ስብሃት ገ/እግዚአብሔር በመጨረሻዋ ሰዓት

Sebhat Gebregziabher ስብሃት ገ/እግዚአብሔር

“በሰላም ነው ማረፍ የምፈልገው ከዚህ በሗላ መኖር አያሻኝም።” ጋሼ ስብሃት

“አካሉ ቢደክምም አእምሮው ግን አስከመጨረሻው የሰላ ነበር” ደራሲና ጋዜጠኛ ዘነበ ወላ

 

Ethiopia Zare (ማክሰኞ የካቲት 13 ቀን 2004 ዓ.ም. February 21, 2012)፦ በስነ ጽሁፍ ስራዎቹ ከፍተኛ ዝናንና ክብርን ያተረፈው አንጋፋው የስነ ጽሁፍ ሰው ደራሲና ጋዜጠኛ ስብሃት ገ/እግዚአብሔር ባደረበት የጉሮሮ ካንሰር ህመም ምክንያት ሰኞ የካቲት 12 ቀን ከሌሊቱ 9ሰዓት ላይ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

በኦታዋ ካናዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በግፍ ለታሰሩ አርበኞች የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ

ፎረም ኦታዋ ለሰብዓዊ መብትና ለዲሞክራሲ በሚል መጠሪያ የተሰባሰቡ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በወያኔ እስር ቤት ተጥለው በመማቀቅ ላይ ለሚገኙ አርበኞችና ቤተሰቦቻቸው መርጃ የሚሆን ገንዘብ አሰባስበው ወደ አገር ቤት ላኩ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢህአዴግ መንግስት በርካታ የአረብ ቲቪዎችን እያወከ ነው

በኢሳት የተጀመረው እወካ ለአረብ ሀገራት ተርፏል

የእውቀት ማነስ ነው ተብሏል

Ethiopia Zare (ቅዳሜ የካቲት 10 ቀን 2004 ዓ.ም. February 18, 2012)፦ የኢትዮጵያ መንግስት የተቃዋሚዎችን ድምጽ ለመገደብ የተያያዘው የጃሚንግ (የእወካ) ስራ በርካታ የአረብ ቴሌቭዥን ጣቢያዎችንም ከስርጭት ውጭ እያደረጋቸው መሆኑ ከፍተኛ ቁጣ አስነስቷል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

በኦሞ ሸለቆ የ200ሺህ ዜጎች ህይወት አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል!

“አንፈናቀልም” ያሉ እየታሰሩ ነው

Ethiopia Zare ( ሐሙስ የካቲት 8 ቀን 2004 ዓ.ም. February 15, 2012)፦ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የታችኛው ኦሞ ሸለቆ በመባል የሚታወቀው አካባቢ መንግስት በህንድ ኩባንያዎች ከፍተኛ ኢንቨስትመንት ለሚታገዘው ኩራዝ የስኳር ልማት ፕሮግራም እንዲውል 300ሺህ ሄክታር የሚጠጋ መሬት በመመደቡ የአካባቢው ነዋሪዎች ህልውና አደጋ ውስጥ ወደወቋል ሲል አልጀዚራ ዘገበ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የንግስት ሳባ የወርቅ ምንጭ ተገኘ

Ethiopia Zare (ረቡዕ የካቲት 7 ቀን 2004 ዓ.ም. February 14, 2012)፦ ከ3 ሺህ አመታት በፊት ሰፊ ግዛት ታስተዳድር እንደነበር በአፈ ታሪክ የምትታወቀው የንግስት ሳባ (ኩዊን ሼባ) የወርቅ ማውጫ ጉድጓዷ መሆኑ የታመነበት ስፍራ በትግራይ ውስጥ ገራልታ በተባለው አምባ ተገኘ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በየመን የኤምባሲ ተወካዮች ተዋርደው ከቤተክርስቲያን ወጡ...

