ቴዲ አፍሮ በሁለተኛው ክስ የመከላከያ ማስረጃዎቹን እንዲያቀርብ ታዘዘ

ከ11 ቀናት በኋላ ፍርድ ቤት ይቀርባል

Ethiopia Zare (ዓርብ ኅዳር 5 ቀን 2001 ዓ.ም. November 14, 2008)፦ አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ”ነፃ” በተባለበት ሁለተኛው ክስ እንዲከላከል በይግባኝ የተወሰነ በመሆኑ ማክሰኞ ኅዳር 16 ቀን የመከላከያ ማስረጃዎቹን ይዞ እንዲቀርብ ትዕዛዝ ተሰጠ። የኤሌክትራ ሙዚቃ ቤት ባለቤት አቶ ተሾመ ፀጋዬም ይቅረቡ ተብሏል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአንድነት ፓርቲ ልዑካን ስዊድን ገቡ

የፊታችን ቅዳሜ በስዊድን ህዝባዊ ውይይት ያካሂዳሉ

UDJP deligates arrival, Stockholm

Ethiopia Zare (ኀሙስ ኅዳር 4 ቀን 2001 ዓ.ም. November 13, 2008)፦ አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲን በመወከል በአውሮፓ ሰባት ሀገሮች ለሥራ የመጡት ሊቀመንበሯ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ እና አቶ አክሉ ግርግሬ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ከቀኑ በ8 ሰዓት ስዊድን ዋና ከተማ ስቶክሆልም ገቡ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ የህዝብ ግንኙነቱን ቀየረ

Ethiopia Zare (ኀሙስ ኅዳር 4 ቀን 2001 ዓ.ም. November 13, 2008)፦ የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ የህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ተጠሪ የነበሩት አቶ ዳንኤል ጎበዜ ከኅዳር 2 ቀን 2001 ዓ.ም. ጀምሮ በገዛ ፈቃዳቸው ኃላፊነታቸውን መልቀቃቸውንና በምትካቸው አቶ ሊቁ እጅጉ በጊዜያዊነት የተኳቸው መሆኑን ኮሚቴው ለኢትዮጵያ ዛሬ በላከው መግለጫ አስታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአውራምባ ታይምስ አዘጋጆች የክስ ደብዳቤ ደረሳቸው

Ethiopia Zare (ረቡዕ ኅዳር 3 ቀን 2001 ዓ.ም. November 12, 2008)፦”አውራምባ ታይምስ” የተሰኘው በሀገር ውስጥ የሚታተመው ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ እና ምክትል ዋና አዘጋጁ ጋዜጠኛ ወንድይራድ ደብረጽዮን የዓቃቤ ሕግ የክስ ደብዳቤ የደረሳቸው ሲሆን፣ ፍርድ ቤት ለኅዳር 17 እንዲቀርቡም ጥሪ ደርሷቸዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ማሪያ ማኬባ (ማማ አፍሪካ) አረፈች

እሁድ ጥቅምት 30 ካስቴልቮልቱርኖ መድረክ ላይ ራስዋን ከመሳትዋ በፊት(ፎቶ AP)

Maria Makeba, died 76

Ethiopia Zare (ኅዳር 1 ቀን 2001 ዓ.ም. November 10, 2008)፦ እውቋ የደቡብ አፍሪካ የፀረ-አፓርታይድ ታጋይ ድምፃዊት ማሪያ ማኬባ (ማማ አፍሪካ) ዛሬ ሰኞ ኅዳር 1 ቀን 2001 ዓ.ም. በ76 ዓመቷ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች። ህልፈተ ሕይወቷ ለበጎ ሥራ በመድረክ ላይ እየተጫወተች እንዲሆን ምኞቷ ነበር፤ ተሳካላትም።

የአሜሪካው ምርጫ በፎቶግራፍ

በያዝነው የአውሮጳውያን ዓመት (2008) በዩናይትድ ስቴትስ የተደረገውን ምርጫ ጋዜጠኞች በፎቶግራፍ ዘግበውታል። 30 ምርጥ ፎቶግራፎችን እንዲመለከቱ እንጋብዛለን። (ፎቶግራፎቹ ከአሶሺየትድ ፕሬስ - AP፣ እና ከጌቲ - Getty የተወሰዱ ናቸው)

Barack's step-grandmother Sarah Obama in Kogelo, Kenya

ሣራ ኦባማ፣ የባራክ ኦባማ እንጀራ እናት ኬንያ ኮጄሎ ከተማ ሙሉውን አስነብበኝ ...

