የመለስ ቀልዶች

ተስፋዬ ገብረአብ

ወያኔ ጉባዔውን አዳማ ላይ አካሄደ።

እናም ጉባዔው በአትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ ንግግር ተቋጨ። አቶ መለስ ዜናዊም በኃይሌ ንግግር ሲስቅ በቴሌቭዥን ተመለከትነው። አቶ መለስ ዜናዊ፣ “በአምስት ዓመታት አጠናቅቀዋለሁ” ያለውን ትንግርታዊ፣ አስማታዊና ሰማያዊ የልማት ዕቅድ ዶክተር ኃይሌ ከአቶ መለስ ብሶ፣ “በሁለት ዓመታት እንጨርሰዋለን” ሲል ቃል ገባ። አያይዞም አትሌት ኃይሌ፣ “ስለ ሰከንድ ማሰብ አለብን” ሲል ተናገረ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጯኺ መፈክሮች እና ውጤቶቻቸው

ታደሰ ብሩ

መግቢያ

“የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የግብርናም የኢንዱስትሪም ሳይሆን የመፈክር ኢኮኖሚ” ነው እያልኩ ስቀልድ ኖሬአለሁ። አሁን አሁን ግን ምፀቱና ቀልዱ ቀርቶ የምር “የመፈክር ኢኮኖሚ የሚባል ነገር ይኖር ይሆን?” እያልኩ ማሰላሰል ጀምሬአለሁ። ይኸ ጉዳይ በአንድ ጋዜጣ በቀልድ መልክ መነሳቱ ነገሩ ሌሎችንም ሰዎች እያሳሰበ መሆኑን ተረድቻለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ድርጅታዊ መበስበስ፣ ጥገኝነት እና አድርባይነትን መዋጋት ያቃተው የኢህአዴግ የ”መተካካት” ድራማ

በአህመድ አባጊሣ

ልባቸውን የናጠ ግን እንደ እባብ ያስቀጠቀጣቸው ግጥም

በውቧ የባህር ዳር ከተማ ቀደም ባለው እና አስከፊውን የደርግ ሥርዓት መንግሎ ለመጣል በተደረገው እልህ አስጨራሽ ትግል ግንባር ቀደም ሚና ስለተጫወቱ እንደ ሙሉዓለም እጅጉ ያሉ ታጋዮች በአንድ አለብላቢ ምላስ ባለው ካድሬ አማካይነት የሰሙት ግጥም ደስ ብሏቸዋል - ወደ 1200 የሚጠጉ በከተማዋ በሚገኘው የተንጣለለው የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመሰብሰቢያ አዳራሽ የታደሙ የንቅናቄው አባላት።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ብርቱካን ሚደቅሳ ከነማንዴላና አን ሳንሱኪ ምድብ ልትገባ ነው

ግርማ ካሣ (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.)

ሐምሌ 27 ቀን 1981 ዓ.ም. ነበር። በአደባባዩ የሰፈረው በመቶ ሺ የሚቆጠር ሕዝብ የተለያዩ መፈክሮችን ይዞ ”እምቢ አምባገነንነትን! እምቢ የአንድ ፓርቲ ሥርዓትን! እምቢ የሰብዓዊ መብት ረገጣን” እያለ ይጮሃል። ታንኮችንና መትረየሶች የተደቀኑባቸው የወታደር መኪናዎችን በማሰማራት፣ የአገሪቱ 27ኛው ክፍለ ጦር ህዝቡን ከቧል። ታንኩ እየቀረበ መጣ። አንድ ወጣት ከታንኩ ፊት ቆመ። ታንኩ ጨፍልቆት አለፈ። ድንገትም ተኩስ ተጀመረ። መሳሪያ በታጠቁ በአገራቸው ሰዎች በተተኮሰ ጥይት በሺሆች የሚቆጠሩ ወደቁ። የሰው ልጆች ደም እንደ ጎርፍ ፈሰሰ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ይድረስ ለዕጩ ’ጠቅላይ ሚንስትራችን’ ኃይሌ ገ/ሥላሴ (ነፃነት ዘገዬ)

