የረቡዕ ግጥም ፬ኛ ዓመት፣ ቁ. ፲፮

በብልጦች መንገድ ላይ ደንቃራ እንደረገጥሽ
በብልጦች መንገድ ላይ!
ሞኝ ነህ! እንዳልሽኝ፣ ያኔ! እንደነገርሽኝ፤
በዛው የሞኝ እግር፣ በዛው የጅል ጫማ፤
የብልጦች መሔጃን መንገድ ሳልሻማ፤
እዚህ ደርሻለሁ - ያንቺን ሰማሁልሽ
በብልጦች መንገድ ላይ ደንቃራ እንደረገጥሽ።
ወለላዬ ከስዊድን (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.)