አቶ አሰፋ አብርሓ ትላንት ከእስር ተለቀቀ
Ethiopia Zare (ዓርብ ሐምሌ 25 ቀን 2000 ዓ.ም. August 01, 2008)፦ በሙስና ወንጀል ተከሰው ፍርድ ቤት ለሰባት ዓመታት ታስረው ከነበሩት ሦስቱ ወንድማማቾች ብቻውን ቀርቶ የነበረው አቶ አሰፋ አብርሃ በትናንትናው ዕለት ከእስር የተለቀቀ መሆኑን የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች አረጋገጡ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...Ethiopia Zare (ዓርብ ሐምሌ 25 ቀን 2000 ዓ.ም. August 01, 2008)፦ በሙስና ወንጀል ተከሰው ፍርድ ቤት ለሰባት ዓመታት ታስረው ከነበሩት ሦስቱ ወንድማማቾች ብቻውን ቀርቶ የነበረው አቶ አሰፋ አብርሃ በትናንትናው ዕለት ከእስር የተለቀቀ መሆኑን የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች አረጋገጡ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ሰዓሊው 700 ሺህ ብር ካሣ ጠይቆ ነበር
Ethiopia Zare (ዓርብ ሐምሌ 25 ቀን 2000 ዓ.ም. August 01, 2008)፦ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት "ቴዎድሮስ ካሳሁን ከኤሌክትራ ሙዚቃ ቤት ባለቤት ጋር፣ በጋራ በመሆን ጭንብል ለብሰው፣ መንገድ ዘግተው የሥዕል ሥራዎቼን ከመኖሪያ ቤቴ በመስረቅ ያለፈቃዴ ተጠቅመዋል። የሥዕሎቼን ክብር በሚነካ ሁኔታም ተጠቅመው የሞራል ጉዳት አድርሰውብኛል" በሚል የ700 ሺህ ብር ካሣ ክፍያ ጥያቄ አቅርቦ ክሱ ውድቅ የተደረገበት ሰዓሊ ይግባኝ ጠየቀ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...

Ethiopia Zare (ዓርብ ሐምሌ 25 ቀን 2000 ዓ.ም. August 01, 2008)፦ በስዊድን ዋና ከተማ ስቶክሆልም የሚካሄደው በአውሮጳ የስድስተኛው የኢትዮጵያውያን የስፖርትና የባህል ፌስቲቫል ዛሬ ጠዋት አምስት ሰዓት (11 AM) የእግር ኳስ ጨዋታው በክብር እንግዶቹ በመንግሥቱ ወርቁ እና በሉቺያኖ ቫሳሎ ተመርቆ ተጀምሯል። (በፎቶግራፉ ላይ ንግግር የሚያደርገው መንግሥቱ ወርቁ ሲሆን፣ በስተግራው ደግሞ ያለው ሉቺያኖ ነው)
ሙሉውን አስነብበኝ ...በዮናታን ፀጋዬ
Ethiopia Zare (ኀሙስ ሐምሌ 24 ቀን 2000 ዓ.ም. July 31, 2008)፦ ስድስተኛው በአውሮጳ የኢትዮጵያውያን የስፖርትና የባህል ፌስቲቫል ዛሬ ማምሻውን በ18፡30 ሰዓት ላይ በስዊድን ዋና ከተማ ስቶክሆልም “ኦሽታ” በተሰኘው ክፍለ ከተማ የህዝብ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ”ቁጭት” በተሰኘው ፊልም በይፋ ተከፈተ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ምክንያቱ የዶ/ር አሸብር ከኢ.እ.ኳ.ፌ. ፕሬዝዳንትነት መባረር ነው
