በአፋር ክልል የተገደሉት ጎብኝዎች ዜግነት ታወቀ
4 ሰዎች ታግተዋል፣ ሁለት ቆስለዋል
Ethiopia Zare (ረቡዕ ጥር 9 ቀን 2004 ዓ.ም. January 18, 2011)፦ ትላንት ማክሰኞ ከጠዋቱ 5 ሰዓት ላይ በአፋር ክልል ያልታወቁ ታጣቂዎች በወሰዱት ርምጃ የተገደሉት አምስት ጎብኝዎች ዜግነት መረጋገጡ እና አራት ሰዎች መታገታቸው ታወቀ። ሙሉውን አስነብበኝ ...4 ሰዎች ታግተዋል፣ ሁለት ቆስለዋል
Ethiopia Zare (ረቡዕ ጥር 9 ቀን 2004 ዓ.ም. January 18, 2011)፦ ትላንት ማክሰኞ ከጠዋቱ 5 ሰዓት ላይ በአፋር ክልል ያልታወቁ ታጣቂዎች በወሰዱት ርምጃ የተገደሉት አምስት ጎብኝዎች ዜግነት መረጋገጡ እና አራት ሰዎች መታገታቸው ታወቀ። ሙሉውን አስነብበኝ ...አስገድዶ መድፈርና ከፍተኛ የመብት ረገጣ ተፈጽሞባቸዋል
Ethiopia Zare (ረቡዕ ጥር 9 ቀን 2004 ዓ.ም. January 18, 2011)፦ በኢትዮጵያ ለም የሆኑ የእርሻ መሬቶችን ለኢንቨስትመንት ለመስጠት መንግስት በያዘው ፕሮግራም ሳቢያ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ከሚኖሩባቸው አካባቢዎች በግዳጅ እየተነሱ ለኑሮ ተስማሚ ወዳልሆኑ ቦታዎች መወሰዳቸውን ሂዩማን ራይትስ ወች አጋልጧል። ሙሉውን አስነብበኝ ...አቶ በረከት ኤርትራን ተጠያቂ አድርገዋል
ሁለት ጀርመናዊያን ተጠልፈዋል
Ethiopia Zare (ማክሰኞ ጥር 8 ቀን 2004 ዓ.ም. January 17, 2012)፦ ባለፈው ሰኞ ማምሻው ላይ በአፋር ክልል ይንቀሳቀሱ በነበሩ የጎብኝዎች ቡድን ላይ ማንነታቸው ያልተረጋገጠ ታጣቂዎች በወሰዱት እርምጃ ቢያንስ 5 ሰዎች መሞታቸውና ሁለት ሌሎች ቱሪስቶች ደግሞ ከባድ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸው በህክምና ላይ እንደሚገኙ ተገለጸ። ሙሉውን አስነብበኝ ...አዲሱ ፌዴሬሽን (ESFNA-ONE) ተብሏል
አቶ አብነት የስፖርት ክለቦችን ለመደለል ገንዘብ መበተን ጀምሯል
Ethiopia Zare (ሐሙስ ጥር 3 ቀን 2004 ዓ.ም. January 12, 2011)፦ የኢትዮጵያዊያን በሰሜን አሜሪካ ስፖረት ፌደሬሽን የሚያካሂደው አመታዊ የስፖርት ውድድር አመታዊ ዝግጅቱን በዳላስ ቴክሳስ እንደሚያካሂድ ይፋ ማድረጉ የሚታወቅ ሲሆን በሼህ መሀመድ አላሙዲ ወዳጅ አቶ አብነት የሚመራ አዲስ ፌደሬሽን ተቋቁሞ ሌላ የስፖርት ውድድር በዋሽንግተን ዲሲ ለማካሄድ በዝግጅት ላይ መሆኑ ታወቀ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...በሔኖክ ሰማእግዜር ፈንቴ
