላሽ ሰጥተዋል። ሙሉውን አስነብበኝ ...