ጥሩነሽ ዲባባ ለሁለተኛ ጊዜ በኦሎምፒክ በአስር ሺህ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ በለንደኑ ኦሎምፒክ በ10 ሺህ ሜትር በአንደኝነት ስታሸንፍ Tirunesh Dibaba wins gold in the women's 10,000m final on Day 7 of London 2012.

Ethiopia Zare (ዓርብ ሐምሌ 27 ቀን 2004 ዓ.ም. August 3, 2012) የ27 ዓመትዋ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ዛሬ በለንደኑ የ2012 ኦሎምፒክ ውድድር በተደረገው የሴቶች የአስር ሺህ ሜትር ለኢትዮጵያም ለራሷም የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች። አትሌት ወርቅነሽ ኪዳኔ እና በላይነሽ ኡልጂራ አራተኛና አምስተኛ በመሆን ጨርሰዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጁላይ 28 አምስት የፖለቲካ ድርጅቶች ለውይይት ተጋበዙ

”ቃሌ” የተሰኘው የፓልቶክ የፖለቲካ መወያያ ክፍል ጁላይ 28 ቀን 2012 እ.ኤ.አ. ”ጥምረት ለነፃነት ለእኩልነትና ለፍትህ በኢትዮጵያ”ን፣ ”ኦሮሞ ነጻነት ግንባር”ን፣ ”የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ”ን፣ ”የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ፓርቲ”ን እና ”የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሽግግር ምክር ቤት”ን በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ለውይይት መጋበዙን ለኢትዮጵያ ዛሬ ገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያዊው ወጣት የለንደን ኦሎምፒክ ችቦን አበራ

ወጣት ዲ/ን ሳሙኤል ብርሃኑ እና ከንቲባ ሮቤን ዌልስ በመድረክ ላይበታምሩ ገዳ

የፊታችን አርብ ለንደን ውስጥ በሚከፈተው እና በብዙ ቢልዮኖች የሚቆጠር የአለም ህዝብን ትኩረት እና ቀልብ ለመጪዎቹ አራት ሳምንታት ይስባል ተብሎ በሚገመተው የለንደን 2012 እኤአ የኦሎምፒክ እና ፓራ ኦሎምፒክ ውድድርን ምክንያት በማደርግ ላለፉት ሶስት ወራት ከጥንታዊቷ የኦሎምፒክ አገር ግሪክ ተነስቶ በመላው የእንግሊዝ ከተሞች ሲበራ የነበራው የኦሎምፒክ ችቦ ለንደን ከተማ ውስጥ አርብ ዕለት ገብቷል። በበነጋታው (ቅዳሜ ዕለት) በመዲናይቱ ጎዳናዎች ላይ በተደረገው የችቦ ማብራት ስነስርአት ላይ የተሳተፈው ወጣት ኢትዮጵያዊ ችቦ አብሪ ከማህበረሰቡ ከፍተኛ አድናቆት እና ድጋፍ ተቸሮታል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አቶ መለስ ዜናዊ ኢንቴንሲቭ ኬር ክፍል ውስጥ ናቸው

የሕወሀት ቱባ ባለስልጣናት በሚስጢር ተከታታይ ስብሰባዎችን እያደረጉ ነው

Ethiopia Zare (ሐሙስ ሐምሌ 12 ቀን 2004 ዓ.ም. July 19, 2012)፦ የጠ/ሚ መለስ ዜናዊ የጤና ሁኔታ አሁንም አወዛጋቢነቱ የቀጠለ ሲሆን በቤጂየም ሆስቲታል በኢንቴንሲቭ ኬር ክፍል አካባቢ ጠባቂዎቻቸውን የተመለከተ ኢትዮጵያዊ ይፋ አደረገ። የህወሃት ቱባ ባለስልጣናት በሀገር ቤት በሚስጥር በተደጋጋሚ ስብሰባዎችን እያደረጉ መሆኑም ታውቋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የዝንጀሮ ችሎት በእነ እስክንድር ላይ ፍርድ ሰጠ

እስክንድር ነጋ 18 ዓመት እስር ተወስኖበታል

አንዷለም አራጌ እድሜ ልክ እስራት ተብሏል

ቁጥር ለመስማት ነበር የሄድነው እሱን ሰምተን ተመልሰናልየእስክንድር ባለቤት ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል

Ethiopia Zare (አርብ ሐምሌ 6 ቀን 2004 .. july 13, 2012)፦ በህወሃት ኢህአዴግ ቁጥጥር ስር የሚገኘውና አሻንጉሊት ዳኞችን በመሰየም የሚታወቀው የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት ዛሬ በእነ እስክንድር ነጋ ላይ ውሳኔ ሰጠ። አንዷለም አራጌ የእድሜ ልክ ሲፈረድበት ጋዜጠኛና የፖለቲካ ተንታኝ የሆነው እስክንድር ነጋ 18 ዓመት ተወስኖበታል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

በማላዊ ሀይቅ የሞቱት ኢትዮጵያዊያን ተገቢው ቀብር ሊደረግላቸው ነው

በጅምላ መቀበራቸው ቀይ መስቀልን አሳስቦታል

ስድስት ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በተአምር ተርፈዋል!!

