“ምን መሥራት እንዳለብኝ አልወሰንኩም” ዶ/ር ፍስኃ እሸቱ

Dr. Fisseha EshetuEthiopia Zare (እሁድ ኅዳር 21 ቀን 2001 ዓ.ም. November 30, 2008)፦ በቅርቡ የሙሉ ዩኒቨርሲትነት እውቅና ያገኘው የ”ዩኒቲ ዩኒቨርስቲ” የቀድሞ ባለቤትና ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፍስኃ እሸቱ፣ ሙሉ ንብረታቸውን በሽያጭ ለሼህ መሐመድ አሊ አል አሙዲና ለዶ/ር አረጋ ካስረከቡ በኋላ፣ በቀጣይ ስለሚሠማሩበት የሥራ ዘርፍ ምንም እንዳላሰቡ ገለፁ። በቅርብ የሚያውቋቸው ምንጮች እንደጠቆሙት ላልተወሰነ ጊዜ ከኢትዮጵያ ውጭ ቆይታ እንደሚያደርጉ ነው። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአቃቂ ወንዝ ብክለት

በማግነስ ፍራንክሊን

ሰዎች በአንድ አካባቢ መሥፈር የጀመሩት የወንዝ ተፋሰሶችን ተከትለው ነው። በዋነኝነትም ወንዞች ለሠፈራ ቁልፍ ሚና ነበራቸው፤ ነገር ግን ከንግድ ተቋማት ጋር ሲተሳሰሩ ምን ይፈጠራል? ሙሉውን አስነብበኝ ...

በአዲስ አበባ የድህነት ደረጃ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ይመራል

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ኅዳር 20 ቀን 2001 ዓ.ም. November 29, 2008)፦ በአዲስ አበባ ከሚገኙ 10 ክፍለ ከተሞች መካከል በድህነት ደረጃ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 13/14 እንደሚመራ አንድ ጥናት አመለከተ። አራዳ፣ አዲስ ከተማና ልደታ ክፍለ ከተሞችም የተጨናነቀ የህዝብ ብዛትና ከፍተኛ የገቢ ማነስ የሚታይባቸው ክፍለ ከተሞች መሆናቸው ተገልጧል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

በታላቁ ሩጫ «ኹከት ፈጥረዋል» የተባሉ ታስረው ተፈቱ

46 ሰዎች ታስረው 19ኙ ፍርድ ቤት ቀርበዋል

የቴዲ አፍሮን ምስል የያዘ ቲሸርት በመልበሳቸው የተያዙ ይገኙበታል

ድብዳባ እንደተፈጸመባቸው ገልጸዋል

Ethiopia Zare (ዓርብ ኅዳር 19 ቀን 2001 ዓ.ም. November 28, 2008)፦ በአዲስ አበባ ለስምንተኛ ጊዜ በተካሄደው ታላቁ ሩጫ ላይ በተሣታፊዎች መካከል የታዋቂውን አርቲስት ቴዎድሮስ ካሣሁንን (ቴዲ አፍሮን) ምስል የያዙ ቲሸርት የለበሱና፣ የቴዲ አፍሮን መፈታት የሚጠይቅ መፈክሮችን ያሰሙ ወጣቶች ለሁለት ቀናት ታስረው በዋስ መለቀቃቸውን ገለፁ። ያነጋገርናቸው ወጣቶች ድብደባ እንደደረሰባቸው ገልፀዋል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

አንድነት በራሪ ወረቀት እንዳያሣትም መከልከሉን ገለጸ

Ethiopia Zare (ዓርብ ኅዳር 19 ቀን 2001 ዓ.ም. November 28, 2008)፦ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በራሪ ወረቀቶችን ለማሣተም ገንዘብ ከፍሎ ውጤቱን ሲጠባበቅ ማተሚያ ቤቱ ጽሑፉን ማተም ስለማይችል፤ ገንዘቡን እንዲወስድ መጠየቁን አስታወቀ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኦባማ ከአልቃይዳ ማስጠንቀቂያ ደረሳቸው

Barack ObamaEthiopia Zare (ቅዳሜ ኅዳር 13 ቀን 2001 ዓ.ም. November 22, 2008)፦ ባራክ ኦባማ አሜሪካ በኢራቅ ያላትን ጦር አስወጥተው ትኩረታቸውን ወደ አፍጋኒስታን የሚያደርጉ ከሆነ ወንጀለኛ በሚሏቸው አሜሪካኖች ላይ ጥቃታቸውን እንደሚቀጥሉ የአልቃይዳ ምክትል መሪ አልዛዋሂር አስታውቀዋል።  ሙሉውን አስነብበኝ ...