... ከዚኽ ወዴት? (ክፍል ስምንት - አያልሰው ደሴ)

የኢትዮጵያ ህዝብ፣ አገር-ወዳድና ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች እና ኢህአዴግ፤ ከዚኽ ወዴት? ክፍል ስምንት

አያልሰው ደሴ (የግል አስተያየት)

በውሳኔው መሠረት ጉባዔ አዘጋጁ ክፍል ስለዚህ ሀገር አቀፍ ጉባዔ ዓላማና አስፈላጊነት በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ለኢትዮጵያውያንና ለዓለም አቀፍ ኅብረተሰብ በጥናት ላይ የተመሠረቱ ቅስቀሳዎችና ገለፃዎችን አድርጓል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በኢትዮጵያ ስለሀገር መፀለይም ያስወነጅላል

ይሄይስ አዕምሮ

በቅድሚያ ውድ ልጃችንና እህታችን ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ከጠባቡ እስር ቤት ወጥታ ወደ ሰፊው እስር ቤት እኛው ዘንድ በመቀላቀልዋ የተሰማኝን ደስት በዚች አጋጣሚ እንድገልጽ ይፈቀድልኝ። እንኳን ደስ ያለን! ... መፈታትዋ ትልቅ ነገር መሆኑ እንዳለ ሆኖ ትግሉ ተጀመረ እንጂ ገና እልባት ስላላገኘ በመለስተኛ ደስታ ዋንውን ድል እንደማንዘነጋ ሁሉአችን ይንጋራው እምነት መሆኑን እረዳለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ እንሆ መሪህ

ግርማ ካሣ

ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ልትፍታ እንደምትችል ከአንዳንድ ምንጮች አንዳንድ ፍንጮች ያገነሁት ከአንድ ሳምንት በፊት ነበር። እንደዚያም ሆኖ ግን ያለፈው ዓመት አዲስ ዓመት መግቢያ አካባቢ ትፈታለች የሚል ወሬ ተወርቶ ስላልተፈታች፣ በዚህ ዓመትም ሙሉ ለሙሉ ትፈታለች የሚል ተስፋ በልቤ አልነበረም። በእርግጠኝነት እንደምትፈታ ድረ ገጾች ማክሰኞ መስከረም 26 ቀን 2002 ዓ.ም ዘገባ እስኪያወጡ ድረስ፣ በአይምሮዬ ውስጥ ጥያቄው ”መቼ ይሆን ነው የምትፈታው? ” የሚለው ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዳዊትና ጎልያድ፣ ብርቱካንና መለስ - ፍቅርና ወንጭፍ

አትክልት አሰፋ - ከቫንኩቨር (ካናዳ)

“አይ.. ኢትዮጵያ ሀገሬ… ሰው አጣች ” አለ አንድ የቅርብ ወዳጄ። በዚያ በቅንጅት ዘመን እዚህ ግባ የማይባሉ ግለሰቦች፤ የኢትዮጵያዊነት መታወቂያ ካርድ ሰጭና ነሽ ሆነውበት አንጀቱ አሮ። ታዲያ ጊዜ አልፎ ጊዜ ተተካና ዛሬ መጣ። ከርሞ ይመጣና ዛሬም ድሮ ይሆናል። ክፋቱ ሰው ቆሞ ይቀራል እንጂ ጊዜውስ ይበራል። የጎልያድና የዳዊት የብርቱካንና የመለስ ፍልሚያስ ከተጀመረ ሁለት አመት ሞላው አይደል?።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢትዮጵያ ህዝብ፤ ... ከዚኽ ወዴት? (ክፍል ሰባት - አያልሰው ደሴ)

የኢትዮጵያ ህዝብ፣ አገር-ወዳድና ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች እና ኢህአዴግ፤ ከዚኽ ወዴት? ክፍል ሰባት

አያልሰው ደሴ (የግል አስተያየት)

... ኢዴኃቅ አዲሱ የኢህአዴግ መሪዎች በሀገራችን ላይ የተከተሉትንና ሥራዬ ብለው የተያያዙትን የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ ቅኝቶች አደገኝነት ጠንቅቆ የተረዳ በመሆኑ እነኛ አደገኛ ውጥኖች በተግባር እንዳይተረጎሙ ከጥንስሱ ጀምሮ በተቻለው መንገድ ሁሉ አምርሮ ታግሏል። ሆኖም በተጠቀሱት ዋና ዋና ምክንያቶች እነኝህን አደጋዎች ማስቀረት ቀርቶ ማዘግየት አልተቻለውም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

መልስ ለልጅ ተክሌ "ለነገሩ ለብርቱካንም ለእኛም መታሰሯ ይበጀናል" ፀሐፊ

ገራዶ

የልጅ ተክሌን ጽሑፍ እንደ ወትሮው ሁሉ ዛሬም አነበብኩት። እንደ ወትሮው ሁሉ ዛሬም ተቃወምኩት። በጽሑፉ ውስጥ እንደ ወትሮው ሁሉ ስሜት ከምክንያት ልቆ አየሁበት። ብዙ የመጻፊያ ሰዓት ስለሌለኝ ጽሑፌን ያለመግቢያና ሀተታ በመደምደሚያ ብቻ አጠር አድርጌ እቋጫለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በሳውዲ ዐረቢያ የኢትዮጵያውያን መከራ (ክፍል ሦስት)

በሳውዲ ዐረቢያ የኢትዮጵያውያን መከራ - የተደበቁ እውነቶች!