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ሐምሌ 3 ቀን  2004 .. july 10, 2012)፦ ባለፈው ወር መጨረሻ ላይ ወደ ደቡብ አፍሪካ በማምራት ላይ የነበሩ ኢትዮጵያውያንን የጫነች ጀልባ በማላዊ ሃይቅ ላይ በመገልበጧ 47 ኢትዮጵያን ወንዶች፣ ሴቶችና ሀጻናት መሞታቸው ሲታወስ በወቅቱ በእካባቢው ነዋሪዎች አማካኝነት ከሃይቁ ዳርቻ ጥቂት ሜትሮች ርቀት ላይ በተቆፈረ ጉድጓድ ውስጥ በጥድፊያ እንዲቀበሩ በመደረጋቸው ለሟቾቹ ክብር ያልሰጠ ሂደት ነው በሚል ቀይ መስቀል እንደ አዲስ ተገቢ ቀብር እንዲፈጸምላቸው ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን ዘ ሰንዴይ ታይምስ የተሰኘ የአገሪቱ ጋዜጣ ዘግቧል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

እነ እስክንድር ነጋ አለም በቃ ይጠብቃቸዋል

ጥፋተኛ ናችሁ የሚል ብይን ተሰጥቷል

 

Ethiopia Zare (ረቡዕ ሰኔ 20 ቀን 2004 .. june 27, 2012)፦ በእነ አንዷለም አራጌ የክስ መዝገብ ከአወዛጋቢው የሽብርተኝነት አዋጅ ጋር በተያያዘ ከመስከረም ወር ጀምሮ በማሰቃያነቱ በሚታወቀው የማእከላዊ እስር ቤትና በቃሊቲ ወህኒ ቤት የቆዩት 24 ተከሳሾች ላይ የጥፋተኝነት ብይን ተሰጠ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በፍትህ ጋዜጣ ላይ የተጣለው አደጋ ስጋት ፈጥሯል

ፍትህ ጋዜጣ አልሻባብ ጋር ግንኙነት አለው የሚያስብል ኢሜል ተልኳል

(ሊያነቡትና ሊያውቁት የሚገባ)

Ethiopia Zare (ሰኞ ሰኔ 18 ቀን 2004 ዓ.ም. june 25, 2012)በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ ተነባቢነት ያገኘችውና በህወሃት መራሹ የኢትዮጵያ መንግስት ዘንድ በአይነ ቁራኛ የምትጠበቀው የፍትህ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ባልደረቦችና በተለይም ሳምንታዊ ትችቶቹን በመጣጥፍ መልክ በማቅረብ የሚታወቀው ታዋቂው የፍትህ ጋዜጣ መስራችና ዋና አዘጋጅ የሆነው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ከፍተኛ ጫና የሚከቱ ማስፈራሪያዎች በመንግስታዊ ጋዜጦች ላይ እየወጡ መሆኑ ታወቀ። በተለይ ሰሞኑን ፍጹም በተለየ መልኩ ለተምስገን ዳሳለኝ መሰረት የለሽ ጽሁፎች በኢሜል እየደረሱት እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

በቫንኩቨር ጸደንያ ቅድስት ማሪያም ቤ/ክርስቲያን ለዋልድባ ገዳም ምህላ ተያዘ

"ትእቢተኛ ነገስታት የነበሩት እነ ናቡከደነጾር በጸሎት ተሸንፈዋል" መላከጸሐይ አፈወርቅ

Ethiopia Zare (እሁድ ሰኔ 10 ቀን 2004 ዓ.ም. June 17, 2012)በቫንኩቨር-ካናዳ የምትገኘው ጸደንያ ቅድስት ማሪያም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ የሆኑት መላከ ጸሐይ አፈወርቅ በዋልድባ ገዳም አካባቢ እየተፈጸመ ያለውን የእርሻ ቁፋሮ እና በመነኮሳት ላይ እየደረሰ ያለውን እንግልት ለማስቆም የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ኃይማኖት ተከታይ ምእመናን ምህላ እንዲገቡ ጥሪ አስተላለፉ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኮለኔል መንግስቱ መጽሀፍ ኢትዮጵያ ውስጥ እየተቸበቸበ ነው

በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ ታተመ!

Ethiopia Zare (ሐሙስ ሰኔ 7 ቀን 2004 ዓ.ም. june 14, 2012)በጸሐይ አሳታሚ ድርጅት የታተመው እና በቀድሞው የኢትዮጵያ ፕ/ት በኮለኔል መንግስቱ ኀ/ማርያም የተጻፈው 'ትግላችን' የተሰኘው መጽሀፍ የመጀመሪያ ክፍል ኢትዮጵያ ውስጥ ታትሞ በስፋት እየተሰራጨ ሲሆን በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ ብቻ ለሶስተኛ ጊዜ መታተሙን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች በተለይ ለኢትዮጵያ ዛሬ ገለጹ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