የኢትዮጵያ ሕዝብ...ከዚህ ወዴት? ክፍል 23 (አያልሰው ደሴ)

ሐ - ከፖሊስ፣ ከጸጥታና ከጦር ኃይል ክፍሎች ጋር የሚገናኝ አንድ የደህንነትና የመረጋጋት ጉዳይ የጋራ አካል ማቋቋም

መ-የአገዛዙን ግትርነትና መሰሪያዊ ባህሪ ባገናዘበ ሁኔታ በግልጽ መመሪያከገዥው ፓርቲና መንግስት እንዲሁም ከሌሎች ድርጅቶች ጋር የሚደራደር አንድ ተደራዳሪ የጋራ አካል በማቋቋም መርህን ያለቀቀና የህዝብን ፍላጎት የሚያንጸብርቅ ድርድር እንዲደረግና ይዘቱንም ህዝብ እያወቀው እንዲሆን ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ በዚህም ረገድ የተጠናከረ የጋራ እንቅስቃሴ እንዲደረግ ጥረት አድርጓል።  (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ)

ሦስቱ ጳውሎሶች (ሕብረት ሠላሙ)

ሕብረት ሠላሙ

በኢትዮጵያውያን የታወቁ፤ ሶስት ጳውሎሶች አሉ። ዋነኛው፤ የኢየሱስ ክርስቶስ ባለሙዋል፤ ዝነኛው፤ ተአምረኛው፤ ሰማእቱ፤ ድንቅ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ነው። ሁለተኛው፤ ሰሞኑን በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን "ብሩክ" በመሰኘት የተወደሱት፤ ፖፕ ጳውሎስ ሲሆኑ ሶስተኛው ደግሞ የኛው፤ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን መሪ፤ አቡነ ጳውሎስ ናቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአቶ መለስ ዜናዊ ዘፈኖች - የጽንስ ማምከኛ ክኒኖች ናቸው

ተሻገር በላይ (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.)

አቶ መለስ ዘፋኝ ወይም የሙዚቃ ሰው ባለመሆናቸው የጽሑፉን ርዕስ ስታዩ ትገረሙ ይሆናል። ነገሩ እንዲህ ነው። ሰው ሲደሰት ብቻ ሳይሆን ሲፈራ ወይም ብቸኝነት ሲሰማው ያቅራራል፣ ይፎክራል፣ ይዘፍናል። ይህን ሲያደርግም የሌሎችን ልቦና (attention) ይስባል። ለራሱም የተሻለ ስሜት ይሰማዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ነፃነት ከገንዘብ በላይ ናት (ይነጋል በላቸው)

ይነጋል በላቸው (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.)

አንጀትን ሰርስሮ የሚገባ ግሩም አባባል። በርዕሴ ላይ የተመለከተውን ወርቃማ ንግግር የተናገረው ከደቂቃዎች በፊት ዚንታን በምትባል የምዕራብ ሊቢያ ትንሽ ከተማ ውስጥ አኒታ በምትባል የነውጠኛው አልጀዚራ ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ የተጠየቀው አንድ በሙያዉ መሃንዲስ አሁን ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ተገድዶ ግን የነፃነት ታጋይ ወታደር የሆነው መሀመድ የሚባል ሰው ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከፔንሲልቫኒያ እስከ ኦንቴሪዮ - ኢሳትና እሳት በኦታዋ

ተክለሚካኤል አበበ (ኦታዋ-ካናዳ)

በረራው ተሰረዘ፡ እኛም ተደናገጥን

የዩኤስ አየር መንገድ ስልከኛ ሰው ደውሎ ያስቀመጠውን “የበረራ መስመር 7744 ስለተሰረዘ በሚከተለው ስልክ ቁጥር ደውሉና ማስተካከያ አድርጉ” የሚለውን መልእክትስሰማ ክው አልኩኝ። ለበረራው የቀረው ከሶስት ሰዓት ያነሰ ነው። ዲባቶ ብርሀኑ ነጋ ከተማሪዎቹ ጋር ያለውን ጣጣ ጠቅለል አድርጎ ወደጥያራ ጣቢያ ለመንዳት የሚያሟሙቅበት ሰዓት ነው። የዚያን ቀን ከሰዓት በኋላ የማስረክበውን ወረቀት ለመጨረስ ደፋ ቀና ስል ስልክ ጥሪዎች እንዳይረብሹኝ ብየ ስልኬን አጥፍቼው ስለነበር፡መልእክቶቼን ለመስማት ስከፍተው ዘግይቼ ነው ያንን የ “በረራ ተሰርዟል” መልእክት የሰማሁት። ተረበሽን።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የመለስ "ጠንካራ" ጎን

