ተኩስ አቁም ይደረግ!

ከወለላዬ (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. ) ኅዳር 10 ቀን 2001 ዓ.ም. (ኖቨምበር 19, 2008)

(በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ)

ልዩነቱ በዛ መስማማቱ ጠፍቶ፣

ትግሉም ወደኋላ ቀረ ተጎትቶ፣

መንግሥት ንጹኅ ዜጎች አለፍርድ ገድሏል፣

መብትና ነፃነት ዲሞክራሲ አፍኗል፣

በምርጫ ብንጥለው ድምፃችንን ነጥቋል፣

ሌላም ሌላም ነገር ብዙ ችግር ፈጥሯል፣

በሠላምም ሆነ በተገኘው መንገድ፣

ከሥልጣን ወንበሩ አለበት መወገድ፣

 

ከሆነ ነገሩ የተቃውሞው መንፈስ፣

አንዱ አንዱን ሳይነካ አለበት መገስገስ።

አለዛ እርስ በእርስ እንዲህ ተጠላልፎ፣

አይቻልም ጭራሽ መጣል አሸንፎ።

ለምሳሌ አንድ ሰው ባለንበት መንደር፣

ወንጀል እየሠራ ቢፈጥርብን ችግር፣

ሕግ ፊት ለማቅረብ ያንን ሰው ለመያዝ፣

ጭቅጭቅ ካመጣን ካበዛን ንዝንዝ፣

 

ጥፋተኛው በሀብት ከአካባቢው በልጦ፣

በዘዴ በጥቅም እኛን አበጣብጦ፣

ይኖራል በሠላም እግሩን አንፈራጦ።

ይህንን ይመስላል አሁንም ነገሩ፣

በቃውሞው ጎራ በዝቶ ግርግሩ

በደለኛ ጭራሽ በሕጋዊ መንገድ፣

ሀገር እየመራ መሰለ እሚራመድ።

 

ስለዚህ በቶሎ ይሄን መጠላለፍ፣

አንዱ ተቃዋሚ ሌላን ወገን መዝለፍ፣

እንካ ሰላምትያ እሰጥና አገባ፣

ቃላትን መሰንጠቅ ተንኮልና ደባ፣

ስም ማጥፋት ውንጀላ የርስ በርስ ሻጥር፣

ለዚች በድህነት ለደቀቀች ሀገር፣

ለራበው ለጠማው ለተበደለ ህዝብ፣

አይረዳውም ጭራሽ ይበጅለት ገደብ።

ጥላቻውም ከፍቶ ከዚህ በላይ ሳያድግ፣

ትግሉ እንዲጠናከር ተኩስ አቁም ይደረግ!


 

ከወለላዬ (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. ) ኅዳር 10 ቀን 2001 ዓ.ም. (ኖቨምበር 19, 2008)

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