ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ በደህንነቶች ታፈነ
Ethiopia Zare (ኀሙስ የካቲት 27 ቀን 2000 ዓ.ም. March 6, 2008)፦ የሓዳር ጋዜጣ አሣታሚና ዋና አዘጋጅ የነበረው ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ዛሬ ጠዋት በደህንነት ሰዎች ታፍኖ መወሰዱን የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጭ አረጋገጠ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...Ethiopia Zare (ኀሙስ የካቲት 27 ቀን 2000 ዓ.ም. March 6, 2008)፦ የሓዳር ጋዜጣ አሣታሚና ዋና አዘጋጅ የነበረው ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ዛሬ ጠዋት በደህንነት ሰዎች ታፍኖ መወሰዱን የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጭ አረጋገጠ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...Ethiopia Zare (ማክሰኞ የካቲት 25 ቀን 2000 ዓ.ም. March 4,2008)፦ በጉጂ እና በቦረና ጎሣዎች መካከል በተነሳ ከፍተኛ ግጭት በዛሬው ዕለት ደን እንደተቃጠለ ዛሬ ማምሻውን የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች ጠቆሙ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...Ethiopia Zare (ማክሰኞ የካቲት 25 ቀን 2000 ዓ.ም. March 4,2008)፦ የቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ በዛሬው ዕለት ወደ አዋሣ ከተማ ተጉዘው በቅንጅት ስም ተመርጠው ደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ከገቡ 23 አባላት ጋር መወያየታቸውን የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች ገለጹ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...Ethiopia Zare (ቅዳሜ የካቲት 22 ቀን 2000 ዓ.ም. March 1,2008)፦ ቅዳሜ ማምሻውን የተሰበሰበው የቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ላዕላይ ምክር ቤት ድርጅቱን በአዲስ ስም ለማስመዝገብ የወሰነ ሲሆን፣ በጎደሉ የሥራ አስፈጻሚ ምትክም አምስት አባላትን የመረጠ መሆኑን ከአዲስ አበባ የደረሰን ዘገባ ጠቆመ።
Ethiopia Zare (ዓርብ የካቲት 21 ቀን 2000 ዓ.ም. February 28,2008)፦ በተቀዳሚ ም/ሊቀመንበሯ ወ/ት ብርቱካን የሚመራው የቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ዛሬ ሊያደርገው የነበረውን የላዕላይ ምክር ቤት ስብሰባ ለነገ ቅዳሜ የካቲት 22 ቀን 2000 ዓ.ም. ማዛወሩን ምንጮቻችን ገልፀዋል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...Ethiopia Zare (ዓርብ የካቲት 21 ቀን 2000 ዓ.ም. / February 29,2008)፦ ዛሬ ረፋዱ ላይ በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከቀኑ ስምንት ሰዓት አካባቢ መርካቶ በሚገኘው ራጉዔል ቤተክርስቲያን አካባቢ "ቁጭራ" በሚባለው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ አጠገብ ቦንብ ፈንድቶ በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን፣ ይህንን ዘገባ እስካጠናከርንበት ሰዓት ድረስ በሰው ሕይወት ላይ ያደረሰውን ጉዳት ለማወቅ አልቻልንም።
ሙሉውን አስነብበኝ ...Ethiopia Zare (ዓርብ የካቲት 21 ቀን 2000 ዓ.ም. February 29,2008)፦ ማህተምና የጽህፈት ቤት መሳሪያዎች አላስረክብም ብለዋልና የነአቶ ተመስገን ዘውዴ ያለመከሰስ የፓርላማ መብት ይነሳልኝና ልክሰሳቸው በማለት አቶ አየለ ጫሚሶ ለፓርላማ ክስ አቀረቡ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...• የሟች ቤተሰቦች ስጋት ላይ ወድቀዋል
• አንድ የክልል ባለሥልጣን ለገዳዩ ከለላ ሰጥቶታል ተብሏል
በሸዋዬ ካሳሁን
Ethiopia Zare (አርብ የካቲት 21 ቀን 2000 ዓ.ም. February 29, 2008)፦ ከአዲስ አበባ በስተሰሜን ራያ ቆቦ በተባለው ከተማ በቂም በቀል በመነሳሳት የሰው ሕይወት ያጠፋው ግለሰብ እስካሁን ድረስ በቁጥጥር ሥር ሊውል ባለመቻሉ በየሟች ቤተሰቦች ስጋት ላይ ወድቀዋል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...Ethiopia Zare (ዓርብ የካቲት 21 ቀን 2000 ዓ.ም. February 29, 2008)፦ ከአዲስ አበባ ከተማ በስተደቡብ በምትገኘው ዲላ ከተማ ባለው «ዲላ ዩኒቨርስቲ» በተገደለ አንድ ተማሪ ምክንያት ዩኒቨርስቲው ተረበሸ። ተማሪውን ገድሎታል በሚል የተጠረጠረው ተማሪም በቁጥጥር ስር ውሏል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...Ethiopia Zare (ሐሙስ የካቲት 20 ቀን 2000 ዓ.ም. February 28,2008)፦ የቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ፓርቲ በተ/ም/ሊ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ የሚመራው የላዕላይ ምክር ቤት ነገ አርብ ስብሰባ እንደሚያካሂድ ታማኝ ምንጮች ጠቆሙ።