የፊታችን ምርጫ ቀልድ ነው፤ መድረኩ ግን መሳተፉ ይበጀዋል

ግርማ ካሣ ( This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. )

የ2002 ምርጫ ሊደረግ ከአንድ ወር በታች ቀርቶታል። ገዢው የህወሓት/ኢህአዴግ መንግሥት ”ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ እንዲሆን ለማድረግ የነበረኝን ቁርጠኝነት እያሳየሁ ነው” ይላል። የአውሮፓ ሕብረት ታዛቢዎችም ምርጫውን ለመታዘብ አዲስ አበባ ገብተዋል። መድረኩ ባለፉት ሦስት ሣምንታት ብቻ በመቱ፣ በወልቂጤ፣ በደብረ ብርሃን፣ በደሴ፣ በወልዲያ፣ በኮምቦልቻ እንዲሁም በተለያዩ የአዲስ አበባ ወረዳዎች ታላላቅ ህዝባዊ ስብሰባዎችን እያደረገ ነው። በአቶ ኃይሉ ሻውል የሚመራው መኢአድ በአዋሳ፣ በአቶ ልደቱ የሚመራው ኢዴፓ ደግሞ በአለታ ወንዶ፣ ጎንደርና ባህር ዳር ህዝባዊ ስብሰባዎች ያደረገ ሲሆን፤ የምርጫ ዘመቻቸውን አጧጥፈውታል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

እነ አቶ መለስ ማጅራቱን ከመቱት ምርጫ ተቃዋሚዎች ለምን ራሳቸውን አያገሉም?

ሀብታሙ አሰፋ

በምርጫ 97 የህዝብ ድምፅ ከተሰረቀ በኋላ ሥርዓቱ ያሰጉኛል ያላቸውን ሁሉ እያሳደደ ያጠቃ ነበር። ዳንኤል በቀለ “አክሽን ኤድ” የተባለው መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ከኃላፊዎቹ አንዱ ነው። በሙያው የሕግ ባለሙያም ጭምር ነው። ምርጫውን ተከትሎ የተለያዩ አስተያየቶች ከሚሰጡ ምሁራን አንዱ ነበር። ሃሳብን መግለፅ ወንጀል በመሆኑ የእነ አቶ መለስ ደህንነቶች ከሚያሳድዷቸው ዜጎች አንዱ ይሆናል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ድብቅነት - ዘላፊነት - ቀጥሎስ?

መሣፍንት ዘፈረንሣይ ለጋሲዮን ( This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. )

“… አቶ ስየም እንዳሉት ሰው ከስህተቱም ሆነ ከስኬቱ ይማራል (እሳቸው የተማሩት ምን እንደሆነ ሲናገሩ አልሰማሁም እንጂ)። አሁን ባለው የሀገራችን ሁኔታ ከናንተ በላይ ከስህተት መማርን ማሳየት የነበረበት ማን ነበር? አሁንም ጊዜ ጥላችሁ አልሄደችም - ይቅርታ ለመጠየቅ በለበጣ ቀነ-ቀጠሮ ማስቀመጡን ትታችሁ፤ ህዝብ ፊት በመቆም የቆሸሸ እጃችሁን ታጠቡ። ማንነታችሁንም አደባባይ አውጡ። … ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢህአዲግ ልዑካኖች በርካታ ጥያቄዎችን ይዘው ተመለሱ

ዘውገ ፋንታ ከስያትል

እሑድ አፕሪል 18 ቀን 2010 እ.ኤ.አ. የኢትዮጵያ ገዥ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣኖች በስያትል ተገኝተው፣ “ከባንክ የተቀመጠ ዕንቁ” ካሏቸው የኢትዮጵያ ወገኖች ጋር የኢትዮጵያን አስከፊ ሁናቴ አስመልክቶ ሰፊ ውይይት አድርገዋል። መልስ ያልተገኘላቸውን ብዙ ጥያቄዎች ልዕካኖቹ ወደ ሀገራችን ይዘው ተመልሰዋል። ትዝብትን ያተረፈ ንግግር ግን ተንጸባርቋል። በጣም ሳይጋነን የምትታወስ ትንሽ የታሪክ ቀን ነበረች ማለት ይቻላል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዱድ - ብሩን አሳዬኝ!

