በሲያትል የኢትዮጵያውያን ፎረም ይመሰረታል

ሰውለሰው (ግንቦት 2003 ዓ.ም) This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. 

አቶ መለስ ዜናዊ ”የብልህነቱ” ጥግ አማራንና ኦሮሞን መከፋፈሉ ነው ይባልለታል። ይህ እንዴት ብልህ ሊያሰኝ እንደሚችል አቶ መለስ ዜናዊ ብቻ ያውቃል። እነዚህ ሁለቱ ትላልቅ ብሔረሰቦች በጠላትነት ተፋርጀው እርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ባይገቡለትም ተባብረው እንዳይቆሙ ለማድረግ በብርቱ ሠርቷል። አቶ መለስ ግድ የለውም፤ ወደ ጎንደር ጎራ ካለ ”ኦሮሞ ሊበላህ እየመጣ ነው” ብሎ በአደባባይ ለመናገር በሰማይ ያለውን እግዜርን አይፈራም። እግር ጥሎት ወደ ወለጋ ብቅ ካለ ደግሞ ”ነፍጠኛ አማራ ሊያጠፋህ እየመጣ ነውና ተጠንቀቅ!” ማለቱን አይረሳውም። እንዲህ በሰው ልጆች መካከል ጥርጣሬንና አለመተማመንን ሲዘራ የሚኖርን ሰው አጃቢዎቹ በምን መለኪያ ”ብልሁ” መሪ እያለ እንደሚያሞካሹት ስናስብ እንገረማለን።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ታክሲዎች ስራ ማቆም አድማ እንድምታ

እስክንድር ነጋ (አዲስ አባባ)

አስኮ፣ ላፍቶ፣ ለቡ፣ አያት ፣ ሲ.ኤም.ሲ፣ ዓለም ባንክ፣ ቀራንዮ፣ ኮተቤ፣ ቃሊቲ… የማለዳ ታክሲ ለወትሮውም መከራ ነው። ግፊያው የድብድብ ያህል ነው። ትላንት ሰኖ ግምቦት 8/2003 ግን ፣ ተጋፍቶ የሚገባበት ታክሲ የጠፋው ገና ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ነበር። የአንድ አዓቱን ግፊያ እየሸሸ ቀደም ብሎ ከቤቱ የሚወጣው የከተማው ነዋሪ ታክሲዎች ምር አድማ መተዋል ብሎ መጠርጠር የጀመረው የወትሮ ደምበኞቹ የውሃ ሽታ ሆነው ሲቀሩበት ነበር። የቻለ እንደ ሰርዲን በሞጠቀጠቁት አውቶቢሶች ላይ እንደምንም ተሰጉጦ አመለጠ። ከፊሉ በእግሩ አስነካው። እድለኛው የቤት መኪና እየተባበረው በምቾት ወደ መሀል ከተማ ዘለቀ። ብዙዎች ከስራና ከትምህርት ቀርተው ወደቤታቸው ተመለሱ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ይድረስ ለውድ እናቴ (አስራደው)

አስራደው ከፈረንሳይ

ውድ እናቴ! ቀደምት የተባረኩ ልጆችሽ የአንቸቸ የእናታችንን ድንበር በደማቸው አጥረው ነጻነትሽን አስከብረውና ተላት አሳፍረውአልፈዋል፤ ታዲያ ለዚህ ውለታቸው ካንቺ የእናት ፍቅር ሌላ የጠየቁት ልዩ ውለታ አልነበረም። ... (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!)

ትብብር ከማን ጋር? አላማውና ልዕለ-ግቡስ? (አያልሰው ደሴ)

አያልሰው ደሴ

ወደነጥቦቹ ከመሄዳችን በፊት ግን እስካሁን "የኢትዮጵያ ጉዳይ አያገባንም፣ ትግላችን ኢትዮጵያ ከምትባል 'ቅኝ ገዥ' ጋር ስለሆነ ከኢትዮጵያዊያን ጋር የሚያሰልፈን ምክንያት የለም" በሚል አቋማቸው ከሚታወቁትና በአሁኑ ጊዜ "ትብብር" ፈጣሪ ስለሆኑትድርጅቶች ባአጭሩ ማየቱ ተገቢ ይመስለኛል። ... (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!)

የአባይን ግድብ መገንባት እንችላለን!