ተስፋዬ ገብረአብ

መለስም ቢሆን ሥልጣኑን እግዚአብሔር እንዳልሰጠው አሳምሮ ያውቃል። ለሥልጣን የአቃው በጭንቅላቱ ተጠቅሞ እንደሆነ ስለሚያምን፣ ሥልጣኑን ሳያስነካ ለማስጠበቅ የቤት ሥራውን ተግቶ ከመሥራት ቦዘዝኖ አያውቅም። በመሰረቱ መለስ በእግዚአብሔር መኖር አያምንም። ስለዚህ "ሰው መግደል ሀጢያት ነው" ብሎ ሊያስብ አይችልም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢትዮጵያ ህዝብ... ወዴት? ክፍል 22 (አያልሰው ደሴ)

ህብረቱ ድህረ-ምርጫ ትኩረት አድርጎ ከተንቀሳቀሰባቸው የትግል ዘርፎች አንዱ የዲፕሎማሲው ክፍል ነነበር። ተቃዋሚው ክፍል በዲፕሎማሲው መስክ የሚያደርገው ትግል የተቀነባበረና አንድ ወጥ እንዲሆን ማድረጉ አስፈላጊ በመሆኑ ቅንጅቱና ህብረቱ አንድ የጋራ አካል አቋቁመው እንዲሰሩ ጥረት የተደረገ ቢሆንም ህብረቱ ብቃቱና ችሎታው ያላቸው አባላትን ያቀፈ አንድ ልዩ አካል (ኮሚቴ) አቋቁሞ ተንቀሳቅሷል። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ)

አባይና የሰሞኑ ግርግር

መስፍን አማን

መቼም የአባይን መገደብ የሚቃወም ሀገሩን የሚወድ ኢትዮጵያዊ ያለ አይመስለኝም። ለሀገራችን መልካም እናስባለን የሚሉ ሀገር ወዳድ ኃይሎች በጉዳዩ ላይ ያላቸው ተቆርቋሪነት ከወያኔ መሪዎች ቢበልጥ እንጂ የሚያንስ አይደለም። ሁላችንም ቀን ወጥቶ በጋራና በመግባባት ሀገራችን የሀብቷ ተጠቃሚ ሆና ከማየት የበለጠ ሌላ ትልቅ ምኞት የለንም። እንደውም ብቸኛው አብዩ ምኞታችን ያ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አፍቃሪ ብርቱካኖችና ተናዳፊ ንቦች (ሙሉነህ ዮሐንስ)

ሙሉነህ ዮሐንስ (ከሲያትል)

ለስምንት ወራት ሙሉ በዝናብ ሲንዠቀዠቅ የነበረው የሲያትል ሰማይ ዳመናውን እየገለጠ በጉጉት ለምትጠበቀው አጭር የበጋ ፀሐይ የተመቻቸ ይመስላል። እኔም ጨቅላዋ ልጄን ከውድ ባለቤቴ ጋር ሆኜ ፀሐይ ለማሞቅ ባለኝ ጉጉት ጀንበር ሳትጠልቅ ወደቤቴ ለመድረስ የመኪና ወፈ ሰማይ ከወረረው የኢንተር ስቴት 5 ሀገር አቋራጭ አውራ ጎዳና ውስጥ እንደተዋጥኩ የእጅ ስልኬ አቃጨለች።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አቤት ውሸት! አቤት ውሸት! (ወንድሙ መኰንን)

ወንድሙ መኰንን (ሎንደን መጋቢት 2003 ዓ.ም.)

ወያኔ የውሸት ቋት ነው። የወያኔ ውሸት ስልችት ያለው ኢትዮጵያዊ በእብለቱ ዙሪያ ቀልድ እየቀለደ የባዶ ሆዱን በሳቅ ያስታግሳል። አንዱ ቀልድ የ42 ኢንቸ ጠፍጣፋ ቴሌቭዥን ወያኔ በዋሸ ቁጥር እየተሸማቀቀ እየተሸማቀቀ ተኮራምቶ ወደ አንዲት ብልጭ፣ ድርግም የምትል 15 ኢንች መለወጡ ነው። ምን ወያኔ ያልዋሸው አለ? ከሻዕቢያ ጋር አብሮ የወጋ እኮ ነው! ምነው ቢባል፣ ”ደርግን አስወግጄ ዴሞክራሲ ላመጣ ነው” አለን። አቤት ውሸት! አቤት ውሸት! ድንቄም ዴሞክራሲ! አሁንም አፈናው ከደርግ የበለጠ እንጂ፣ ያነሰ አለመሆኑን እንደነቃንበት ያውቅ ይሆን?!

ሙሉውን አስነብበኝ ...