የተማሪዎቹ ጥያቄዎች የተለያዩ መልክ ያላቸው ናቸው። ዛሬ ማምሻውን አዲስ አበባ ከተማ የትምህርት ነጻነታችንን የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ተጋፍቶናል ሲሉ በመቶዎች የተቆጠሩ የአወሊያ የመለስተኛ፣ ሁለተኛ ደረጃና ኮሌጅ ተማሪዎች ድምጻቸውን በማሰማት ላይ ናቸው።
ጥያቄዎቻችን ካልተመለሱ ወደቤታችን አንሄድም በሚል በትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ ዛሬ ሊያድሩ የወሰኑት ተማሪዎች፤ ቁጥራቸው ከ600 በላይ እንደሆነ ይናገራሉ። ለአንድ ሳምንትም ትምህርት ተቋርጧል።
“ምንም አይነት ችግር ሳይፈጠር ኮሌጁን የእልምና ጉዳዮች ዘግቶብናል፣ የኮሌጁ መምህራንና ዲኖች ከስራ ተሰናብተዋል፣ እንዲሁም የአወሊያ መስጊድ ኢማም የሆኑት ሼክ ይማም ተባረዋል” ስትል አንዲት ስሟ እንዳይጠቀስ የፈለገች የአረቢኛ ቋንቋ የኮሊጅ ተማሪ ገልጻለች።
የጸጥታ ሃይሎች የትምህርት ቤቱን ግቢ ከበዋል፤ እስካሁን ሰልፉን ለመበተን ከማስፈራራት በስተቀር በተማሪዎቹ ላይ የደረሰባቸው ጥቃት የለም።
በወለጋ ዩኒቨርስቲ ደግሞ ተማሪዎች የምግብ ጥራት መጓደል አሳስቧቸዋል፤ አልፎም ለተቃውሞ አድርሷቸዋል።
ከለት ወደለት የደፈረሰ የጎርፍ ውሃ የመሰለ ሽሮ መብላት ታከተን፤ በአግባቡ ያልተበጠረና አሸዋ ያለበት እንጀራ መብላት እስከመቼ? የሚመደብልን በጀት በቂ ሆኖ ሳለ፤ የምግብ ጥራት ማሽቆልቆሉ ለምን? እያሉ ውስጥ ውስጡን ሲያጉተመትሙ የነበሩት የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች፤ የገና ለት ነው አንጀታቸው ለይቶለት የተቆረጠው።
ከቤተሰባቸው ተለይተው በዓሉን የሚያከብሩት ተማሪዎች እልቅ ቅጠል የማይል ምግብ ቀረበልን ሲሉ፤ ምግብ ላለምብላት ይወስኑና፤ በምግብ ቤቱ ዙሪያ ይሰባሰባሉ።
ተማሪዎቹ የምግብ ጥራት እንዲሻሻል ሲጠይቁ የመጀመሪያቸው አልነበረም። ወዲያውኑ የጸጥታ ሃይሎች በአካባቢው ተገኝተው ተማሪዎቹ ጋር ግብ ግብ ይገጥማሉ። የታጠቁ ሃሎች በከፈቱት ተኩስ አንድ ተማሪ መቁሰሉንና ሌሎች ደግሞ መደብደባቸውን ተማሪዎቹ ይናገራሉ።
ጥቃት ከደረሰባቸው አንዱ በአሁኑ ወቅት የቀዶ ጥገና ህክምና ተደርጎለት በነቀምት ሆስቲታል ውስጥ ይገኛል። የፌዴራልና የኦሮሚያ ፖሊስ በአካባቢው ተገኝተው በወሰዷቸው እርምጃዎች ድብደባ ደርሶባቸው በሆስፖታል የሚገኙ ተማሪዎች እንዳሉም ተገልጿል።
የሶስተኛ አመት ተማሪ ተስፋየ ደገፋ በአካዳሚክ ፕሬዝደንቱ ዶር ኤባ ሚጀና ስለተደበደብ ለህይወቱ አስጊ ሁኔታ ላይ እንደሚገን ተማሪዎቹ ለኦሮሚኛ ዝግጅት ክፍላችን ገልጸዋል።