ግርማ ካሣ

በአገር ውስጥም ሆነ ከአገር ውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን በሰፊው እያነጋገረ ያለው ጉዳይ ቢኖር በቅርቡ የኢሕአዴግ መንግሥት ይፋ ያደረገው የአባይ ግድብ ፕሮጀክት ነው። አቶ መለስ ዜናዊ ምንም እንኳን የውጭ አገር መንግሥታትና ድርጅቶች እርዳታቸውን ለመዘርጋት ፍቃደኛ ባይሆኑም፣ ሰማኒያ ሚሊዮን የሚሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ በራሱ ገንዘብ ግድቡን መስራት እንደሚችል፣ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

“መናድ” የሚለው ቃል በዶ/ር ነገደና በአቶ መለስ በተግባር ሲፈተን

አሸብር ከጀርመን This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

“መናድ” የሚለው ቃል “ና” ላልቶና ጠብቆ ሲነበብ የተለያየ ትርጉም አለው። ጠብቆ ሲነበብ ተደራጊነትን ሲያመለክት፤ ላልቶ ሲነበብ ደግሞ አድራጊነትን ያመለክታል። ለምሳሌ በቅርቡ ዶ/ር ነገደ “መናድ” ያለበት ሕገ-መንግሥት …” ሲሉ የተጠቀሙበት “መናድ”ን “ና”ን አጥብቆ በማንበብ ነው። እሱን በኢትዮ-ሚዲያ፣ በኤካዴፍ፣ … እንዲሁም ሌሎች ድረ-ገጾች ላይ ወጥቷል። (ጽሑፉን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ!)። አቶ መለስ ደግሞ አላልቶ በማንበብ እንዴት እንደተጠቀሙበት እንይ። 

ሠላማዊ ትግል ሞተ ወይስ የኛ ወኔ ተበጠሰ? (ያሬድ አይቼህ)

ያሬድ አይቼህ

የኢትዮጵያ አገራዊ ፖለቲካ ላይ ገንቢና ጠቃሚ ተጽዕኖ ለማድረግ ከዲያስፖራ የሚደረገው ጥረትና ትግል ከምርጫ 2002 ማግስት ጀምሮ አቅጣጫው ተሰበጣጥሯል። በተለይ ሠላማዊ እና ህጋዊ ትግል ላይ እኔ ተስፋ ስላደረኩ፤ ከኢህአዴግ 99.6% ወንበር ማግበስበስ በኋላ የኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ሂደት በጣም ጭጋጋማ፤ ጨለማ፤ ድንግዝግዝና ተስፋ አስቆራጭ ሆኖብኝ ነበር። ሙሉውን አስነብበኝ ...

እንዴት ይብቃ? (አንተነህ መርዕድ)

አንተነህ መርዕድ

በቃ! ገዬ! ያክል! አሎኒ! ዲታህ! ወጣንድም! በስ! ጊደስ!

በቃ የሚለው ቃል ሀገር ውስጥና ውጭ በምንገኝ ለውጥ ፈላጊ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ጎልቶ የሚነገር ክቡር ቃል ሆኗል። በዚህ ሰፊ ጽንሰ ሃሳብ በያዘ ቃል ዙርያ በመንቀሳቀስ ተጨባጭ ኃይል ፈጥሮ ዘላቂ ለውጥ ለማምጣት የ”በቃ!”ን መልዕክት በሚገባ መረዳትን ይጠይቃል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

“ሶስተኛው ሪፐብሊክ” የቶሮንቶ ስብሰባና የኢትዮጵያ መጪው ዘመን (ክፍል አንድ)

ልጅ ተከሌ (ኦታዋ - ካናዳ)

ቦታው ኤድመንተን ውስጥ ነው። ስብሰባው የኦጋዴን ማህበረሰብ ስብሰባ። ተናጋሪው ኦባንግ ሜቶ። የምስራቅ ጫፍና የምእራብ ጫፍ ወግ። ሰሜንና ማእከሉ መነጋገርና መግባባት በተሳናቸው ግዜ፡ የምእራቡ ኢትዮጵያዊ የምስራቁን ኢትዮጵያ ሲያግባባውና ሲሸመግለው። “እኛ ኢትዮጵያዊያን” ብሎ ጀመረ ኦባንግ። እኛ ኢትዮጵያዊያን ብሎ ሲጨርስ፡ በመካከል ግን አንዲት የኦጋዴን ሴት ተነሳችና “who the hell are you to tell me that I am an Ethiopian? I am not Ethiopian. You have to apologize for calling me an Ethiopian” አለችው። ወረደችበት። ወደ አራት መቶ የሚጠጉ የኦጋዴን ተወላጆችና ሌሎች ኢትዮጵያዊያን አዳራሹን ሞልተውታል። ኦባንግ አልደነገጠም። እንዲህ ያለውን ጥያቄና ፍጥጫ ለምዶታል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አሳማ ቢን ላደን ማን ነው? (ዳንኤል ገዛኸኝ)

ዳንኤል ገዛኸኝ

የኒውዮርኩ መንትያ ህንጻዎች የሽብር ጥቃት ጠንሳሽ (ማስተር ማይንድ) ኦሳማ መሃመድ ቢን ላዲን በእለተ ሰንበት እሁድ ሌሊት ነው ከፓኪስታን ዋና ከተማ አቦታባድ በ61 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትጘኘው የምቾት ከተማ ሜይ 1 ቀን 2011 ዓ.ም መገደሉ በአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ሁሴን ኦባማ የተገለጠው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...