አሰባብሮ ወደ ፖለቲካ፤ ለአማተር ፖለቲከኞች፣ ስድስቱ አቋራጭ ነጥቦች፣ …(ሰሎሞን ተሰማ ጂ.)

ሰሎሞን ተሰማ ጂ. (ከአ.አ.)

የዛሬ ስምስት አመት ገደማ፣ ዝነኛ የሩጫ ባለሙያ ኃይሌ ገ/ሥላሴ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ወደ ፖለቲከኛነት እቀየሳለሁ ሲል ተደምጧል። ኃይሌ ብቻም ሳይሆን ታዋቂው የኢትዮ ሳውዲ ቱጃር ሼክ ሙሐመድ አላሙዲን በ1997 ዓ.ም ከመቅጽፈት ወደ ፖለቲከኛነት ተቀይረው ነበር። ከተዋንያኑና ከመድረክ ሙያተኞቹ እነ ደበበ እሸቱ፣ ታማኝ በየነ፣ ሰለሞን ተካልኝ፣ ነዋይ ደበበና ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዴ አፍሮ) ከመቅጽፈት ከተዋቂዎቹ አደባባይ ወደ ፖለቲካ መድረክ ላይ ሊገቡ ሲሞክሩ አይተናል፤ ታዝበናል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያውያን በዚህች ሰዓት (ተሻለ መንግሥቱ)

ተሻለ መንግሥቱ

በውጪ ሀገራት የምትኖሩ ወገኖቻችን እኛ በሀገር ውስጥ ያለነው ወገኖቻችሁ እየኖርን እሚመስላችሁ ከሆነ እያልኖርን መሆናችንን ትረዱ ዘንድ ይህችን አጭር ዘገባ በጥሞና አንብቡና የምንገኝበትን ሰቆቃ ተገንዘቡልን፤ ‹እኛ› ስል ብዙዎቻችንን ማለቴ እንጂ የኀልውናችን መረጋገጥ ለኅልውናቸው ማሸብረቅ መሠረት የሆነውን እነአያ እንደልቡን እንዳልሆነ መቼም ካለተጨማሪ ማብራሪያ ይገባችኋል ብዬ እገምታለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሙሉጌታ ኃይሉ - የጠለቀው ጀንበር

ደረጀ ከበደ እና ኃይለገብርኤል አያሌው

እንደ አለመታደል ሆኖ አካዳሚክ እውቀት፣ የዘመናዊነት ተጽዕኖ፣ የምዕራባውያኑ በጎ ባህል ሁሉ የቅርባችን ሆኖ እያለ ልንላቀቀውና ልንተወው ካልቻልንው አሮጌ ባህላችን ውስጥ አንዱ የሆነው ሰዎች በህይወት ዘመናቸው ለሚያደርጉት በጎ አስተዋጽዖ፤ በሕይወት እያሉ የማመስገንና ለተተኪው ትውልድ ያላቸውን አርኣያነት በማንሳት ማክበርና የድካማቸውን ፍሬ ሌሎች እንዲማሩበት ማድረግ ተስኖናል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢህአዴግ የማይሰማቸው የኢህአዴግ ድምፆች

ተመስገን ደሳለኝ

‹‹...ኑሮ ተወደደ፣ ድህነት በረከተ፣ ህግ ተፋለሰ፣ አድሎአዊ አስተዳደር ሰፈነ፣ የብሔር ከፍፍሉ አስከፊ ደረጃ ደረሰ፣ ስራ አጥ ተንሰራፋ፣ ሀገር ጥሎ የሚሰደደው በዛ፣ ረሀብተኛው ስፍር ቁጥር አጣ፣ በሀገር ላይ የመኖር ዋስትና ጠፋ፣ ሰላም ደፈረሰ፣ ተስፋ መነመነ፣ ሀብት ንብረት ማፍራት ከበደ፣ አምባገነንነት ገነገነ፣ ፓርላማው በአንድ ጉልበተኛ ፓርቲ መዳፍ ወደቀ፣ በልማት ስም ያለጥናት ማፈናቀሉ ለስቃይ ዳረገ፣ ግብር የነጠቃን ያህል አደገ...ወዘተርፈ›› ሙሉውን አስነብበኝ ...

ተቀናቃኝ ቡድኖችና ፖለቲካ

ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም
ተመስገን ደሳለኝ በተቀናቃኝ ቡድኖች ላይ አዲስ የመነጋገሪያ ርእስ ከፍቶአል (ግንቦት 3፣ 2004)፤ ጉዳዩ በጣም አንገብጋቢና በጣም ወቅታዊ ነው፤ እንደተለመደው አንብበን ችላ የምንለው ጉዳይ አይደለም፤ ሁላችንም በተቻለን መጠን እውነትን ይዘን ያለ ይሉኝታና ያለፍርሃት በራሳችን ላይ እንዝመትና እውነትን ይዘን እንነሣ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የህዝብ እና የተቃዋሚ ፓርቲዎች መንታ መንገድ

