የቴዲ አፍሮን ጉዳይ የሚያዩት ዳኛ በጠበቃው ሊከሰሱ ነው

Teddy AfroEthiopia Zare (ቅዳሜ ሐምሌ 19 ቀን 2000 ዓ.ም. July 26, 2008)፦ የቴዲ አፍሮን ጉዳይ በዳኝነት በመመልከት ላይ ያሉትን ዳኛ ልዑል ገብረማርያምን እና የምኒልክ ሆስፒታል አስተርጓሚ ሊከሰሱ ነው። ከሳሻቸው የቴዲ አፍሮ ጠበቃ አቶ ሚሊዮን አሰፋ ሲሆን፣ በብይኑ ላይም ይግባኝ ሊል መሆኑን ለአዲስ ነገር ጋዜጣ ገለጸ። 

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሦስት የቀይ መስቀል መድኃኒት ቤቶች በአዲስ አበባ ተዘጉ

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ሐምሌ 19 ቀን 2000 ዓ.ም. July 26, 2008)፦ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር፣ በአዲስ አበባ የሚገኙ ሦስት የመድኃኒት መሸጫ መደብሮቹ ተዘጉ። የማኅበሩ መድኃኒት ቤቶች፣ የመድኃኒት ዋጋቸው ተመጣጣኝ መሆን ለተጠቃሚው ኅብረተሰብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክቱ እንደነበር ታውቋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ለሎሬት ፀጋዬ ገ/መድኅን መታሰቢያ አዲስ ድረ ገጽ ተከፈተ

L. Tsegaye G/MedhinEthiopia Zare (ኀሙስ ሐምሌ 17 ቀን 2000 ዓ.ም. July 24, 2008)፦ ለታዋቂው ኢትዮጵያዊ የሥነ ጥበብ አባት ለሎሬት ፀጋዬ ገብረመድኅን መታሰቢያ ይሆን ዘንድ በመጀመሪያ ስሙ መጠሪያ ”ፀጋዬ” የተሰኘ ድረ ገጽ መከፈቱንና በይፋ ሥራውን መጀመሩን ድረ ገጹ በዛሬው ዕለት ለኢትዮጵያ ዛሬ በላከው ኢ-ሜይል ገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አንድነት ምርጫ ቦርድ የጠየቀውን ማሻሻያዎች አሟልቶ አስገባ

ስሙን በሚመለከት ማሻሻያ ሳያደርግ ቦርዱ እንዲወስንለት ጠየቀ

Ethiopia Zare (ኀሙስ ሐምሌ 17 ቀን 2000 ዓ.ም. July 24, 2008)፦ ”አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ” ፓርቲ ለምርጫ ቦርድ ፈቃድ መጠየቂያ ማመልከቻ ካስገባ በኋላ፤ ባለፈው ሣምንት ኀሙስ ዕለት ምርጫ ቦርድ በጽ/ቤቱ በኩል አስር ነጥቦችን ዘርዝሮ ማሻሻያዎችና ለውጦች እንዲደረግባቸው ለፓርቲው በደብዳቤ አሳውቆ በነበረው መሠረት፣ ፓርቲው በዛሬው ዕለት በደብዳቤ ምላሽ መስጠቱን ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች ገለጹ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የቴዲ አፍሮን ፎቶ በፊት ገጹ ያተመው ጋዜጣ ተከሰሰ

Teddy AfroEthiopia Zare (ኀሙስ ሐምሌ 17 ቀን 2000 ዓ.ም. July 24, 2008)፦ ቴዲ አፍሮን ፖሊሶች ሲጎትቱት የሚያሳየውን ፎቶግራፍ (በግራ በኩል የሚታየውን ፎቶ) በፊት ገጹ ላይ ያወጣው በሀገር ውስጥ የሚታተመው ”መሰናዘሪያ” የተባለው ጋዜጣ በፎቶግራፉ ምክንያት መከሰሱን ለኢትዮጵያ ዛሬ የደረሰው መረጃ አስረዳ። የጋዜጣው ዋና አዘጋጅ ወሰንሰገድ መሸሻን ፖሊስ ጠርቶታል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

እነኢ/ር ኃይሉ ”ቅንጅት”ን በፍ/ቤት ተከለከሉ

Eng. Hailu Shawelበመኢአድ ስም ሊቀጥሉ ይችላሉ

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ሐምሌ 15 ቀን 2000 ዓ.ም. July 22, 2008)፦ የቅንጅት አመራሮች ከእስር ከተፈቱ በኋላ በተፈጠረው ልዩነት ኢ/ር ኃይሉ ሻውል የሚመሩት ቡድን ”ቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ፓርቲ” ይገባኛል በማለት ምርጫ ቦርድን ከስሶ ሲከራከር የነበረ ሲሆን፣ በዛሬው ዕለት የዋለው ችሎት ለምርጫ ቦርድ ወስኖ እነኢ/ር ኃይሉ ሻውልን ”ቅንጅት” የሚለውን ስም መከልከሉን ለኢትዮጵያ ዛሬ የደረሰው መረጃ ጠቆመ። 

