የኢትዮጵያ ድምጽ ሬድዮ (ስዊድን) አመታዊ በአሉን አከበረ

ደራሲ ገጣሚና ባለቅኔ ኃይሉ ገብረዮሃንስ እና ጋዜጠኛ አህመድ አሊ ተሸላሚ ሆኑ

ማትያስ ከተማ

ደራሲ ገጣሚና ባለቅኔ ኃይሉ ገብረዮሐንስ

Ethiopia Zare (ሐሙስ መስከረም 3 ቀን 2005 ዓ.ም. September 13, 2012) የኢትዮጵያን አዲስ ዓመት አንተርሶ የምስረታ በአሉን በየዓመቱ የሚአከብረው የኢትዮጵያ ድምጽ ራድዮ አስራ ዘጠነኛ አመቱን በርካታ ኢትዮጵያውያን ታዳሚዎች በተገኙበት ቅዳሜ ሴፕቴንበር 8,2012 (ጳጉሜ 3,2004 ዓ.ም) አከበረ። በበአሉ አከባበር ላይ ደራሲ ገጣሚና ባለቅኔ ኃይሉ ገብረዮሃንስን በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን የተዘጋጀላቸውንም የክብር ሽልማት ተቀብለዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በኢትዮጵያ ታስረው የነበሩት ሁለት የስዊድን ጋዜጠኞች ተፈቱ

በድምሩ 1900 እስረኞች አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ከእስር ይፈታሉ

ጋዜጠኞች ዮሐን ፐርሾን (በግራ) እና ማርቲን ሺቢ (በቀኝ) Johan Persson (L) and Martin Schibbye (R)Ethiopia Zare (ሰኞ ጳጉሜን 5 ቀን 2004 ዓ.ም. September 10, 2012)፦ ላለፉት አስራ አራት ወራት በእስር የቆዩትና በሽብረተኝነት ክስ ተመስርቶባቸው የ11 ዓመት እስራት የተፈረደባቸው ስዊድናውያን ጋዜጠኞች ማርቲን ሺቢ እና ዮሐን ፐርሾን ዛሬ ጳጉሜን 5 ቀን ማምሻውን በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከ11 ሰዓት በኋላ መፈታታቸውን የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች አረጋገጡ። ከቃሊቲ ወጥተው በቀጥታ ወደ ስዊድን ኤምባሲ መሄዳቸው ታውቋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአክቲቪስትና አርቲስት ታማኝ የአውስትራሊያ ቆይታ ጠቅላላ ሪፖርት

ላለፉት 8 ዓመታት አገራዊ ፋይዳ ያላቸውንና ለህዝባችን ሁለንተናዊ ነጻነት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን በመደገፍ ሲንቀሳቀስ የቆየው የሜልበርን ዲሞክራሲ ለኢትዮጵያ ድጋፍ ቡድን ባደረገለት ግብዣ በ 12/08/12 አውስትራሊያ የገባው ተወዳጁና እውቁ የጥበብ ሰው አርቲስት ታማኝ በየነ በአውስትራሊያ 5 የተለያዩ ከተሞች ማለትም በሜልበርን ፤ በሲድኒ፤ በአድላይድ፤ በብሪዝበንና በፐርዝ በተከናወኑ የኢሳት ድጋፍ ማሰባሰቢያ ዝግጅቶች ላይ በመገኘት ከ 115 ሺህ በላይ ዶላር ማሰባሰብ ችሏል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሀዘን ለመግለጽ የተሰበሰቡ አርቲስቶች የእዝን መዋጮ ተጠየቁ

ሰራዊት ፍቅሬና እቁባይ በርሄ ሚና ተጫውተዋል

ልዩ ሪፓርታዥ (ከአዲስ አበባ)

Ethiopia Zare (ማክሰኞ  ነሐሴ 22 ቀን 2004 .. August 28, 2012)፦ የአቶ መለስ ሞትን ተከትሎ በሀገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች ዜጎች ሀዘናቸውን በአደባባይ ወጥተው እንዲገልጹ በድርጅታዊ አሰራር እየተገደዱ መሆኑ ሲታወቅ በየመስሪያ ቤቱና በየዩኒቨርሲቲዎቹ ያሉ ሰራተኞችና ተማሪዎች ጥቁር ለብሰው በተወሰነ ሰዓት እንዲሰባሰቡ የታዘዙባቸው ደብዳቤዎች ለይፋ እይታ በቅተዋል። በተመሳሳይ መልኩ ለገዥው መንግስት ሁነኛ አገልጋይ በሆኑት በሰራዊት ፍቅሬ እና በእቁባየይ በርኸ  አስተባባሪነት የተሰባሰቡ አርቲስቶች የእዝን ገንዘብ ቃል እንዲገቡ መደረጉን በስፍራው የተገኘው የኢትዮጵያ ዛሬ ተባባሪ ሪፖርተር አመልክቷል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የጠ/ሚ መለስ ዜናዊ አስከሬን ከሀገር ውጭ ነው

  • “ቤተሰቦቻቸው አብረዋቸው ናቸው”
  • “ቀብራቸው እስኪፈፀም ብሔራዊ የኀዘን ቀን ታውጇል”
  • “ፓርላማው በቅርቡ ተሰብስቦ ም/ጠ/ሚኒስትሩን ቃለ-መኃላ ያስፈጽማቸዋል” አቶ በረከት ስምዖን

ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ለመጨረሻ ጊዜ ለህዝብ የታዩበት PM Meles Zenawis’ last public appearance

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ነኀሴ 15 ቀን 2004 ዓ.ም. August 21, 2012)፦ የመንግሥት መገናኛ ብዙኀን በዜናውቸው ዛሬ ጠዋት ላይ የጠ/ሚ መለስ ዜናዊን ማረፍ ከዘገቡ በኋላ በአንዳንዶች ላይ መደናገጥን፣ በአንዳንዶች ላይ ኀዘን የተስተዋለ ሲሆን፤ ታክሲ ላይ ሲያለቅሱ የታዩ ጥቂት ሰዎችም ነበሩ። አብዛኛው ሰው የመለስን መሞት ተለማምዶት ከመቆየቱ የተነሳ የአብዛኛው ሰው ዝምታ እንደመለስ ያለ አነጋጋሪ ጠቅላይ ሚኒስትር የመሞቱን ዜና የሰማ አይመስልም። ሁሉም ሰው የተለመደ ሥራውን እና የተለመደ እንቅስቃሴውን ቀጥሎ ተስተውሏል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ማረፋቸውን በመጨረሻ መንግሥት አመነ

የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ Former PM Meles Zenawi

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ነኀሴ 15 ቀን 2004 ዓ.ም. August 21, 2012)፦ በመጨረሻም የኢትዮጵያ መንግሥት ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ በ57 ዓመታቸው ማረፋቸውን ዛሬ ጠዋት በመንግሥት መገናኛ ብዙኀኑ አማካኝነት አመነ። ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ላለፉት ሁለት ወራት ከመገናኛ ብዙኀን ከመጥፋታቸውም በላይ በውጭ ሀገር የሚገኙ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን መታመማቸውን ቀጥሎም ማረፋቸውን ቢዘግቡም፤ አቶ በረከት ስምዖንን ጨምሮ ሌሎች ባለሥልጣናትም አቶ መለስ በሐኪም በታዘዘ እረፍት ላይ መሆናቸውን ሲገልጹና ሲያስተባብሉ መክረማቸው ይታወሳል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አትሌት መሰረት ደፋር ለኢትዮጵያ ሦስተኛውን ወርቅ አስገባች

ጥሩነሽ ዲባባ ደግሞ ነኀስ

አትሌት መሰረት ደፋር በ5000 ሜትር የለንደኑን ኦሎምፒክ በአሸናፊነት ስትወጣ Meseret Defar of Ethiopia celebrates winning gold in the Women's 5000m Final

Ethiopia Zare (ዓርብ ነኀሴ 4 ቀን 2004 ዓ.ም. August 10, 2012)፦ አትሌት መሰረት ደፋር ዛሬ ማምሻውን በለንደን ኦሎምፒክ በተካሄደው የአምስት ሺህ ሜትር የሴቶች ሩጫ ውድድሩን በአንደኝነት በመጨረስ የወርቅ ሜዳሊያ ስታገኝ ጥሩነሽ ዲባባ ደግሞ ሦስተኛ በመውጣት የነኀስ ሜዳሊያ አግኝታለች። ገለታ ቡርቃ ደግሞ አምስተኛ ሆናለች።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በሴቶች ማራቶን አትሌት ቲኪ ገላና ክብረወሰን በመስበር ወርቅ አገኘች

አትሌት ቲኪ ገላና ክብረወሰን ስታስመዘግብ Tiki Gelana of Ethiopia celebrates as she crosses the finish line to win the gold

Ethiopia Zare (እሁድ ሐምሌ 29 ቀን 2004 ዓ.ም. August 5, 2012)፦ በለንደኑ ኦሎምፒክ በዛሬው ዕለት በተካሄደው የሴቶች ማራቶን ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ቲኪ ገላና ውድድሩን በ2፡23፡07 ሰዓት አንደኛ ወጥታ በመጨረስ የወርቅ ሜዳሊያ ከማግኘቷም በላይ የኦሎምፒክ ክብረወሰንን ሰብራለች።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ተሸነፈ፣ ወንድሙ ነኀስ አገኘ

”የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ወጣትና ተተኪ ሯጮችን የማዘጋጀትና የማሰለፍ ብቃት ያንሰዋል” አትሌቲክስ አፍቃሪ ኢትዮጵያውያን

አትሌት ሙሐመድ ፋራህ በ10 ሺህ ሜትር የለንደን ኦሎምፒክ  ሲያሸንፍ Mohamed Farah of Great Britain crosses the line to win gold in the Men's 10,000m

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ሐምሌ 28 ቀን 2004 ዓ.ም. August 4, 2012)፦ በዛሬው ዕለት በለንደን ኦሎምፒክ በተካሄደው የአስር ሺህ ሜትር የወንዶች ሩጫ ሶማሊያ ሞቃዲሾ ውስጥ የተወለደውና የ29 ዓመቱ የእንግሊዝ ሯጭ ሙሐመድ ፋራህ አንደኛ ሲወጣ፣ ኢትዮጵያውያኖቹ ወንድማቾች ታሪኩ በቀለ እና ቀነኒሳ በቀለ ሦስተኛና አራተኛ ወጥተዋል። ቀነኒሳ በቀለ በዚሁ ርቀት ያለፉትን ሁለት ኦሎምፒኮች ክብረወሰን መስበሩ ይታወሳል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