ተመስገን ደሳለኝ

የመኢአድ ም/ሊቀመንበር ዶ/ር ታዲዮስ ቦጋለ የመኢአድ ሊቀመንበር በሆኑት ኢንጂነር ኃይሉ ሻወል በተከሰሱበት ክስ ሁለት አመት ከስድስት ወር ተፈርዶባቸው ከርቸሌ ገቡ፤ መኢአድ እንደአንባሻ ተከፋፈለ፤ የማይለያዩት ኃይሉ ሻውል እና ማሙሸት አማረ ተለያዩ። አንድነት ፓርቲ ብርቱካን ሚደቅሳ ትፈታ ይል የነበረውን ጥያቄ አንዱአለም አራጌ ይፈታ በሚል ቀየረው፤ ብርቱካንን በማስብ ይበራ የነበረውንም ሻማ አንዷአለምን በማሰብ ይበራ ዘንድ ወሰነ፤ ብርቱካን ሚደቅሳ ስለኢትዮጵያ ፖለቲካ ልታጠና ዋሽንግተን ሄደች፣ ስዬ አብርሃ ለትምህርት ወደአሜሪካ ሄዱ፤ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ጀርመናዊ ህፃናቶችን ስለኢትዮጵያ ፖለቲካ ሊያስተምሩ ጀርመን ገቡ፡፡ ሙሉውን አስነብበኝ ...

ታሪክ ያላነበቡ ታሪክ ሰሪዎችና፣ ታሪክ ያላነበቡት ታሪክ ዘካሪዎች፣ ጉድ አፈሉብን!

ሰሎሞን ተሰማ ጂ. (ከአ.አ) - (ለፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም በተለይ)

0. መግቢያ

ፍሬድርክ ኒቼ በደስታና በፈንጠዝያ የምፎልሉትን እንሰሳት ተጠጋና ጠየቃቸው። "ለምንድነው እንደዚህ ደስተኛ ልትሆኑ የቻላችሁት?" የሚል ነበር ጥያቄው። እነሱም ባንድነት፣ ባንድ ቃል መለሱለት። ምንም ሳይወያዩ፣ ምንም ነገር ሳይፎካከሩ፣ መንፍሳቸውም ሳይቀናና፣ አንዱም ሌላውን ሳይተች፣ ደመ-ነሳቸው በሚነግራቸው መሰረት፣ "ምንም ታሪክ (memory of things) ስለሌለን ነዋ!" አሉት። ከአፍታ በሁዋላ "ምን አላችሁኝ? እስኪ ድገሙልኝ?" ሲል ጥያቄዎቹን አጅጎደጎደባቸው። እነሱ ግን የሰጡት መልስ አጭርና አስገራሚ ነበር። "ምኑን ነው የምንደግምልህ?" የሚልና ክው አድርጎ የሚያስቀር መልስ። ሁሌም የሚደንቀኝ አይነት፣ "ቅስም-ሰባሪ" መልስ ይሉዋችሁዋል እንዲህ ያለው ነው-እንጂ! ሌላ ምን ሊሆን ይችላል? ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሹክሹክታው ክፍል ሁለት ገፅታ

ተመስገን ደሳለኝ
ከዚህ ቀደም ‹‹ሹክሹክታው ምንድርነው?›› በሚል ርዕሰ ጉዳይ አንድ ፅሁፍ ፅፌ ነበር። የፅሁፉ ጭብጥ የሚያጠነጥነው የአረብ ሀገራት የተሳካ አብዮትን ተከትሎ በኢትዮጵያም ሁለት ዓይነት ሹክሹክታዎች ነፍስ መዝራታቸው ላይ ነበር። ሙሉውን አስነብበኝ ...

በፍትሕ ጋዜጣ ላይ ለምንጽፍ ሁሉ እየተናገሩ አለማነጋገር፣ እያሰቡ አለማሳሰብ

ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም

ይህ ጽሑፍ ለእኔም የተጻፈ በመሆኑ አንድ ቀልድ እንደመግቢያ ልናገር፤ አማኑኤል ሆስፒታል ሕመምተኛው ውጭ ይጽፋል፤ ሀኪሙ ይመጣና ‹‹ከበደ፣ እንደምናደርህ?›› ብሎት ሰላምታ ከተለዋወጡ በኋላ፣ ሀኪሙ ምን እየጻፍክ ነው? ይልና ይጠይቃል፤ ህመምተኛው ‹‹ደብዳቤ›› ይላል፤ ሀኪሙ ‹‹ለማን ነው?›› ብሎ ሲጠይቅ፣ ሕመምተኛው ‹‹ለራሴ›› ይላል፤ ሀኪሙ የሕመምተኛውን የውስጥ ስሜት ለማወቅ ጓጉቶ ‹‹ምን ይላል?›› ብሎ ይጠይቃል፤ ሕመምተኛው በመደነቅ ዓይኑን በልጠጥ አድርጎ ‹‹ዶክተር መቼ ተላከና፣ መቼ ደረሰኝና!›› አለው፤ እኔም…

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