ጠቅላይ ሚኒስትሩን አማካሪዎች በጨረፍታ ፫

ተመስገን ደሳለኝ

ከወር በፊት ‹‹የጠቅላይ ሚኒስትሩን አማካሪዎች በጨረፍታ›› በሚል ርዕስ በጀመርነው የ‹‹ጨረፍታ ዳሰሳ›› ሁለት አማካሪዎችን ‹‹ጨርፈን›› አይተን ነበር፡፡ ጓድ (ዶ/ር) ፋሲል ናሆምን እና ባይሎጂስቱን ሬድዋን ሁሴንን። በእርግጥ ስለሁለቱ አማካሪዎች ዛሬም ጥቂት እናይና ወደ ዋናው አጀንዳችን ወደፕ/ር እንድሪያስ እሸቴ እናመራለን። ከዛ በፊት ግን ስለእነጓድ ፋሲል ጥቂት ተጨማሪ መረጃዎችን ደግሞ ማየቱ ያስፈለገበትን ምክንያት ላስረዳ፤ ሙሉውን አስነብበኝ ...

ለኢትዮጵያዊያን፤ የጨለመው ስደት በኖርዌይ

ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ)

በሃገራቸው ባለው ጨካኝና አረመኔያዊ አገዛዝ ሳቢያ፤ገዛዙ በፈጠረው የኑሮ ውድነት፤ የነጻነት እጦት፤በችጋሩ፤ በሙስና፤ አረመኔው መንግሥት ሆን ብሎ፤ አውቆ፤ ፍጥረቱ ለጥፋት ተልእኮው በኢትዮጵያዊያን ላይ ስደትናእንግልትን ማደርጀት ነው፤ በሚፈጽመው የዲያቢሎስ ተግባር ሃገራቸውን ጥለው የተሰደዱት ኢትዮጵያዊያን በሰሜን አፍሪካ፤በመካከለኛው ምስራቅ በሌሎችም የአፍሪካ ሃገራት ለባሰ መከራና ስቃይ እየተዳረጉ ነው። ኢትዮጵያውስጥ መኖር ሳይሆን ለመኖር ማሰብ እንኳ ችግር ሆኖባቸው ስደትን ቢመርጡም ስደቱም ዳግም እያሰደዳቻው ነው። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የዳውሮ ህዝብ ከድጥ ወደ ማጥ (ክፍል -1)

ከቧንቧና ከምንጭ የሚገኘው ውሃ ወደ ቦቴ መኪና እደላ ተሸጋገረ

ዋካ ከስዊድን

መግቢያ 

ካለፉት ጥቂት ወራት ጀምሮ የዳውሮ ዋካ ህዝብ የተለያዩ የልማት ጥያቄዎችን ለመንግሥት ማቅረቡ ይታወቃል። ጥያቄውን ተከትሎ ገዢው የህወሃት መንግስት ፍትሃዊ ምላሽ ለህዝቡ ለመስጠት ባለመፈለጉና ባለመቻሉ የተነሳ በአካባቢው ከፍተኛ አለመረጋጋት ተከስቶ እንደነበርና መንግሥትም ዴሞክራሲያዊ የነበረውን የህዝብ ጥያቄ ተቀብሎ ኃላፊነት ባለው መልኩ አጥንቶና መርምሮ ውሳኔ መስጠት ሲጠበቅበት በርካታ ህዝብ በማሰርና በማንገላታት ብሎም በማስፈራራት ህዝባዊ እንቅስቃሴውን በጉልበት ለመግታት ሞክሯል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ቤታቸውን እየከፈቱ ሰው ሌባ ይላሉ

