የቴዲ አፍሮ ጠበቃ ተፈታ፣ ቴዲ ከጨለማ ቤት ወጣ

Ethiopia Zare (ዓርብ ነኀሴ 2 ቀን 2000 ዓ.ም. August 08, 2008)፦ የቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ጠበቃ አቶ ሚሊዮን አሰፋ ባለፈው ረቡዕ ሐምሌ 30 ቀን 2000 ዓ.ም. ”ችሎት በመዳፈር” በሚል ለአንድ ወር ከሃያ ቀናት ከተፈረደበት በኋላ በጠቃው አቶ አበባ አሳምን አማካኝነት ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ተዘዋዋሪ ችሎት ይግባኝ በማለቱ አቶ ሚሊዮን ዛሬ ማምሻውን መፈታቱን እንዲሁም ቴዲ አፍሮ ደግሞ 27 ቀናት ታስሮ ከነበረበት ጨለማ ቤት እንዲወጣ መደረጉን የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች ገለጡ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከ34 ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ስለድርቅ ተዘፈነ

Ethiopia Zare (ኀሙስ ነኀሴ 1 ቀን 2000 ዓ.ም. August 07, 2008)፦ ወጣት ሔኖክ ገብሬ ከኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገጽ በጋራ በመተባበር ”ምንድንነው ምስጢሩ?” በሚል ርዕስ በሀገራችን በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለውን ድርቅና ረሃብ በሚመለከት ነጠላ ዜማ በዛሬው ዕለት ለህዝብ አቅርቧል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአንድነት ፓርቲ ማመልከቻ ዓርብ በቦርዱ ይታያል

ቦርዱ በአንድ ወር ምላሽ ካልሰጠ ድርጅቱ ሕጋዊ ይሆናል

Ethiopia Zare (ኀሙስ ነኀሴ 1 ቀን 2000 ዓ.ም. August 07, 2008)፦ ዛሬ ከአዲስ አበባ በደረሰን መረጃ መሰረት አንድነት ፓርቲ አስር ማስተካከያዎችን አድርጎ ያስገባው ማመልከቻ ከጽሕፈት ቤቱ ወደ ቦርዱ መመራቱንና ዓርብ ለመጀመሪያ ጊዜ ቦርዱ እንደሚያየው ታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የቴዲ አፍሮ ጠበቃ እስር ተፈረደበት

Teddy Afroጋዜጠኛው በገደብ ተለቋል

የቴዲ ጠበቃ እንቁጣጣሽን ቃሊቲ ያሳልፋል

Ethiopia Zare (ረቡዕ ሐምሌ 30 ቀን 2000 ዓ.ም. August 06, 2008)፦ የቴዎድሮስ ካሳሁንን ችሎት የሚመሩት ዳኛ ልዑል ገብረማርያም በችሎቱ ሂደት ላይ ፍትሃዊ ባለመሆናቸው የተነሳ ለዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ክስ እመሰርታለሁ በማለት ለአዲስ ነገር ጋዜጣ ላይ ቃለምልልስ የሰጠው የቴዲ አፍሮ ጠበቃና ቃለ ምልልሱን ያተመው ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ዛሬ የተፈረደባቸው መሆኑን የአዲስ አበባ ዘጋቢዎቻችን አረጋገጡ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የቴዲ ጠበቃና የአዲስ ነገር አዘጋጅ ለነገ ተቀጠሩ

ታስረው ይቆዩ ተብሏል

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ሐምሌ 29 ቀን 2000 ዓ.ም. August 05, 2008)፦ በዳኛ ልዑል ገ/ማርያም ትዕዛዝ ዛሬ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ የታዘዙት የቴዲ አፍሮ ጠበቃ ሚሊዮን አሰፋና የአዲስ ነገር ጋዜጣ አዘጋጅ መስፍን ነጋሽ ታስረው ካደሩበት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበው፤ ለነገ መቀጠራቸውን የፍርዱን ሂደት ከተከታተሉ የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች ለማወቅ ችለናል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አውራምባ ታይምስ ስለ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እንዳይዘግብ ታገደ