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ትናንት የቴዲ አፍሮን ችሎት ከተከታተሉት አስሩ ታስረው፣ 5ቱ ዛሬ ፍ/ቤት ቀረቡ

Teddy Afroየታሰሩት “ችሎት ረብሻችኋል፣ ድንጋይ ወርውራችኋል” በሚል ነው

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ሐምሌ 15 ቀን 2000 ዓ.ም. July 22, 2008)፦ በትናትናው ዕለት የቴዲ አፍሮን ችሎት ለመከታተል ከመጡ ችሎት ተከታታዮች መካከል አስሩ ታሰሩ። በዛሬው ዕለትም ፖሊስ ሜክሲኮ በሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ ነክ ፍርድ ቤት አምስቱን አቅርቧቸው የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ የጠየቀባቸው ሲሆን፣ ፍርድ ቤቱ ፈቅዶለታል። 

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በቤጂንጉ ኦሎምፒክ ተሳታፊ አትሌቶች ስም ዝርዝር ታወቀ

የእነ ኃይሌ ገ/ሥላሴ ሥራ አስኪያጅ ማስጠንቀቂያ ተሰጠው

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ሐምሌ 15 ቀን 2000 ዓ.ም. July 22, 2008)፦ የፊታችን ነሐሴ 3 ቀን 2000 ዓ.ም. (August 8, 2008) በሚከፈተው የቤጂንጉ ኦሎምፒክ የሚሳተፉ አትዮጵያውያን አትሌቶች ታወቁ። በዚህ በቻይና በሚደረገውና 17 ቀናት በቀሩት ኦሎምፒክ ላይ ኢትዮጵያ በአምስት የተለያዩ ውድድሮች በሴቶችም በወንዶችም ትሳተፋለች።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ቴዲ ለሚቀጥሉት 75 ቀናት ቃሊቲ ይቆያል

Teddy Afro- ክሱን ተከላከል ተባለ

- ወዳጅ ዘመዶቹ በእንባ ተራጭተዋል

Ethiopia Zare (ሰኞ ሐምሌ 14 ቀን 2000 ዓ.ም. July 21, 2008)፦ አዲስ አበባ በፍተኛ ዝናብ ተውጣለች። ዝናቡን ከምንም ያልቆጠሩ የቴዲ አፍሮ ቤተሰቦች፣ ጓደኞችና አድናቂዎቹ በከፍተኛው ፍርድ ቤት መግቢያ በር ላይ በተለመደው ሁኔታ ሰልፍ ይዘዋል። ከላይ ስለሚወርድባቸው ዝናብ አንድም ያዘነ ፖሊስ አለነበረም። “ምናለበት ውስጥ ገብተን ብንጠብቅ?” የሚለው ጥያቄም መልስ አላገኘም። በተለመደው ሰዓት ከጠዋቱ 2፡45 ሲሆን፣ ወደ ግቢው እንድንገባ ተፈቀደ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የጁላይ ሃያው የሲያትሉ ህዝባዊ ውይይት (ሪፖርታዥ)

”እንደትናንቱ ሁሉ ዛሬም አብራችሁን እንድትሆኑ እጠይቃለሁ” አቶ አስራት ጣሴ

”ለአኝዋክ ህዝብ ብቻ መታገል መፍትሔ አያመጣም” አቶ ኦባንግ ሜቶ

”በዓለም ላይ ካሉ ሀገሮች ምንም ሥራ የማይሠራው የአቶ መለስ ዜናዊ መንግሥት ብቻ ነው” ፕ/ር አለማየሁ ገ/ማርያም

”ኢትዮጵያዊነታችሁ የማትገላገሉት ስለሆነ የምትኮሩባት ኢትዮጵያ እንድትሆን መታገል አለባችሁ” ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም

Andenet public meeting in Seattle, July 20, 2008

Ethiopia Zare (ሰኞ ሐምሌ 14 ቀን 2000 ዓ.ም. July 21, 2008)፦ ትናንት እሁድ ሐምሌ 13 ቀን 2000 ዓ.ም. አንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ በሲያትል ከህዝብ ጋር ያደረገው ውይይት በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁ ታወቀ። በዚህ ህዝባዊ ውይይት ላይ ተጋባዥ ተናጋሪዎች የነበሩት ፕ/ር መስፍን ወልደማርያምና አቶ አስራት ጣሴ ከአንድነት ፓርቲ፣ ፕ/ር አለማየሁ ገ/ማርያም እና አቶ ኦባንግ ሞቶ ናቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...