147 ሰዎች በዘር ማጥፋት ወንጀል ተከሰሱ

    በኦሮሞ ተወላጆች ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈፅመዋል የተባሉት
    - ለ98 ሰዎች አሰቃቂ ሞት ተጠያቂ ናቸው፣
    -  አንዲት ሴት ለ16 ሆነው ደፍረዋል፣  
    - 300 የሚሆኑ ቤቶች አቃጥለዋል፣
    - በርካታ የቀንድና የጋማ ከብቶችን አልባሳትና እህል ዘርፈዋል በሚል ተከሰዋል

Ethiopia Zare (ዓርብ ጥቅምት 28 ቀን 2001 ዓ.ም. November 7, 2008)፦ ሦስት ረዳት ኢንስፔክተሮችና ሁለት ኮንስታብሎችን ጨምሮ፣ አድራሻቸው እንደሚገልፀው 147 የቤንሻጉል ክልል ነዋሪዎች፤ በብሔረሰብ አንድ የኾነን ህዝብ በሞላ ወይም በከፊል ለማጥፋት በማሰብ የኦሮሞ ብሔረሰብ ተወላጅ በሆኑ አርሶ አደሮች ላይ ጉዳት በማድረስ የ98 ሰዎችን ህይወት አጥፍተዋል፣ የአካል ጉዳት አድርሰዋል፣ አንዲት ሴት ለ16 በመኾን አስገድደው ደፍረዋል፣ 300 የሚኾኑ ቤቶች አቃጥለዋል፣ በርካታ የቀንድና፣ የጋማ ከብቶችን፣ አልባሳትና እህል ዘርፈል ባላቸው ተከሳሾች ላይ የፌደራል ዓቃቤ ሕግ ክስ መሠረተ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከኦነግ ጋር በተያያዘ 15 ሰዎች ታሰሩ

የሒልተን ሆቴል ም/ሥራ አስኪያጅና የሐዊ ሆቴል ባለቤት ይገኙበታል

(ስም ዝርዝራቸውን ይዘናል)

Ethiopia Zare (ዓርብ ጥቅምት 28 ቀን 2001 ዓ.ም. November 7, 2008)፦ የአዲስ አበባ ሒልተን ሆቴል ም/ሥራ አስኪያጅና የሐዊ ሆቴል ባለቤትን ጨምሮ፣ በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ አንዳንድ ግለሰቦች፣ ከኦነግ ጋር በተያያዘ ታሰሩ። ከተጠርጣሪዎቹ ውስጥ አንዳንዶቹ የኦፌዲንና የኦብኮ አባላቶች እንደሚገኙበት ገልጾ፣ በከተማ ውስጥ የተለያየ የሽብር ተግባራትን ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ የተገኙ ናቸው ሲል ፖሊስ መግለጫ አውጥቷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በአራቱ የሀገሪቱ ማዕዘናት አንድነት 35 ቢሮዎችን ከፈተ

Ethiopia Zare (ዓርብ ጥቅምት 28 ቀን 2001 ዓ.ም. November 7, 2008)፦ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ፣ በአራት የተለያዩ የሀገሪቱ ማዕዘናት ለሁለት ሣምንታት ተንቀሳቅሶ 35 ጽ/ቤቶችን መክፈቱንና አባላት ማደራጀቱን አስታወቀ። ከከፈታቸው ቢሮዎች አምስቱ በህዝቡ ግፊት ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...