የስዊድን ጋዜጠኞችና…

ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም

የስዊድን ጋዜጠኞች በቃሊቲ መታሰራቸው ያሳዝናል፤ የሚያሳዝነው ራሳችንን በማጋለጣችን እንጂ ስዊድኖቹ ይጎዳሉ  በማለት ብቻ አይደለም፤ በአጠቃላይ በሁለት ‹‹ጥፋቶች›› እርግጠኛ መሆን የሚቻል ይመስለኛል፤ አንደኛ፣ ያለፈቃድ  ኢትዮጵያ ክልል ውስጥ ተገኝተዋል፤ የትም አገር ቢሆን ወንጀል ነው፤ ፋርስ ወይም ኢራን በተደጋጋሚ እንዲህ ዓይነት ሁኔታ አጋጥሞታል፤ ሁለተኛው በእኔ ግምት ጥፋታቸው የሚሆነው የምዕራባውያን አጠቃላይ ‹‹የነፃነት ትግል››  የተባለውን ሁሉ በተቻላቸው መጠን ለመርዳት ያላቸው እምነት ነው፤ ለዚህ እምነታቸው ብዙ የተለያዩ ምክንያቶች አሉ፤ እንዲያው በደፈናው ትግልን ከመደገፍ  ጀምሮ እስከ ሃይማኖት ድረስ የነፃነት ታጋዮች ነን- ባዮችን የሚረዱበት  ምክንያት ያገኛሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

እሪ ይበል ወንዙ፤ እሪ ይበል ሃይቁ!

ከዓለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ)

ከሶስት ዓመታት ቀደም ብሎ ‹‹እሪ በልልኝ ሃይቁ፤ በተፈጥሮ ላይ የተፈጸመ ወንጀል››በሚል ርዕስ ሳምንታዊ መጣጥፍ አቅርቤ ነበር፡፡ የዚያን ጊዜው መጣጥፌ ያተኮረው በወቅቱ ከአዲስ አበባ በስተ ደቡብ ላይ በ50 ኪሎሜትር ርቀት የሚገኘውና በአንድ ወቅት በጠቃሚ ወንዝነቱ ይታወቅ የነበረውን አሁን ለብክለት የተዳረገውን የቆቃን ሃይቅ ውሃ በመጠጣት፤ለበሽታና ለሞት የተጋለጡትን በአሰርት ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ሕለፈት በተመለከተ ነበር፡፡ ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሲኖዶሱ እና መጅሊሱ የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ማጥመቂያ?

በተመስገን ደሳለኝ

ጳጳሳት፣ ካህናት፣ ቀሳውስት፣ ዲያቆናት፣ ሼህ፣ ኢማም፣ ኡላማ፣ ደረሳ፣ ፓስተር፣ ዘማሪ፣ ካድሬ፣ ጠርናፊ፣ ተጠርናፊ፣ ሊግ፣ ማህበር፣ ፎረም፣ ግንባር ቀደም አርሶአደር፣ ልማታዊ ባለሀብት፣ ልማታዊ ጋዜጠኛ፣ ልማታዊ አርቲስት፣ ልማታዊ ማስታወቂያ ሰራተኛ፣ ልማታዊ እድር፣ ልማታዊ ማሀበር፣ ልማታዊማን ቀረ? ማንም። እናም በዛሬ ጊዜ እመንም አትመንም የእነዚህ ሁሉ ምንጭ መለስ እና ኢህአዴግ ናቸው። በተቀረ የእምነት/ሀይማኖት መገኛ ቤተክርስቲያን እና መስጊድ መሆናቸው ከቀረ ዘመን አልፎበታል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

በድን ሬሣ የሚዘርፍ አረመኔ መንግሥት

ነፃነት ዘገዬ

አንዱ ወዳጄ እንዲህ አለኝ … “ጋሽ ነፃነት፣ ኑሮየን አንተም ታውቀዋለህ። ምኑን እነግርሃለሁ? አሁንስ ምርር ብሎኛል። የት አባቴን ልሂድ? እንደቆራጦቹ በሰውነቴ ላይ ላምባ አርከፍክፌ ልቃጠል ወይንስ ከአንዱ ፎቅ ወጥቼ ቁልቁል ልፈጥፈጥ? በገመድ ልታነቅ ወይንስ የዐይጥ መርዝ ልጠጣ? ዥው ባለ ገደል ልከስከስ ወይንስ እባቡሩ መንገድ አስፋልቱ ላይ ገብቼ በሚበር መኪና ልዳጥ? ምን ልሁን? እስኪ ፍረደኝ!

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