ፓስተር ዳንኤልና መጥምቁ ዮሐንስ (መክብብ ማሞ)

መክብብ ማሞ

... መጥምቁና ፓስተሩ አንድ አምላክ፣ አንድ ጌታ እናመልካለን ይላሉ። መጥምቁ የሕግ የበላይነት ይከበር ሲል፤ ፓስተሩ ግን ሕግ እንዳስፈላጊነቱ ሊከበር ወይም ሊሻር ይሻር ይችላል ይላል። መጥምቁ የመንግሥት ባለሥልጣንንም ሆነ ገዥን በግልጽ ፊት ለፊት ያጠፋውን በመናገር ”ተሳስተሃል” ሲለው፤ ፓስተሩ ግን ”ከመንግሥት ጋር በመሥራት” መሸለም የሐቀኝነት መለኪያ ነው ይለናል። መጥምቁ በሐሰት ከምመሰክር፣ እውነትን እያወቅሁ ዝም ከምል ሕይወቴን እሰጣለሁ ሲል፤ ፓስተሩ ግን እንዲህ ያለ ሞኝነት አያስፈልግም ተመሳስሎ መኖር ነው ተገቢው ነገር ይለናል። መጥምቁ እውነት ነፃ ያወጣል እያለ ሲሰብክ፤ ፓስተሩ ደግሞ ”ለይቅርታ ቦርድ ጥፋተኛ ነኝ ብሎ መማጸን ነፃ ያስወጣል” ይላል። ... ሙሉውን አስነብበኝ ...

”የልጅ ነገር ሁለት ፍሬ፤ ...” (አስራደው ከፈረንሣይ)

አሥራደው (ከፈረንሣይ)

ለልጅ ተክሌ፣

”እኛ ወያኔዎች (ኢህአዲጎች) ጦርነት መሥራት እንችላለን” ያለን ማን ነበር? ልጅ ተክሌ። እስቲ ሃሳብ አብላልተህና (አቁላልተህ) አሽትት፤ መጎርናቱ ካልሸተተህ ወይ ሞያ ክዶሃል፤ ወይም የማሽተቻ ህዋሶችህ ደንዝዘዋልና የጤና ባለሙያ መጎብኘት ያሻሃል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የተሸነፍነው በትግራይ ነው፤ የምንድነውም በትግራይ

ዣንጥራር ተክሌ (ከቫንኩቨር-ካናዳ)

አረጋሽ ለአድዋ፤ አድዋም ለአረጋሽ

ብለህ ብለህ አረጋሽን? ደግሞ ምን አመጣህብን?

ይሄንን የምጽፈው እንድታምኑ አይደለም። ሀሳብን ያለማብላላትና ያለማቁላላት፤ ለተቃውሞ ተቀባብለው ለተቀመጡ ሰዎች ለግንዛቤ እንዲረዳ ነው። አንዳንድ ሰዎች አሁን ይሄንን የማውሪያ ጊዜ ነው እንዴ? ሌላ ስንት ነገር እያለ ይላሉ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...

ተቃዋሚው ብቃት አለውን? (ኩችዬ)

ኩችዬ - መጋቢት 23 ቀን 2002 ዓ.ም. (ኤፕሪል 1 ቀን 2010 እ.ኤ.አ.)

በህዝብ አዕምሮ ውስጥ ጥርጣሬ የመፍጠርን ያህል የፕሮፓጋንዳ ድል የለም። ለዚህ ማስረጃ ከፈለጋችሁ የሂትለር ቀኝ-እጅና የፕሮፓጋንዳ ጠበብት የነበረውን ጎብልስን ጠይቁት። ዓለም ሲፈጠር የት ነበርክ ትሉኛላችሁ እንጂ፤ ከያን ጊዜ ጀምሮ ይመስለኛል ጥርጣሬ መፍጠር የፕሮፓጋንዳ መሣሪያ የሆነው። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሚታዘነውስ ለነ አቶ መለስ ዜናዊ ነው (ግርማ ካሣ)

ግርማ ካሣ (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.)

የእህታችን የወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ የጤና ሁኔታ ብዙዎቻችንን እያሳሰበና እያስጨነቀ እንደሆነ አስባለሁ። ሊያስጨንቀንና ሊያሳስበንም በርግጥ ይገባል። የርሷ ሕመም የእያንዳንዳችን ሕመም ነው። በርሷ ላይ የሚደርሰው በኛ እንደደረሰ ነው። እርሷ ስታቃስት እኛም እናቃስታለን። ከዚህ በፊት በአንድ ጽሑፌ እንደገለጽኩት፣ እኛም ዓላማዋን ዓላማችን አድርገን ይዘን የተነሳን “ብርቱካን ሚደቅሳዎች” ነን። አራት ኪሎ ያሉ ባለሥልጣናት አንዲቷን ብርቱካን ሚደቅሳ በአካል ቢያስሯትም በአሥር ሚሊዮን የሚቆጠሩ ብርቱካን ሚደቅሳዎች ተወልደዋል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

