የዓለም የገንዘብ ቀውስ - ለአፍሪካ ሥጋት

የአፍሪካ የገንዘብ ሚኒስትሮች መፍትሔ ፍለጋ ሊወያዩ ነው

Ethiopia Zare (እሁድ ጥቅምት 23 ቀን 2001 ዓ.ም. November 2, 2008)፦ የዓለም የገንዘብ ቀውስ በአፍሪካ ልማትና ዕርዳታ ላይ ተጽኖ በማሳደሩ፣ የአፍሪካ ሀገሮች የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትሮች ስብሰባ ሊያደርጉ መሆኑን የአፍሪካ ሕብረት የኢኮኖሚ ጉዳዮች ኮሚሽነር አስታወቁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

እነኢንጂንየር ግዛቸው ታስረው ተፈቱ

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ጥቅምት 22 ቀን 2001 ዓ.ም. November 1, 2008)፦ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በአማራ ክልል ጎጃም የፓርቲውን ጽሕፈት ቤቶች ለመክፈት የተጓዙት ኢንጂንየር ግዛቸው ሽፈራውና የፓርላማ አባል የሆኑት አቶ አዕምሮ አወቀ እና አቶ ልባዊ አበበ ልዩ ስሟ ደንበጫ በተባለች ከተማ ውስጥ ዛሬ ለሦስት ሰዓታት ታስረው ተፈቱ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጋዜጠኛ አማረ ራሱን ከሳተበት ነቃ

Amare Aregawi, journalistየመግደል ሙከራውን የፈፀሙት ቅጥር ነፍሰገዳዮች እንደሆኑ ይጠረጠራል

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ጥቅምት 22 ቀን 2001 ዓ.ም. November 1, 2008)፦ በትናንትናው ዕለት በሀገር ውስጥ የሚታተመው የአማርኛው ”ሪፖርተር” እና የእግሊዝኛው ”The Reporter” ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ፣ ባለቤትና አሣታሚ ጋዜጠኛ አማረ አረጋዊ ላይ የመግድል ሙከራ ያደረጉበት ሦስት ግለሰቦች ቅጥር ነፍሰ ገዳዮች እንደሆኑ ተጠርጥራል። እስከዛሬ ማምሻውን ከፍተኛ ጥበቃ እየተደረገለት በሕክምና ላይ እንደሚገኝና ራሱን ስቶ ከነበረበት መንቃቱን የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች ገለጡ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአዲስ አበባ ሴቶች ማኅበር መሪ በግምገማ ተነሱ

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ጥቅምት 22 ቀን 2001 ዓ.ም. November 1, 2008)፦ በሕግ ባለሙያዎቹ አቶ ዳንኤል በቀለና አቶ ነፃነት ደምሴ ላይ የሐሰት ምስክር አዘጋጅተው ያቀረቡት፣ በምርጫ 97 ኢህአዴግን ወክለው የተወዳደሩትና የአዲስ አበባ ሴቶች ማኅበር መሪ የሆኑት ወ/ሮ ጥጉ ወልደሰንበት በግምገማ ከሥልጣናቸው ተነሱ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በመቱ ሁለት የአንድነት ፓርቲ አስተባባሪዎች ታሰሩ

Ethiopia Zare (ዓርብ ጥቅምት 21 ቀን 2001 ዓ.ም. October 31, 2008) አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ጽ/ቤቶችን ለመክፈት በተንቀሳቀሰባቸው የክፍለ ሀገራት ከተሞች ችግሮች እያጋጠሙት መሆኑ ተገለጸ። በመቱ ከተማ ሁለት አስተባባሪዎች ህዝብን አነሳስታችኋል በሚል መታሰራቸውን የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች ከአዲስ አበባ አስታወቁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የቴዲ አፍሮ ጉዳይ በቀድሞው ዳኛ እጅ ገባ

Teddy Afroዳኛ መሐመድ ዑመር ተነስተው የቀድሞው ዳኛ ልዑል ገ/ማሪያም ተተኩ

  ቴዲ አፍሮ የፊታችን ሰኞ ውሳኔ ላያገኝ ይችላል

Ethiopia Zare (ኀሙስ ጥቅምት 20 ቀን 2001 ዓ.ም. October 30, 2008)፦ የዝነኛውን የአርቲስት ቴድሮስ ካሳሁንን (ቴዲ አፍሮን) ችሎት ሲያዩ የነበሩት የቀድሞው ዳኛ ልዑል ገ/ማሪያም ከዚህ በኋላ የሚኖሩትን የቴዲን ችሎቶች በዳኝነት እንደሚመሩ የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች ገለጹ። ያለፉትን ሁለት ችሎቶች ብቻ ሲያስችሉ የነበሩት ዳኛ መሐመድ ዑመር ከትናንት ጥቅምት 19 ጀምሮ የቴዲ አፍሮ ጉዳይ ከሚታይበት ችሎት ተነስተዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጠ/ሚ/ር መለስ ሹም ሽር አካሄዱ

PM Meles Zenawiአምስት ሚኒስትሮች ከሥልጣን ተነሱ፣ 3ቱ ተቀያየሩ

ማስታወቂያ ሚኒስቴርን አፈረሱት

Ethiopia Zare (ኀሙስ ጥቅምት 20 ቀን 2001 ዓ.ም. October 30, 2008)፦ ጠቅላይ ሚ/ር መለስ ዜናዊ በዛሬው ዕለት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 9 ሚኒስትሮችን የሾሙ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ 5ቱን ከሥልጣናቸው ሲያነሷቸው፣ ሦስቱን ደግሞ ቦታ አቀያይረዋቸዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...