እስር ቤት ሰበራ!

ክፍል ሦስት

ነቢዩ ሲራክ - ከሳውዲ ዐረቢያ

የረመዳን ዋዜማን ተንተርሸ ከክፍል አንድ ሁለት ያደረስኩትን ቀጣይ መጣጥፍ ሰፋ አድርጌ ለማስቃኘት ያያዝኩትን ዕቅድ የሚያሰናክል አጋጣሚ ተፈጥሯል። ምሽት ላይ ተርሂል ተብሎ ከሚጠራው የጅዳ ጊዜያዊ እስር ቤት ያገኙሁት የስልክ መልእክት ያላሰብኩት የአካሄድ ለውጥ ጠቋሚ ነበር! የተርሂል እስር ቤትን መከራ ሁለንተናዊ ገጽታና የወንድም እህቶቸን መከራ በቀጣይነት ላነሳው የነበረ ጉዳይ ቢሆንም ዛሬ አነሳው ዘንድ ተገደጃለሁ። ታሳሪዎች እጂግ ተማርረዋል። ሁኔታው መልኩን እየቀየረ መመጣቱን ከሚሰጡት የምሬትና የተስፋ መቁረጥ ቃላት መገመት ይቻላል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የትራንስፎርሜሽኑ መዘዝ

ይሄይስ አዕምሮ (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.)

በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያን ለዘመናት ጨንፍሮ ከያዛት ድህነት ለማላቀቅ የኢህአዴግ መንግሥት የትራንስፎርሜሽን ዐዋጅ በቅርቡ ማወጁ የሚታወቅ ነው። ጥሩ መመኘት ጥሩ ነው። ዐዋጁ እንደስካሁኖቹ የግብር ይውጣና የማሞኛ ዐዋጆች ሆኖ የማይቀር ከሆነ ሀገርና ህዝብ ለሽዎች ዓመታት ተዘፍቀውበት ከነበሩበት የድህነት አዘቅትና የችግር አዙሪት መውጣታቸው ከሰይጣን በስተቀር የማያስደስተው ስለሌለ ሁላችንንም እሰየው የሚያሰኝ ዕፁብ ድንቅ ነገር ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ለነገሩ ለብርቱካንም ለኛም መታሰሯ ይበጀናል

አለቃ ተክሌ - ከቫንኩቨር-ኦታዋ (ካናዳ)

አንዳንድ ሰዎች፤ እንዲሁም ቤተሰብ

እናቷ እንኩዋን፡ መቼም የናት አንጀት ነውና፡ ትፈታልኝ እንጂ፡ እንኳን ታሰረች ሊሉ አይችሉም። አንዳንድ ሰዎች ግን፡ በግልም ባደባባይም ከብርቱካን ጋር በተያያዘ የሚያሰሙት ከንፈር መምጠጥና፡ አይ “ይህቺ ሴት ተጎዳች” ንግግር ስህተት ነው ብዬ ነው ሀተታዬን የምጀምረው፡ ዛሬ። ብርቱካን ለመረጠችው የፖለቲካ ሕይወት ነው የታሰረችው። አንድ እንዳይኑ ብሌን የሚሳሳልኝ ጓዴ፡ እባክህ ወዳጄ ተክሌ “እኔ እኔ” እያልክ አትጻፍ፡ እኔ አንተን ከትችት መከላከል ሰልችቶኛልና ብሎ ቢመክረኝም፡ ዛሬም እኔ እያልኩ ነው የምጽፈው። እነሆ እንደኔ እንደኔ፡ ብርቱካን፡ የወጣላት፡ በሳልና፡ የበቃች መሪ እንድትሆን፡ በእስርና በእንግልት መፈተን አለባት።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ስለወ/ት ብርቱካን ጠ/ሚ መለስ የማይደፍሩት ሐቅ

PM Meles Zenawiሠላማዊት

ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ በአሜሪካው ኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው ስለወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ሲጠየቁ በየመድረኩ ከሚለዋወጡት ምላሽ አንዱን መለሱ። ”ይቅርታ አልጠየኩም የሚል ሰው በሕጋችን መሠረት ይቅርታው ተነስቶ ውሳኔው ተፈፃሚ ይሆናል አሉ” (ቃል በቃል ስለመጥቀሴ ርግጠኛ አይደለሁም)። የትኛው ሕግ ይህን እንደሚል ግን አንቀጽ ጠቅሰው ማስረዳት አይችሉም። እንዲህ የሚል ድንጋጌ የያዘ አዋጅም ሆነ ደንብ የለም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...