አባቱን አክባሪ ትውልድ በሲያትል (አቤል አድማሱ)

አቤል አድማሱ

እ.ኤ.አ. February 13, 2010 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩን የሥነ መለኮትና የቅዳሴው ሊቅ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስን የመጨረሻ ስንብት አስመልክቶ በተለያዩ የዜና ማሰራጫዎችና የድረ ገፆች ላይ አይነተኛና ለምዕመናን አስደንጋጭ ዜና ሆኖ ሰንብቷል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የጄኔራል አበበ ተክለኃይማኖትና የአቶ መለስ ዜናዊ ምልልስን በተመለከተ (ግርማ ካሣ)

ግርማ ካሣ (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.)

የቀድሞ የኢትዮጵያ የአየር ኃይል አዛዥ ሜጀር ጄነራል አበበ ተ/ኃይማኖት “ኢትዮጵያ የአሰብ ወደብን የመጠቀም ህጋዊ መብቷን ያጣችው በፓርቲው (ኢህአዲግ) ውስጥ በነበረው ድንቁርና እና ትዕቢት ነው” ማለታቸውን በመጥቀስ፣ ጋዜጠኖች ለጠየቋቸው ጥያቄ አቶ መለስ ዜናዊ ሲመልሱ፦ ሙሉውን አስነብበኝ ...

"... ሕገወጦችን ከምርጫ በኋላ እንከሳለን ..." አቶ መለስ ዜናዊ

ተሻገር በላይ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

"... ሕገወጦችን ከምርጫ በኋላ እንከሳለን ..." የሚለው ንግግር የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ሊቀመንበር፣ የኢህአዲግ ሊቀመንበር፣ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር እና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ የሆኑት አቶ መለስ ዜናዊ ሰሞኑን ከተናገሩት ውስጥ የተወሰደ ነው። ይህ አባባላቸው አዲስ ሆኖብኝ ሳይሆን ከምርጫ ሂደት ጋር ሲታይ አግባብ የሌለው መሆኑን ወዳጆቻቸውና ደጋፊዎቻቸው ማየት ቢችሉ ብዬ ነው። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአንድነቱ ቀኝ አዝማች

ዕድሜዓለም

ከዓመት በፊት በኢትዮጵያ ዛሬ ድረ-ገጽ ላይ “አንድነትም እንደ መአህድ ብርቱካንም እንደ አስራት” በሚል ርዕስ ጽሁፍ ወጥቶ ነበር። ፀሐፊው መአህድ ተመስርቶ በብቃት መንቀሳቀስ እንደጀመረ ከውስጥም ከውጪም የገጠመውን ፈተና አመላክተው፤ መሪውን ፕ/ር አስራትን ወደ እስር ቤት በመላክ ፓርቲውን እንዴት መቆጣጠር እንደተቻለ የራሳቸውን እይታ የጋዜጠኛው ማስታወሻ ደራሲ ተስፋዬ ገብረአብ በሰጠው ምስክርነት አስደግፈው አሳይተውናል። በንጽጽርም ከ10 ዓመት በኋላ አንድነትና መሪው ብርቱካን ተመሳሳይ ዕጣ እንደገጠማቸው ፀሐፊው በጊዜ በቦታና በድርጊት እያመሳከሩ ነግረውናል።  ሙሉውን አስነብበኝ ...

ይድረስ ለአቶ ገብሩ አስራት፣ ከመርስኤ ኪዳን

መርስኤ ኪዲን

እንዳሁኑ ሳይሆን ቀድሞ “ገብረማሪያም” ምርጥ ከሚባሉ ስሞች አንዱ ነበር። እናም አንዳንድ ዓይነደረቅ ሰዎችን ለመግለፅ በትግርኛ ”ዘይሓፍር ድሙ ገብረማሪያም ሽሙ” የሚል አባባል አለ። ትርጉሙም “የማያፍር ድመት ስሙ ገብረማሪያም ነው” ማለት ነው። ይህን አባባል ለመጠቀም ያስገደደኝ በምርጫ ተፎካካሪ ፓርቲዎች መካከል ባለፈው ሣምንት በተደረገው ክርክር መድረክን ወክለው የተገኙት ሰው አቶ ገብሩ አስራት መሆናቸውን ሳይ የተፈጠረብኝ ግርምት ነው። የክርክሩ አጀንዳ “ሰብዓዊ መብት፣ የሕግ የበላይነትና መልካም አስተዳደር” ስለነበር ነው ግራ መጋባቴ። ምክንያቱም አቶ ገብሩ የትግራይ ፕሬዝዳንት እያሉ ትግራይ ውስጥ የዩንቨርስቲ ተማሪ ስለነበርኩ፤ የእሳቸው አስተዳደር ምን ይመስል እንደነበር ጠንቅቄ ስለማውቅ ነው። ሙሉውን አስነብበኝ ...