የከተማ ድሆች ሁኔታ
በቅርቡ ጥናት ያደረጉ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፣ በአዲስ አበባና በሌሎች የሀገሪቱ ዋና ዋና ከተሞች ድህነት መባባሱን ነው። በተለይም በመዲናዋ አዲስ አበባ የድህነት ገጽታው በከፍተኛ ፍጥነት ማሻቀቡን ከሚታየውና ከሚሰማው ነገር መረዳት ይቻላል። ሙሉውን አስነብበኝ ...
በቅርቡ ጥናት ያደረጉ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፣ በአዲስ አበባና በሌሎች የሀገሪቱ ዋና ዋና ከተሞች ድህነት መባባሱን ነው። በተለይም በመዲናዋ አዲስ አበባ የድህነት ገጽታው በከፍተኛ ፍጥነት ማሻቀቡን ከሚታየውና ከሚሰማው ነገር መረዳት ይቻላል። ሙሉውን አስነብበኝ ...
”በወያኔ ምርጫ ማናቸውም ተቀዋሚዎች መሳተፍ የለባቸውም” አቶ አዛለ ደስታ
”ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ምርጫ መገባት አለበት" ተክለሚካኤል አበበ
Ethiopia Zare (ማክሰኞ ኅዳር 30 ቀን 2001 ዓ.ም. December 9, 2008)፦ በመጪው 2002 ዓ.ም. (2010 እ.ኤ.አ.) ምርጫ በሀገር ቤት የሚገኙ የተቃዋሚ ኃይሎች ምን ማድረግ ይገባቸዋል ከሚል ሃሳብ በመነሳት የመጀመሪያው ህዝባዊ ስብሰባ በቫንኩቨር ካናዳ ቅዳሜ ዲሴምበር 13 ቀን 2008 እ.ኤ.አ. እንደሚካሄድ ተለጸ። ሙሉውን አስነብበኝ ...
"ስብሰባው የተሳካ ነበር" ወ/ት ብርቱካን
ዶ/ር ነጋሶ፣ አቶ ስዬ፣ ፕ/ር በየነ፣ ... ተገኝተዋል

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ኅዳር 27 ቀን 2001 ዓ.ም. December 6, 2008)፦ አብዛኛውን የቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ፓርቲ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በመያዝ ስያሜውን አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ በማለት ሕጋዊ እውቅና አግኝቶ የሚንቀሳቀሰው አንድነት ፓርቲ ዛሬ የመጀመሪያውን ህዝባዊ ስብሰባ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ። በስብሰባው ላይ የቀድሞው የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፣ አቶ ስዬ አብርሃ፣ ፕ/ር በየነ ጴጥሮስና ሌሎችም ተገኝተዋል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ዝርዝር ዘገባ የታከለበት
(የፍርድ ውሳኔውን ሙሉ ቃል ይዘናል)
በተጨማሪም የ18 ሺህ ብር ቅጣት ተፈረደበት
“በይግባኝ ወይንም ‘በሽምግልና’ ሊፈታ ይችላል” ታዛቢዎች
Ethiopia Zare (ዓርብ ኅዳር 26 ቀን 2001 ዓ.ም. December 05, 2008)፦ ዝነኛው ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ዛሬ በዋለው ችሎት ስድስት ዓመት እስራትና 18 ሺህ ብር ቅጣት ተፈረደበት።
የአማራ ክልልና አዲስ አበባ ህዝብ ብዛት አከራካሪ ሆኗል
Ethiopia Zare (ዓርብ ኅዳር 26 ቀን 2001 ዓ.ም. December 05, 2008)፦ የኢፌዲሪ የህዝብ ቆጠራ ኮሚሽን የ1999/2000 ዓ.ም. የኢትዮጵያ የህዝብ ቆጠራ የመጀመሪያ ደረጃ ውጤት 73 ሚሊዮን 918 ሺህ 505 መድረሱን አስታወቀ። የአማራ ክልልና አዲስ አበባ ህዝብ ብዛት አከራካሪ ሆኗል። ሙሉውን አስነብበኝ ...
Ethiopia Zare (ዓርብ ኅዳር 26 ቀን 2001 ዓ.ም. December 05, 2008)፦ በሚኒስትሮች ሹም ሽር የጀመረው የፌደራል ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች የሥልጣን ሽግግር ወደ ሚኒስትር ዴኤታዎችም እየተጓዘ ነው።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
Ethiopia Zare (ዓርብ ኅዳር 26 ቀን 2001 ዓ.ም. December 05, 2008)፦ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ፣ በሶማሊያ ያለውን የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሚተካ ጦር እስከሚያዘጋጅ ድረስ፣ ኢትዮጵያ ጦሯን በሶማሊያ ለማቆየት መስማማቷን አንድ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለሥልጣን ገለፁ። ሙሉውን አስነብበኝ ...
Ethiopia Zare (ሰኞ ኅዳር 22 ቀን 2001 ዓ.ም. December 01, 2008)፦ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ባለፈው ኀሙስ እና ዓርብ በአዲስ አበባ ከተማ ሲቀሰቅስበት የነበረው አይሱዙ መኪና ታሰረ። ሙሉውን አስነብበኝ ...
ለቅጣት ውሳኔ የፊታችን ዓርብ ተቀጠረ

Ethiopia Zare (ሰኞ ኅዳር 22 ቀን 2001 ዓ.ም. December 01, 2008)፦ ለስምንት ወራት ሰው በመኪና ገጭቶ በማምለጥ ወንጀል ተከሶ በእስር ላይ የሚገኘው አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን፣ ዛሬ ኅዳር 22 ቀን በመጥፎነቱ በሚታወቀው የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት ጥፋተኝ ተብሎ እንደተወሰነበት ችሎቱን የተከታተሉ የአዲስ አበባ ምንጮቻችን አስረዱ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ደራሲና ባለቅኔ ኃይሉ ገ/ዮሐንስ የክብር እንግዳ ሆነው የኖታ ጨዋታ ናሙና ላጠኑ ምስክር ወረቀት ሰጡ

Ethiopia Zare (እሁድ ኅዳር 21 ቀን 2001 ዓ.ም. November 30, 2008)፦ ከስምንት ወራት በፊት በስዊድን ዋና ከተማ በስቶክሆልም የተቋቋመው ”የኢትዮጵያ መዚቃና ድራማ ቡድን” (EMDG) ቅዳሜ ኅዳር 20 ቀን 2001 ዓ.ም. (November 29, 2008) ሥልጠናውን በሚሰጥበት አዳራሽ ውስጥ ለተሰበሰቡት እንግዶች የሙዚቃ ናሙና አሳይቷል። ሠልጣኞቹ ከክብር እንግዳው የምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል። ሙሉውን አስነብበኝ ...