ኩችዬ

በውጭ የሚኖረው ወጣት ባገሩ ፖለቲካ ንቁ ተሳታፊ አለመሆኑ ያሳዝነኛል። አንዳንዴማ ከዚያም ያለፈ ነው የሚያደርገኝ። ሰሞኑን ታዲያ ጃዋር ሲራጅ መሀመድ የተባለ ኦሮሞ ወገኔ ተስፋ ዘራብኝ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

20 ሚሊዮን ብር ለኢህአዲግ ከንግዱ ማኅበረሰብ

ፍቅሩ

ባለፈው እሁድ ሚያዝያ 3 ቀን 2002 ዓ.ም. የወጣው በሀገር ቤት የሚታተመው የእንግሊዝኛው ”ፎርቹን” ጋዜጣ በንግድ ሥራ የተሰማሩ ግለሰቦች ለኢህአዲግ ማጠናከሪያ ይሆን ዘንድ 20 ሚሊዮን ብር እንዳዋጡ ዘገበ። ’እሰየው!’ የሚያሰኝ ክንውን ነው - ከምርጫ 97 በኋላ የንግዱ ማኅበረሰብ እንዲህ በግላጭ የሚደግፈውን ፓርቲ ማሳወቁ ’ይበል!’ የሚያሰኝ ነው። በንግድ ሥራ የተሰማሩ ግለሰቦች እንዲህ በድፍረት የሚደግፉትን ፓርቲ ሲያሳውቁ ለሁሉም ጥሩ ነው። እያንዳንዱ ግለሰብ የፈቀደውን ፓርቲ የመደገፍ መብት አለውና። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከመድረክ የአሜሪካ ጉብኝት ምን ይጠበቃል?

መክብብ ማሞ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

የስምንት ፓርቲዎች ጥምረት የሆነው መድረክ ከፍተኛ አመራሮች በአሜሪካ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ እንዲሁም በመጪው ምርጫ ዙሪያ በውጪ የሚኖረውን ኢትዮጵያዊ ድጋፍ ለማግኘትና ያለውንም ለማጠናከር ካለፈው ሣምንት ጀምሮ ወደ አሜሪካ እየገቡ ይገኛሉ። አቶ ገብሩ አስራት፣ ኢንጂንየር ግዛቸው ሽፈራው እና ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የሚገኙበት ቡድን ያለፈው ቅዳሜ በሲያትል እንደሁም እሁድ በሳን ሆዜ ከተሞች ስብሰባዎችን አድርገዋል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

አረጋዊ ገብረዮሐንስን ማን ገደለው?

አሥራት አብርሃም

በጊዜ ምንገባው

ማምሸቱን የተውነው

ሌባ ወይም ሰይጣን

አይደለም … የፈራነው

ፅልመት ተገን አርገው

Aregawi Gebreyohannes, አረጋዊ ገብረዮሐንስማጅራት የሚመቱ

ገዥዎች ስላሉ ነው።

ይህ ግጥም በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ያሉ ተቀዋሚ ፖለቲከኞች ስጋት የሚያመላክት ነው። የገዥው ፓርቲ ባለሥልጣናት ቀን ህዝቡ እያየ በተቀዋሚ ፓርቲ አባላት ላይ ሲብስባቸው ወይም ሲደነግጡ ካልሆነ በስተቀር ጥቃት ለማድረስ አይደፍሩም። ማታ በጭለማ ከሆነ ግን እንድትመታ ወይ ማጅራት መቺ ገዝተው፣ ወይም ከአሁን በፊት በሆነ ነገር የተጣላህን ሰው ፈልገው፣ “አይዞህ! እንደፈለክ አድርገው!” ብለው ይልኩብሃል። ዕድለኛ ከሆንክ ተደብድበህ በሕይወት ትተርፋለህ። እስካሁን አራት የዓረና-መድረክ ተወዳዳሪዎች በዚሁ መልክ ከፍተኛ ድብደባ ደርሶባቸው ከሞት ብቻ ተርፈዋል። ድንገት ጎደሎ ቀን ከገጠመህ ደግሞ ሞትህ የግድ ይሆንና ልክ እንደ አረጋዊ ገብረዮሐንስ የሠላማዊ ትግል ሰማዕት ሆነህ ትሞታለህ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የምርጫ 2002 ትያትር እና አደገኛነቱ

ተድላ ወሰኔ ነጋሽ - Tirschenreuth, Germany

... በዚሁ መጠን ትግሉ እንዲቀጥል ለማድረግ ወሳኝ ነን በሚሉ የተቃዋሚ ፓርቲዎች አባላትና መሪዎቻቸው በዓላማቸው ፀንተው ሲቆዩና የትግል ስልቶቻቸውን በኢህአዲግ መጠን ለአሸናፊነት በሚያበቃ ተርታ ደርጅተው አይታዩም። አንድነትና ኢትዮጵያዊነት በወሬ ወይም በወረቀት ላይ ብቻ ካልሆነ በስተቀር እስከመጨረሻው አይተገበርም። ... ሙሉውን አስነብበኝ ...