ዛሬ ለቴዲ አፍሮ ወሳኝ ቀን ነው

Ethiopia Zare (ሰኞ ሐምሌ 14 ቀን 2000 ዓ.ም. July 21, 2008)፦ የብዙዎችን ቀልብ ገዝቶ የቆየው ታዋቂውና ተወዳጁ አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን ከሦስት ወራት የእስር ቆይታ በኋላ በአወዛጋቢው የምኒልክ ሆስፒታል የሰነድ ማስረጃ የዓቃቤ ሕግ ክርክር ተደምድሟል። ፍርድ ቤቱም በዛሬው ችሎቱ በጉዳዩ ላይ ብይን ለመስጠት ቀጠሮ ሰጥቷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የጉምሩክ ሥራ አስኪያጅ በፖሊስ ተይዘው እንዲቀርቡ ታዘዘ

የፍ/ቤቱ ትዕዛዝ 15 ቀን ቢሆነውም እስካሁን አልቀረቡም

መስሪያ ቤቱ ጉዳዩን በሰበር አሳግዷል

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ሐምሌ 12 ቀን 2000 ዓ.ም. July 19, 2008)፦ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ባለሥልጣን ሥራ አስኪያጅን ፖሊስ አስሮ እንዲያቀርባቸው ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጠ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

“በአሸባሪነት የተጠረጠሩ 28 እስረኞችን በዋስ ለቀዋል” በሚል የተከሰሱት ዳኛ ለክሱ ምላሽ ሰጡ

በስድስት ሠራተኞችም ክስ ቀርቦባቸዋል

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ሐምሌ 12 ቀን 2000 ዓ.ም. July 19, 2008)፦ በአሸባሪነት ተጠርጥረው የተያዙ 28 እስረኞችን በዋስ ለቀዋል በሚል በቀረባበቸው የዲሲፕሊን ክስ ላልተወሰነ ጊዜ የሚቆይ የሥራ እግድ የተጣለባቸው ዳኛ ኑሩ ሰዒድ የተከሰሱበትን ጉዳይ አስመልክተው ለዳኞች አስተዳደር ጉባዔ በደብዳቤ መልስ መስጠታቸውን ምንጮች ጠቆሙ። በዳኛው ላይ በስድስት የድጋፍ ሰጪ ሠራተኞችም ክስ ቀርቦባቸዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የድሬዳዋ ኤፍ.ኤም. ራዲዮ ጣቢያ ተቃጥሎ ከ1.3 ሚሊዮን ብር በላይ ንብረት ወደመ

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ሐምሌ 12 ቀን 2000 ዓ.ም. July 19, 2008)፦ ባለፈው እሁድ ሐምሌ 6 ቀን 2000 ዓ.ም. የድሬዳዋ ኤፍ.ኤም. ራዲዮ በከተማው ጊዜያዊ አስተዳደር ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ሕንፃ አራተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው ስቱዲዮው መደበኛ ዝግጅቱን እያስተላለፈ ሳለ ከቀኑ 9 ሰዓት ከ53 ደቂቃ ላይ ስቱዲዮ ውስጥ የነበሩት የዕለቱ ተረኛ አዘጋጆች መቆጣጠሪያ እየተባለ ከሚጠራው ክፍል ጭስ ሲጨስ በማየታቸው ዝግጅታቸውን አቋርጠው ዘለው ይወጣሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የፋሺስት ኢጣሊያ ግፍ አሁንም ያነጋግራል

Alpini WarcrimesEthiopia Zare (ቅዳሜ ሐምሌ 12 ቀን 2000 ዓ.ም. July 19, 2008)፦ ከዛሬ 73 ዓመት በፊት የፋሺስት ኢጣሊያ ሠራዊት በኢትዮጵያኖች ላይ አሰቃቂ ግፍና ጭፍጨፋ መፈፀሙ የቅርብ ጊዜ ታሪካችን ነው። በወቅቱ የፋሺስት ሠራዊት በተጠቀመው የመርዝ ጋዝ ያደረሰው እልቂት ከፍተኛ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ፎርቹን ጋዜጣ በፕሬስ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ 20 ሚሊዮን ብር ካሣ እንዲከፍል ክስ ቀርቦበታል

ፎርቹን ጋዜጣ ከአንበሳ አውቶቡስ ክስ በነፃ ተሰናበተ

የአያት እና የሣባ ኢንጂነሪንግ ክስ ይቀረዋል

Ethiopia Zare (ዓርብ ሐምሌ 11 ቀን 2000 ዓ.ም. July 18, 2008)፦ በግል ፕሬስ ታሪክ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በ20 ሚሊዮን ብር የካሣ ጥያቄ ክስ የተመሰረተበት ”ፎርቹን” የተባለው ሀገር ውስጥ የሚታተመው የእንግሊዝኛ ጋዜጣ በስም ማጥፋት ከቀረቡበት ሦስት ክሶች የአንበሳ ከተማ አውቶቡስ ክስን ሲረታ፤ የአያት ሪል ስቴት ክርክር እንዲቀጥል ትዕዛዝ የተሰጠበት ሲሆን፣ ለሣባ ኢንጂነሪንግ ክስ ደግሞ መልስ አቅርቧል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አና ጐሜዝ የአውሮፓ ሕብረት መሪዎችን ወቀሱ

Anna GomezEthiopia Zare (ዓርብ ሐምሌ 11 ቀን 2000 ዓ.ም. July 18, 2008)፦ የአውሮፓ ፓርላማ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ አባልና ዲፕሎማት የሆኑት ሚስ አና ጐሜዝ የአውሮፓ ሕብረት መሪዎች በቡድን 8 ሀገሮች ጉባዔ ላይ በሰብዓዊ መብት ረገጣ ከሚወቀሱ የአፍሪካ መሪዎች ጋር መሆን ለሰብዓዊ መብት ጥበቃ ያላቸው አመለካከት ዝቅተኛ ነው በማለት ወቀሱ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አንድነት ፓርቲ ስሙን ተከለከለ

Ethiopia Zare (ኀሙስ ሐምሌ 10 ቀን 2000 ዓ.ም. July 17, 2008)፦ “አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ” በሚል ስያሜ ፓርቲ ለማቋቋም ጠቅላላ ጉባዔውን አካሂዶና አስፈላጊውን ማስረጃዎችና ፎርማሊቲዎች አሟልተው ባለፈው ሣምንት ረቡዕ ለምርጫ ቦርድ ፈቃድ መጠየቂያ ማመልከቻውን ያስገቡትና መሥራቾቹ “አንድነት” የሚለውን ስም መጠቀም እንደማይችሉ ምርጫ ቦርድ በዛሬው ዕለት መግለጹን ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ምንጮቻችን ገለጹ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...