አንድነት ወደ አውሮፓ ነገ ይጓዛል

ወ/ት ብርቱካንና አቶ አክሉ ነገ ወደ ሎንዶን ይገባሉ

Ethiopia Zare (ኀሙስ ጥቅምት 27 ቀን 2001 ዓ.ም. November 6, 2008)፦ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሁለት አመራሮቹን ነገ ወደ አውሮፓ ይሸኛል። አመራሮቹ በአውሮፓ ሰባት ሀገሮች ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን፣ የየሀገሮቹ ባለሥልጣናትና ከአውሮፓ ሕብረት ባለሥልኖች ጋር ለመወያየት ማቀዱን ለመረዳት ችለናል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በኬንያ ኀሙስ ቀን ብሔራዊ በዓል እንዲሆን ታወጀ

በኦባማ መመረጥ ከተሞች በደስታ በተሞሉ ነዋሪዎች ተጨናንቀዋል

Ethiopia Zare (ኀሙስ ጥቅምት 27 ቀን 2001 ዓ.ም. November 6, 2008)፦ የኬንያው መሪ ምዋይ ኪባኪ በአባቱ ኬንያዊ የሆነውን ባራክ ኦባማን ለአሜሪካ ፕሬዝዳንትነት መመረጥ አስመልክተው ኀሙስ ኖቨምበር 6 ቀን በሀገሪቱ የበዓል ቀን ሆኖ እንዲውል መልዕክት አስተላለፉ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ፕሬዝዳንት ባራክ ሁሴን ኦባማ

የአሜሪካ ህዝብ ታሪክ ሠራ

Presidant Barack Hussein Obama

Ethiopia Zare (ረቡዕ ጥቅምት 26 ቀን 2001 ዓ.ም. November 5, 2008)፦ የዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ህዝብ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቁር ፕሬዝዳንት መረጠ። ሴናተር ባራክ ኦባማ 44ኛው የአሜሪካን ፕሬዝዳንት ሆኖ ተመረጠ። የ2008 ምርጫ ታሪካዊ ምርጫ ሆነ።  ኋይት ሐውስ የመጀመሪያዋን ጥቁር ቀዳማዊ እመቤት አገኘች።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ወደ ኢትዮጵያ የሚተላለፍ ራዲዮ ዛሬ ይጀመራል

መጠሪያው ”የኢትዮጵያ አደራ ድምፅ ራዲዮ” ተብሏል

በማትያስ ከተማ

Ethiopia Zare (ረቡዕ ጥቅምት 26 ቀን 2001 ዓ.ም. November 5, 2008)፦ "የኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች መነጋገሪያ መድረክ" (Ethiopian Current Affairs Discussion Fourm) የሚባለው የፓልቶክ መድረክ አባላት ለኢትዮጵያና ለአካባቢው ሀገሮች በቀጥታ የሚተላለፍ ራዲዮ ለማስተላልፍ ዝግጅት መጨረሳቸውን አሳወቁ። ራዲዮው ሥርጭቱን ዛሬ ይጀምራል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የዳኛ አባት ስም መሳሳት 2000 ብር አስቀጣ

ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ ቅጣቱን ከፍላ ተለቀቀች

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ጥቅምት 25 ቀን 2001 ዓ.ም. November 4, 2008)፦ የእንቢልታ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ የቴዲ አፍሮን ጉዳይ የሚያስችሉትን ዳኛ የአባት ስም በመሳሳትዋ በፍትህ ሚኒስቴር በተመሰረተባት ክስ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 14ኛ ወንጀል ችሎት በዛሬው ዕለት የ2000 ብር ቅጣት ወስኖባታል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ቴዲ አፍሮ ለ28 ቀናት በእስር ይቆያል

"መዝገቡን መርምረን አልጨረስንም" ዳኛ ልዑል

ለኅዳር 22 ተቀጠረ

ነፃ የወጣበት የስዕል ክስ ተሸሮ ይከላከል ተባለ

Teddy Afro

Ethiopia Zare (ሰኞ ጥቅምት 24 ቀን 2001 ዓ.ም. November 3, 2008)፦ ልደታ በሚገኘው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቴዲ አፍሮ ችሎት በሚታይባቸው ቀናት የፍርድ ቤቱ ቅጽር ግቢም ሆነ ውጪው ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ከፍተኛ ጥበቃ ይደረግባቸዋል። በህዝብም ይጨናነቃሉ። ዛሬም አካባቢው ከፍተኛ ውጥረት ይታይበት ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የዳኛ አባት ስም የተሳሳተችው ጋዜጠኛ ጥፋተኛ ተባለች

Tsion Girma, journalist
ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ

ለቅጣት ውሳኔ ነገ ተቀጠረች

5ኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስራ እንድታድር ተደረገ

Ethiopia Zare (ሰኞ ጥቅምት 24 ቀን 2001 ዓ.ም. November 3, 2008)፦ የቴዲ አፍሮን ችሎት እንዲዳኙ ተመድበው የነበሩትን ዳኛ የአባት ስም በመሳሳትዋ ተከስሳና ታስራ የነበረችው ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ ዛሬ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 14ኛ ወንጀል ችሎት ለአራተኛ ጊዜ ቀርባ ጥፋተኛ የተባለች ሲሆን፤ የቅጣት ውሳኔ እስኪሰጣት በእስር እንድትቆይ ተደረገ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሆመር ሲምፕሰን ኦባማን መረጠ

Homer Simpson & Obama, APየማኬይን ደጋፊዎች ”ዘ ሲምፕሰንስ”ን ተቹ

Ethiopia Zare (እሁድ ጥቅምት 23 ቀን 2001 ዓ.ም. November 2, 2008)፦ በዓለም ላይ ካሉት ታዋቂ የቴሌቭዥን ተከታታይ ፊልሞች ውስጥ ”ዘ ሲምፕሰንስ” የተሰኘው የካርቱን ፊልም ላይ ያለው ዋና ገፀ-ባህሪ ሆመር ሲምፕሶን በእሁዱ ትዕይንት ለባራክ ኦባማ ድጋፉን በመስጠቱ ከጆን ማኬይን ደጋፊዎች ከፍተኛ ተቃውሞና ትችት ደረሰበት።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ቴሌ አዳዲስ አገልግሎቶች ሊጀምር ነው

የሞባይል ካርድ ከ25 ብር በታች ይቀርባል

Ethiopia Zare (እሁድ ጥቅምት 23 ቀን 2001 ዓ.ም. November 2, 2008)፦ የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን፣ በተያዘው በጀት ዓመት (2001 ዓ.ም.) የተለያዩ አዳዲስ አገልግሎቶችን ለደንበኞቹ ለማቅረብ በዝግጅት ላይ መሆኑን አስታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዳሸን ባንክ 239.1 ሚሊዮን ብር አተረፈ

በ2000 ዓ.ም የጀት ዓመት 93.5 ሚሊዮን ብር ለመንግሥት ቀረጥ ከፍሏል

Ethiopia Zare (እሁድ ጥቅምት 23 ቀን 2001 ዓ.ም. November 2, 2008)፦ በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ የግል ባንኮች አንዱ የሆነው ዳሽን ባንክ፣ ባለፈው በጀት ዓመት (2000 ዓ.ም.) 239 ነጥብ አንድ ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ አገኘ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...