‘አልወለድም’ (መስፍን ማሞ)
አልወለድም
ደራሲ - አቤ ጉበኛ
አስተያየት - መስፍን ማሞ ተሰማ
መነሻ
በተለያዩ ማህበራዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የረዥም ርቀት ጭውውት ከምናደርጋቸው ወዳጆቼ መኻል በቅርቡ ዳጎስ ያለ ፖስታ ደረሰኝ። ከፍቼ ስመለከተው የአቤ ጎበኛ አልወለድም መጽሐፍ ፎቶ ኮፒ ነበር።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
አልወለድም
ደራሲ - አቤ ጉበኛ
አስተያየት - መስፍን ማሞ ተሰማ
መነሻ
በተለያዩ ማህበራዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የረዥም ርቀት ጭውውት ከምናደርጋቸው ወዳጆቼ መኻል በቅርቡ ዳጎስ ያለ ፖስታ ደረሰኝ። ከፍቼ ስመለከተው የአቤ ጎበኛ አልወለድም መጽሐፍ ፎቶ ኮፒ ነበር።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
አረጋዊ በርሀ (ዘሔግ)
በቅርቡ “መለስ ዜናዊ እና የህወሓት የትግል ጉዞ” በሚል ርዕስ፣ ፀሐፊ ኢያሱ መንገሻ (ኮ/ል) ተብሎ፣ ባለ 313 ገፆች አንድ መጽሐፍ መጋቢት 2002 ዓ.ም. አዲስ አበባ ታትሞ ወጥቶ፤ ከጫፍ እስከ ጫፍ አነበብኩላቸው። መጽሐፉ አቶ መለስን ልዩ የታሪክ ካባ ለማልበስ ሲባል ብዙ የተደከመበት የፈጠራ ቅንብር መሆኑ ገና ከሽፋኑና ከመቅድሙ ያስታውቃል። ለዚሁም በተጨማሪ ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ከባህል ሚኒስትሩ ጋር በመሆን በሸራተን ሆቴል ደግሰው ነሐሴ 22 ቀን 2002 ዓ.ም. መርቀውለታል። ፀሐፊው ኮ/ል ኢያሱ መንገሻ ይባል እንጂ፤ በዚህ የፈጠራ ቅንብር የአቶ መለስ እጅ በእጅጉ እንዳለበት ብዙ ጠቋሚ ነጥቦች በዚህ መጽሐፍ ይገኛሉ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...በ”ምርኮኛ” መጽሐፍ ላይ የግል አስተያየት
ነሲቡ ስብሐት (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.)
በአንድ ብዕር ሁለት መጽሐፍ። የዚያን ትውልድ ተጋድሎና የዘመኑን መቅሰፍት። በአንድ በኩል በወጣትነት ዘመኑ ያ ትውልድ ለሀገሩ አንድነት፣ ለሰው ልጆች መብትና ለዴሞክራሲ ያደረገውን ተጋድሎና የከፈለውን መስዋዕትነት፤ በሌላ በኩል የዛሬው ወጣቶች ደግሞ በኤች.አይ.ቪ. ቫይረስ የተጠቁትን ወገኖች በግብረ ሰናይ ድርጅቶች አማካይነት የሚያደርጉትን እንክብካቤና ሕይወት አርዝም ጥረት።
ሙሉውን አስነብበኝ ...አበራ ለማ
ይድረስ ለሥነኪን ተጠባቢው አለማየሁ ታዬ - ታለህበት