የተማሪው የጤና ሁኔታ አስጊ በመሆኑ ለተጨማሪ የህክምና እርዳታ ወደ አዲስ አበባ ከአቅም በላይ ተብሎ ሊላክ እንደታሰበ ተማሪዎቹ ይናገራሉ። በወለጋ ዩኒቨርስቲ የትምህርት ሂደቱ በከፊል ቀጥሏል። የዩኒቨርስቲውን ፕሬዝደንት ፕሮፌሰር ፈቃዱ በየነ የዝግጅት ክፍላችን በተደጋጋሚ ደውሎላቸው ስልካቸውን አያነሱም።
የምስራቅ ወለጋ የፖሊስ ኮሚሽነር ኢንስፔክተር ኦላና ጌታቸው የተጎዱ የሚባሉት ተማሪዎች ማን እንደደበደባቸውና ጥቃቱን እያደረሰባቸው እንደሆነ አልታወቀም ብለዋል። እስካሁን የታሰሩ ተማሪዎች አለመኖራቸውን ነው ኢንስፔክተር ኦላና የገልጹት።
በደቡብ ክልል ሃዲያ ዞን ደግሞ፤ በሆሳእና ከተማና አካባቢዋ የሚገኙ ከ429 በላይ ተማሪዎች ትምህርታችንን አጠናቀን ስራ አጥተናል በሚል የዞኑ መስተዳድር የስራ እድል እንዲከፍትላቸው ጠይቀዋል።
ተማሪዎቹ ተወካዮች መርጠው ከመስተዳድሩ ጋር ለረጅም ጊዜ ሲደራደሩና ሁኔታውን ሲከታተሉ መቆየታቸውን ነው የሚናገሩት። በስተመጨረሻ ተወካዮቻቸው ከዞኑ መስተዳድር ጋር ለመነጋገር ገብተው ባለመመለሳቸው ተቃውሞው መባባሱን አንድ ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀ ተማሪ ገልጾልናል።
የሃዲያ ዞን የፖሲስ አዛዥ ኮማንደር አዲሴ ፈይሳ ግጭቱ መፈጠሩን ገልጸው፤ ከታሰሩ ተማሪዎች መካከል ሁሉም ትምህርት ተሰጥቷቸው መፈታታቸውን ተናግረዋል።
“በኦነግ ውስጥ የተፈጠረው ችግር ምክንያት የጠራ ራእይ ማጣት ነበር” የኦነግ ከፍተኛ አመራር
Ethiopia Zare (ሐሙስ ታህሳስ 26 ቀን 2004 ዓ.ም. January 5, 2011)፦ በፈረንጆችቹ አዲስ አመት መግቢያ የኦሮሞ ተወላጆች በብዛት ይኖሩባታል በምትባለው ሜኔሶታ ክፍለ ከተማ በተጠራ ህዝባዊ ስብሰባ ላይ ይፋ የሆነውና ኦነግ (የኦሮሞ ነጻነት ግንባር) ከተመሰረተበት ከ1960 እኤአ ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያን አንድነት የተቀበለበትን መግለጫ ካወጣ ጀምሮ የተለያዩ አስተያየቶች በመሰማት ላይ ናቸው።
ሙሉውን አስነብበኝ ...በዋሽንግተን ዲሲ ወርሀዊ የሻማ መብራት ስነስርአት ተካሄደ!
Ethiopia Zare (ሰኞ ታህሳስ 23 ቀን 2004 ዓ.ም. January 2, 2011)፦ በ”ማርች ፎር ፍሪደም”ና በሌሎች የሰብአዊ መብት ድርጅቶች አስተባባሪነት በየወሩ በአሜሪካን ፕሬዚዳንት መኖሪያ ፊት ለፊት የሚካሄደውና በኢትዮጵያ የታሰሩ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞችን የሚያስበው የሻማ ማብራት ስነስርአት በሞቀ ሁኔታ ተካሄደ። ሙሉውን አስነብበኝ ...