ግሩም ተ/ሀይማኖት

ሀበሻ በየመን ክፍል 10

የምጀምረው በሁለት አሳዛኝ ዜና ነው፡፡ የመን ውስጥ ከሚታተሙት የግል ጋዜጣዎች አንዱ የሆነው አል-ሻራዕ የተባለው በ21/1 2012 ዕትሙ ሶስት ኢትዮጵያዊያን ተገደሉ በሚል የያዘውን ዘገባ ተርጉሜ እንደሚከተለው አስነብባለሁ። በዚህ ሰሞን በባህር ወደ የመን ከገቡ በርካታ ኢትዮጵያዊያን መካከል ሰላሳ የሚሆኑትን ወደ ሳዑዲ ለመውሰድ የጫናቸው መኪና ላይ በተከፈተ ተኩስ ሶስቱ ሲሞቱ የመናዊ ሾፌሩን ጨምሮ የቆሰሉም መኖሩ ተረጋገጠ፡፡ ማንነታቸውን የሚገልፅ ምንም አይነት መረጃ ካልተገኘላቸው ሟቾች ጋር ከነበሩት መካከል አምስት የሚሆኑትን ደግሞ ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል። የሟቾቹ ኢትዮጵያዊነትም የተረጋገጠው አብረዋቸው ካሉት ተጓዦች ነው፡፡ ሙሉውን አስነብበኝ ...

በጋምቤላ የምስጢር ደኅንነት ሠራተኛው ተገደሉ - (አኢጋን)

በጋምቤላ ክልል በምስጢር የደኅንነት አባል ሆነው ይሠራሉ የተባሉት አቶ ጌታቸው አንኮሬ ባልታወቁ ሰዎች በድንገት መገደላቸውን ተከትሎ ቀደም ሲል በክልሉ የነበረው ውጥረት በከፍተኛ ደረጃ መባባሱ ተገለጸ። የክልሉ ባለሥልጣናትና ካድሬዎችም ስጋት ላይ ወድቀዋል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

በሱማሊያ የኢትዮጵያ ጦር ሰፈር በአጥፍቶ ጠፊዎች ተጠቃ!

አልሸባብ 10 ወታደሮች ገደልኩ ብሏል

Ethiopia Zare (ረቡዕ ጥር 21 ቀን 2004 ዓ.ም. January 25, 2012)፦ በደቡብ ምዕራብ ሶማሊያ በሚገኘው የኢትዮጵያ ጦር ጠቅላይ ሰፈር ላይ የአልሸባብ አጥፍቶ ጠፊ በሚኒባስ ሙሉ የታጨቁ ቦምቦች ማፈንዳቱ ተዘገበ። በጥቃቱ 10 የኢትዮጵያ ወታደሮች መግደሉን አልሸባብ ገለጸ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

በአፋር ክልል ለታገቱት ጀርመናዊያን አርዱፍ ኃላፊነት ወሰደ

‘5ቱ ጎብኝዎች የሞቱት በኢትዮጵያ መንግስት ጥይት ነው’ አርዱፍ

Ethiopia Zare (ረቡዕ ጥር 14 ቀን 2004 ዓ.ም. January 23, 2011)፦ ባለፈው ሳምንት ለ5 ጎብኝዎች ሞት ምክንያት ለሆነው እና ለ27 ጎብኝዎች ላይ ለተቃጣው ጥቃት በህወሀት መራሹ የኢትዮጵያ ወታደሮችና በአፋር አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት ግንባር (አርዱፍ) መሀከል በተነሳ ጦርነት መሆኑንና ታጋቾቹ ሁለት ጀርመናዊያን በእጁ እንደሚገኙ አርዱፍ አስታወቀ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከጓድ መንግስቱ ኃይለማርያም ‹‹ትግላችን›› ጋር…

ተመስገን ደሳለኝ

ማን ይፈራል ሞት

ማን ይፈራል

ለእናት ሀገር ሲባል..

የጊዜው ወታደራዊ ደርግ አስተዳደር፣ የአብዮታዊ ጦር ሰራዊት ጠቅላይ አዛዥ፣ የኢትዮጵያ ሰራተኞች ፓርቲ ዋና ፀሀፊ፣ የኢህዴሪ ሊቀመንበር፣ የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት… ጓድ መንግስቱ ኃ/ማርያም ሰሞኑን በስደት ከሚኖሩበት ዙምባቤ ‹‹ትግላችን›› የተሰኘ መጽሐፍ አሳትመው በ39 የአሜሪካ ዶላር እየቸበቸቡ ነው። በእርግጥ ሀገር ከመሸጥ መጽሐፍ መሸጥ የተሻለ ነበር። ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