"ባለ 30 ገጽ ክስ ተዘጋጅቶብኛል" አውራምባ ታይምስ

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ሐምሌ 29 ቀን 2000 ዓ.ም. August 05, 2008)፦ ዛሬ ገበያ ላይ የዋለው "አውራምባ ታይምስ" ጋዜጣ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋን በሚመለከት ምንም አይነት ዘገባ እንዳይዘግብ መከልከሉን በመግለጽ የዶ/ሩን ምስል በትልቁ የኤክስ ምልክት አድርጎ በማውጣት ጋዜጣውን ለአንባቢዎቹ ማቅረቡን ሪፖርተሮቻችን ከአዲስ አበባ ገለጹ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የቴዲ አፍሮ ጠበቃ እና የአዲስ ነገር ጋዜጣ አዘጋጆች ታሰሩ

Teddy Afroምክንያቱ የቴዲ ጠበቃ ለአዲስ ነገር ጋዜጣ ዳኛውንና ተርጓሚውን እንደሚከስ መግለጹ ነው

Ethiopia Zare (ሰኞ ሐምሌ 28 ቀን 2000 ዓ.ም. August 04, 2008)፦ የቴዲ አፍሮ ጠበቃ አቶ ሚሊዮን አሰፋ የቴዲን ጉዳይ የሚያዩትን ዳኛ ልዑል ገብረማርያምን እና የምንሊክ ሆስፒታል አስተርጓሚን እንደሚከስ ለአዲስ ነገር ጋዜጣ በመግለጹና ጋዜጣው ዜናውን በመዘገቡ ምክንያት የጋዜጣው ዋና አዘጋጆችንና ጠበቃውን ፖሊስ ይዞ እንዲያቀርባቸው ዳኛው በሰጡት ትዕዛዝ መሰረት የጋዜጣው አዘጋጆች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበው እንደነበር ከአዲስ አበባ የኢትዮጵያ ዛሬ ዘጋቢ ገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮ-ስዊድን ዋንጫውን ወሰደ

ESCFE cup, sweden 2008

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ሐምሌ 26 ቀን 2000 ዓ.ም. August 02, 2008)፦ በስዊድን ዋና ከተማ ስቶክሆልም በተካሄደው በአውሮጳ የስድስተኛው የኢትዮጵያውያን የስፖርትና የባህል ፌስቲቫል ላይ በተደረገው የእግር ኳስ ውድድር የኢትዮ-ስዊድን ቡድን ከሎንዶኑ ካታንጋ ጋር ለፍፃሜ ደርሰው ኢትዮ-ስዊድን በቅጣትምት አራት ለሦስት አሸንፏል። ቡድኑ ከክብር እንግዶቹ አንዱ ከሆነው ከመንግሥቱ ወርቁ ዋንጫውን ወስዷል። (በፎቶግራፉ ላይ አቶ መንግሥቱ ወርቁ ለኢትዮ-ስዊድን የቡድን አንበል ዋንጫውን ሲሰጥ) 

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በኢትዮ-ኤርትራ ድንበር ጦርነት አንዣቧል

አንሚ የኢትዮ- ኤርትራን ድንበር ለቆ እንዲወጣ ተወሰነ

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ሐምሌ 26 ቀን 2000 ዓ.ም. August 02, 2008)፦ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት፣ በኢትዮ ኤርትራ ድንበር ላለፉት ስምንት ዓመታት አሰማርቶት የነበረውን የሰላም አስከባሪ ኃይል እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ማቆሙን አስታወቀ፡፡ ኢትዮጵያና ኤርትራ በማንኛውም ሰዓት ጦርነት ውስጥ ይገባሉ ተብሎ ተሰግቷል፡፡ በኢትዮጵያ በኩል መንግስት በሚቆጣጠራቸው የመገናኛ ብዙሀን ልዩ ቅስቀሳ እየተካሄደ ሲሆን የተለያዩ ዘመናዊ ጦር መሳሪያዎች በቲቪ ለህዝብ እየቀረቡ መሆኑን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ይጠቁማል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...