ነፃነት ዘገዬ

የኢትዮጵያን ወቅታዊ ጉዳይ ይሁነኝ ብሎ ለሚከታተል የውስጥም ሆነ የውጭ ታዛቢ በየዕለቱ አዳዲስ አስገራሚ ነገር አያጣም። ”ቀን የሰጠው ቅል ...” እንዲሉ ጊዜ የሰጠው ሞልፋጣ ሁሉ ባልተገራ ስድ አንደበቱ ህዝብን ባገኘው አጋጣሚና መድረክ እየተነሳ ሲሳደብ መስማት ደግሞ የዘመናችን ፍሽን ሆኖ ከመገኘቱም በላይ ይህ በአሳዛኝነቱ ከሁሉም የሚበልጥ ሀገራዊ ጉዳይ ’ሃይ’ የሚለው ማጣቱ ይበልጥ ያስገርማል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በሳውዲ ዐረቢያ የኢትዮጵያውያን መከራ (ክፍል ሁለት)

በሳውዲ ዐረቢያ የኢትዮጵያውያን መከራ - የተደበቁ እውነቶች - በረመዳን ዋዜማ (ክፍል ሁለት)

ነቢዩ ሲራክ - ከሳውዲ ዐረቢያ

ረመዳን ለመግባት የቀሩት ጥቂት ቀናት ናቸው። በመጀመሪያ ክፍል መጣጥፌ እየተውተረተርኩ ለማስረዳት እንደሞከርኩት "የዐረብ ሀገር ኑሮ መረረን! ኑሮ አንገሸገሸን በቃን! ወደ ሀገራችን እንገባ!?" በሚል በፖሊስ ለመያዝ ድልድይ ስለወደቁት ወገኖችና በሳውዲ ስለ ረመዳንን አቀባበል ሽር ጉድ የታዘብኩትን ለማሳየት ሞክሬያለሁ። አብዛኛው እህቶችና ጥቂት ወንድሞቸ ከተኮለኮሉበት ድልድይ ስር በደረሰባቸው የወረበላ ወከባ፤ መደብደብና መደፈር ተማርረው ጂዳ ወደ ሚገኘው ቆንስል መስሪያ ቤት ቢያቀኑም ምላሽ አለማግኘታቸውን ለማስቃኘት መዳዳቴን አትረሱትም። በአምስት ቀን ቆይታቸውን ካየሁትና ከግፉዓኑ የሰማሁትን የምስክርነት ቃል ላጋራችሁም ሞክሬያለሁ። ማንበብ እንዳላሰለቻችሁ በሚል የመጣጥፌን ሃሳቦች ሰብሰብ ለማድረግ በግርድፍ በግርድፉ ለማስቀመጥ ስሞክር አልፎ አልፎም ቢሆን የዓረፍተ ነገር መጣረስ የፊደል ግድፈት አልጠፋም። ለዚህም ይቅርታ ጠይቄ ወደ ዛሬ ወጋ ወጌ ላቅና ...

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በሳውዲ ዐረቢያ የኢትዮጵያውያን መከራ (ክፍል አንድ)

በሳውዲ ዐረቢያ የምንገኝ ግፉአን ኢትዮጵያውያን መከራ - በረመዳን ዋዜማ (ክፍል አንድ)

ነቢዩ ሲራክ - ከሳውዲ ዐረቢያ

... በመቶዎች የሚቆጠሩ የመናውያን፣ ኢትዮጵያውያን፣ ሶማሌያውያንና ኤርትራውያን ስደተኞች አደገኛውን የቀይ ባህር በትናንሽ ጀልባዎች ታጭቀው የጨካኝ አሸጋጋሪ ደላሎችን ግፍ የተሞላበት እርምጃ በመቋቋም የማይጨበጠውን ህልምን ለማሳካት ትግል ይዘዋል። አብዛኛው ወንዶች እየተደበደቡ ሴቶች እየተደፈሩ የየመንን በርሃዎች ቆርጠው ወርቅ ይታፈሳል ወደ ተባለበት የቱጃሮች ሀገር ሳውዲ ዐረቢያ ሲገቡ ይያዛሉ። ለወህኒ ከማዳረግ አልፎ በጥይት እየተደበደቡ ደመ-ከልብ ይሆናሉ። ጥቂት የቀናቸው አይሆኑ ሆነው ካሰቡት ሲደርሱ ያላለላቸው በርሃ በልቶዋቸው የመቅረቱን ትኩስ ዜና ሰምተን ሳናጣጥመው ሌላ ህሊና ሊቀበለው በማይችል ዜና መስማት ጀምረናል። በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በሳውዲ የጠረፍ ከተማ በጀዛን ድንበር ከተያዙ በኋላ በተጨናነቀው እስር ቤት አሳር መከራ እያዩ መሆናቸውን እንሰማለን። ይህንን ከተለያዩ ምንጮችና ከሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎች ማረጋገጥ ቢቻልም ሁኔታውን አሳምረው ከሚያውቁት ከመንግሥታቸን ተወካይ ባለስልጣናት ግን ማረጋገጫ ማግኘት አልተቻለም። ይህ በእንጥልጥል ላይ እንዳለ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በበኩላቸው በጂዳ የግርድና አስከፊ ኑሮ አንገፍግፏቸው ወደ ሀገራቸው የሚመልሳቸው አጥተው ለወራት በእንግልት ላይ መሆናቸውን ሰማሁ። ...