ይህች ሂሣዊ ንባብ አከል ማስታወሻዬ ትድረስህ። እንደ ተጋባዥ የሥነ ግጥም የኔታ ሁኜ፣ አንተ ደግሞ የ”ፍካታ የሥነ-ጽሑፍ ክበብ” ታሊባን* ሁነህ የዛሬ አሥራ ምናምን ዓመታት በፊት እንደተዋወቅን ከላክልኝ መልዕክት ተረድቻለሁ። የዘሩት በቅሎ፣ አሽቶ፣ ፍሬውም ጎምርቶና በስሎ ከማየት በላይ ላንድ ገበሬ ምን የሚያስደስተው ፀጋ አለ? የኔና ያንተም ትውውቅና ቁርኝት በዚህ ሊመሰል ታድሏልና እሰየው ነው።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ታምራት ታረቀኝ
አቶ ስየ አብርሃ መጽሐፍ ጻፉ ሲባል ለማግኘት ጉጉት ያደረብኝ ከደደቢት እስከ ምኒልክ ቤተመንግሥት በነበረው ጉዞ አበይት የሆኑትን ይልቁንም ሌላው ተራ ታጋይ ሊያውቃቸው የማይችላቸውን ግን ትውልድ ሊያውቃቸው ታሪክም ሊመዘግባቸው የሚገቡ ጉዳዮችን ይተርኩልናል በሚል ስሜት ነበር።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ጌዲዎን በለጡ
የዛሬው ትኩረቴ መጥሐፉ በጥቅል ሃሳቡ ባስተላለፈልኝ ፍሬ ጉዳይ ላይ ብቻ ያነጣጠረ በመሆኑ እንዲያ ብቻ ይተርጎምልኝ፤ ባለ 439 ገጹ “ነፃነትና ዳኝነት” ስለያዘው ዝርዝር ጉዳይ የተገለጠልኝን ያህል ለማለት በሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ። ለወጉ ይመቸኝ ዘንዴ አለፍ አለፍ ብዬ በመግቢያቸው በመጀመሪያውና በሁለተኛው አንቀጽ የተጠቀሰውን ላመል መነካካት አሻኝ፤ ...
ሙሉውን አስነብበኝ ...የተስፋዬ ገብረአብ የመጽሐፍ-ሂሱ ሂስ

ዘውገ ፋንታ
መግቢያ
ደራሲው ተስፋዬ ገብረአብ፣ ስየ አብርሃ ስለጻፈው “ዝባዝንኬ” መጽሐፍ ባቀረበው “የመጽሐፍ ሂስ” ሌላ ሂስ መጻፍ ለማይቀርብ ምግብ እጅ ማስታጠብ ይሆናል። የዚህ ጽሑፍ ዓላማ ተስፋዬ ገብረአብ ስለ ስየ መጽሐፍ ማሾፉን ለመቃወም ወይም ስየን ለመደገፍ አይደለም። ስየ ይህን ከጠበቀ በውጤቱ ሊበሳጭ ይችላል። ተስፋዬ ገብረአብም የስየ መጽሐፍ ውሸት የዋጠው ነው ያለውን ይህ ፀሐፊ ቢደግፍም የዚህ ጽሑፍ ዓላማ ሲገለጽ የሚያረካው አይሆንም።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ተስፋዬ ገብረአብ
ስየ አብርሃ የፃፈውን መጽሐፍ አነበብኩት።
የተደጋገመውን ዝባዝንኬ እየዘለልኩ እንደምንም ጨረስኩት። የስየ ወንድሞች የገዟቸው መኪኖች የሻንሲ ቁጥር ምንም ስለማያደርግልኝ እየነጠርኩ አልፌዋለሁ።
ስየ ላይ አልፈረድኩበትም። ሙሉውን አስነብበኝ ...
ያገር ልጅ
ስለተስፋዬ ገብረአብ ሸጋ የአማርኛ ቋንቋ ብዕርተኝነት እንዳዲስ እዚህ ላይ አላነሳም። በጣም ብዙ ብዙ ተቺዎችና አስተያየት አንጓቾች በቁጥራቸው መጠን ብለውታል። ደራሲው ተስፋዬና የፕሮፓጋንዳ መጣጥፍ ጣፊው ተስፋዬም የብዕር ውበት ለዛቸው አንድ ነው። ልዩነታቸው ከዘላቂው የፈጠራ ሥነ-ጽሑፍ ሰብዕናና ካላፊው ከረጋፊው የፕሮፓጋንዳ ሰውነት ላይ ብቻ ነው። ሙሉውን አስነብበኝ ...