Ethiopia Zare (ረቡዕ ሐምሌ 23 ቀን 2000 ዓ.ም. July 30, 2008)፦ ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን (ፊፋ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን ከማናቸውም ዓለም አቀፍና አህጉር አቀፍ ውድድሮች እንዲሁም ከሌሎች ሀገሮች የእግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ጋር የሚኖረውን ግንኙት ከትናንት ጀምሮ ማገዱን አስታወቀ። መንስኤው የዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንትነት መባረር ነው።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
Ethiopia Zare (ማክሰኞ ሐምሌ 22 ቀን 2000 ዓ.ም. July 29, 2008)፦ ”በቸልተኝነት መኪና በማሽከርከር የሰው ሕይወት እንዲያልፍ አድርገሃል” ተብሎ ተከሶ ለነበረው ድምፃዊ ሰማኸኝ በለው የመከላከያ ምስክር ሆኖ የቀረበው ትራፊክ ፖሊስ ለሰማኸኝ በሐሰት መስክረሃል በሚል በዛሬው ችሎት ”ጥፋተኛ” መባሉን የኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገጽ ሪፖርተር ዘገበ።
Ethiopia Zare (ማክሰኞ ሐምሌ 22 ቀን 2000 ዓ.ም. July 29, 2008)፦ በአሜሪካ ምርጫ ኦባማም ይመረጥ ማኬይን አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የምታራምደው ፖሊሲ እንደማይቀየር የአሜሪካ የዲሞክራሲና ሰብዓዊ መብት ቢሮ ረዳት ሴክረታሪ ሚስተር ዴቪድ ክራመር ገለፁ። አያይዘውም ሀገራቸው በኢትዮጵያ ያለው የሰብዓዊ መብት አያያዝ፣ ፕሬስንና መያዶችን አስመልክቶ የወጣው ሕግ እንደሚያሳስባት ተናግረዋል።
Ethiopia Zare (ማክሰኞ ሐምሌ 22 ቀን 2000 ዓ.ም. July 29, 2008)፦ ኢንጂንየር ናርዶስ ሙሉጌታ ነዋሪነቱ በእንግሊዝ አገር ሲሆን፣ የ40 ዓመት ጎልማሳ ነው። የሚሠራው በታዋቂው የፎቶ ኮፒ ማሽን አምራች በሆነው ዜሮክስ (Xerox) ኩባንያ ውስጥ ነበር።
Ethiopia Zare (እሁድ ሐምሌ 20 ቀን 2000 ዓ.ም. July 27, 2008)፦ ኢትዮጵያውያን ባለሥልጣኖች የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ወስደው ሥራ ለመሥራት ኢትዮጵያ ከሚገቡ የቻይና ድርጅቶች ጋር በከፍተኛ ሙስና ተሳስረዋል። ቻይናውያን ከሚወስዱዋቸው በቢሊዮን በሚቆጠር ገንዘብ የሚያወጡ ፕሮጀክቶች መካከል የመንገድ ሥራ፣ የቴሌ ኔትዎርክ ግንባታ፣ የመብራት ኃይል ሥራዎች ተጠቃሽ ናቸው።
ሙሉውን አስነብበኝ ...አንድ በቆሎ 2 ብር ገብቷል
ባለፈው ዓመት 50 ሣንቲም የነበረው አንድ የተጠበሰ በቆሎ 2 ብር ከ50 ሣንቲም ገባ
Ethiopia Zare (እሁድ ሐምሌ 20 ቀን 2000 ዓ.ም. July 27, 2008)፦ በዘንድሮው የምርት ዘመን የበቆሎ ምርት በከፍተኛ ሁኔታ በማጠሩ የአንድ ነጠላ የተጠበሰ በቆሎ ዋጋ ሁለት ብር ከ50 ሣንቲም ሲሆን፣ ያልተጠበሰው ደግሞ ሁለት ብር እየተሸጠ መሆኑን በአዲስ አበባ ተዘዋውረው ያረጋገጡ የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች ገለጹ። ባለፈው ዓመት ሦስቱ የተጠበሰ በቆሎ አንድ ብር ይሸጥ የነበረ ሲሆን፣ አንድ ፍሬ በቆሎ ደግሞ 50 ሣንቲም ነበር።
ሙሉውን አስነብበኝ ...