ሙሉውን አስነብበኝ ...

... ኢህአዴግ፤ ከዚኽ ወዴት? (ክፍል ስድስት - አያልሰው ደሴ)

የኢትዮጵያ ህዝብ፣ አገር-ወዳድና ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች እና ኢህአዴግ፤ ከዚኽ ወዴት? ክፍል ስድስት

አያልሰው ደሴ (የግል አስተያየት)

ሐ-፩፦ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ቅንጅት (ኢዴኃቅ) ...፣

በተጨማሪም ከዚኽ በላይ እንዳየነው ኢዴኃቅ እንደኢትዮጵያዊ ድርጅቶች ስብስብ ኢህአዴግ በኢትዮጵያ ላይ የተያያዘውን የጥፋት አቅጣጫ ለማስቀየርና ለሀገር አንድነትና ለህዝባዊ ሥርዓት እውን መሆን የሚያደርገው ትግል ሁሉ-አቀፍ እንዲሆንና የበለጠ እንዲጎለብት በማሰብ፣ በሱ (በኢዴኃቅ) ውስጥ ያልተካተቱና በሀገሪቱ ላይ ለውጥ እንዲመጣ የሚሹ ፀረ-ኢህአዴግ ኃይሎች እንዲሰባሰቡ ያልተቋረጠ ጥረት አድርጓል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

28 ቢሊዮን 469 ዶላሩ የት ገባ? 384 ቢሊዮን ብሩ ማለቴ ነው!

ሲሳይ አጌና - ከአዲስ አበባ

ቀጣዩ ቀልድ ከዚህ ጽሑፍ ይልቅ “በውሸት ደዌ ለምትሰቃዩ - እነሆ ዕውነቱ!” በሚል ርዕስ ቀደም ሲል ነኀሴ ላይ ለለቀቅኩት ጽሑፍ ይበልጥ የሚስማማ ይመስለኛል። ሆኖም ቀልዱን አንድም በወቅቱ ላስታውሰው ባለመቻሌ፤ በሌላ በኩል ይህ ጽሑፍ ምንም እንኳን በዋናነት በዓለም አቀፍ እርዳታዎች ላይ ቢያተኩርም እንደ ቀጣይ ክፍል ሊወሰድ የሚገባው በመሆኑ፤ በሦስተኛ ደረጃ ግንኙነት ባይኖረው እንኳን ቀልዱን ያልሰማችሁ ብትሰሙት ማለትም ብታነቡት ምን ጉዳት አለው? በሚል ከሱ ልጀምር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሦስተኛው መድፍ

ተስፋዬ ገብረአብ

እነሆ! “የስደተኛው ማስታወሻ” የተባለው መድፍ ተሠርቶ ተገባዶአል …

በዚህ አያያዜ ቶሎ የምጨርሰው ይመስለኛል። “ስደት” ርዕሰ ጉዳዩ ሰፊ ነው። ይፃፍ ከተባለ 20 ጥራዝም አይበቃው። ሆኖም አጀንዳዬ ከሀገራችን ፖለቲካ ሊያፈነግጥ እንደማይችል ግልፅ ነው። የአብዛኛው የስደት ምክንያቱ ፖለቲካውም አይደል? በመሆኑም ስደትና ፖለቲካውን ከወቅታዊ ጉዳዮቻችን ጋር እያዋሃድኩ እተርካለሁ። ሙሉውን አስነብበኝ ...