የሰብዓዊ መብት ጥሰትና የዘር ማጥፋት ወንጀል በኢትዮጵያ (ንጉሤ ጋማ)

በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ጥሰትና የዘር ማጥፋት ወንጀል አስመልክቶ በለንደን የተካሄደ ስብሰባታላቅ ህዝባዊ ስብሰባ በእንግሊዝ ፓርላማ ተካሄደ

ንጉሤ ጋማ

የሁሉም ፓርቲዎች የፓርላማ ቡድን በ3ኛው ዓለም ትብብር (All Party Parliamentary Group on the Third World Solidarity) በመባል የሚጠራው ድርጅት በታላቋ ብሪታኒያ ከሚገኙ የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ አባላት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው እን በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ላይ የተወያየ ታላቅ ህዝባዊ ስብሰባ በለንደን ተካሄደ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ቢያንስ ዶሮዋን አንሆንም?

Dorowaኩችዬ - መጋቢት 1 ቀን 2002 ዓ.ም. (ማርች 10 ቀን 2010 እ.ኤ.አ.)

ሹም መሆን ብዙ ፈተና አለው ወዳጄ! አንዲት አነስተኛ ወረዳ ውስጥ አስተዳዳሪ ሆኖ የተመረጠ ሰው የህዝቡን ተሳትፎ ለማግኘት ቁርጥ ሃሳብ ያደርጋል። የነጋዴው፤ ያስተማሪው፤ የተማሪው፤ የገበሬው በር አልቀረውም። የሁሉንም አንኳኳ። አንዱን ቀን እግሩ ካንድ ገበሬ ቤት ይጥለውና ... 

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ለኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው

ወዶ የዋጡትቅልጥም ከፍርምባ ይጥም

ታምራት ታረቀኝ

ከኢ/ር ግዛቸው ጋር ለመጨረሻ ግዜ ተገናኝተን የተነጋገርነው ሰኔ 11 ቀን 2001 ዓ.ም. በእኔ ጠያቂነት በርሳቸው ቢሮ ውስጥ ነው። ከቀትር በኋላ። ርሳቸው ጋር ለመነጋገር ምክንያቶቼ ሁለት ነበሩ። አንደኛው ሰኔ 8 እና 9 በነበረው የብሔራዊ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ በሌሎች ሰዎች እየተመሩ ስህተት ሲፈጽሙ ማየቴ ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ዋና ፀሐፊ አስራት ጣሴ ከኃላፊነት በመሸሽ በምክትላቸው ወጪ የሚያደርጉዋቸው ደብዳቤዎች ጉዳይ ነበር። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ወገኖቻችን በአገር ቤት ለለውጥ ዋጋ እየከፈሉ ነው - በውጭ ያለነውስ? (ግርማ ካሣ)

ግርማ ካሣ (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.) የካቲት 27 ቀን 2002 ዓ.ም.

ግንቦት 15 ቀን 2002 ዓ.ም. ምርጫ በኢትዮጵያ ይደረጋል። ይህን ምርጫ በተመለከተ የተለያዩ አስተያየቶች ሲሰጡ ሰንብተዋል። ስለዚህ ምርጫ ከአዲስ አበባ የሚመጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በአገር ቤት ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተከፈተውን እጅግ በጣም ጠባብ እድል በመጠቀም፣ የምርጫውን ዘመቻ በተጧጧፈ መልኩ የያዙት ይመስላል። ምንም እንኳን ዘግይተው ቢጀምሩም የምርጫ ክርክሮች በመጠኑም ቢሆን እየተሰሙ ነው። አፈናውና እንግልቱ፣ መታሰሩና መገደሉ ቢበዛም ያንን ሁሉ በመቋቋም ሕዝባዊ ስብሰባዎች በመደረግ ላይ ናቸው። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የመለስ ዜናዊ ገደብ አልባነት

ካሕሳይ በርኸ እና ተስፋይ አፅብሃ (የካቲት 26 ቀን 2002 ዓ.ም. / ማርች 5 ቀን 2010)

መለስ የህወሓት 35ኛውን ዓመት አስመልክቶ ሲናገርና በድምፅ ወያነ ትግራይ ጥያቄዎች ቀርበውለት ሲመልስ ልዩ ክብደት የሚሰጣቸው የቅስቀሳ መልዕክቶች አሉ። አንዱ መልዕክት በሃሳቦች ላይ ሳይሆን በሰዎችና ድርጅቶች እንዲሁም በተሸፋፈነ መልክ በህዝብ ላይ ያነጣጠረ አስቀያሚ፣ መጥፎ አርኣያነት ያለውና ባህላችንን የሚበክል ስድብ ነው። ሁለተኛው ደግሞ በሃሳቦች ላይ ያተኮረ የሚመስል ነገር ግን ሃሳቡ የተቃዋሚዎች መሆኑን ማስረጃ ሳይቀርብለት በእነሱ ያልተባለን እንደተባለ አድርጎ የሚያቀርበው በውሸት ላይ የተመሰረተ ህዝብን የማወናበድና የማስፈራራት ቅስቀሳ ነው። ሙሉውን አስነብበኝ ...

“የባላንጣዎች ቡድን” (ኩችዬ)

ኩችዬ - ማርች 4 ቀን 2010 ዓ.ም. (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. - http://www.blogspot.com/)

እርስ በርስ የሚጋጭ ሃሳብ ያዘለ ስለሚመስል “የባላንጣዎች ቡድን” ብሎ ነገር ግር ሊል ይችላል። ስመ ጥሩዋ የታሪክ ተመራማሪ ዶሪስ ጉድማን “Team of Rivals” በሚል ርዕስ ስለ አብርሃም ሊንከን ያቀለመችው ድንቅ መጽሀፍ ነው ። ከዛሬ ነገ አነበዋለሁ በሚል አባዜ ውስጥ መጠመዴን የታዘበ ወዳጄ ነው ሰበብ ለማሳጣት ጭምር ይህን መጽሐፍ ጀባ ያለኝ። “ስለ አብርሀም ሊንከን አሥር ሺህ የሚደርሱ መጻህፍትና መጽሔቶች ታትመው ሳለ ዶሪስ ምን ይሁን ብላ ነው ሌላ መጽሐፍ የምትጨምረው?” ያሉ ሁሉ አፋቸውን በጨው አጥበዋል። ዶሪስ ታሪክን የምታበጥረው ለርሷ ብቻ በተቸረ ዓይነት የተመራማሪነት ስልት ነውና መጽሐፉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አንብብያን አገኘ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ወያኔ ማነው?

አያልሰው ደሴ (የግል አስተያየት)

“... ይህ ድርጅት ከትግራይ ወደ ቀረው የሀገሪቱ ክፍል ሲሸጋገር፣ ይዞታውን እንጂ መሠረታዊ የሆነውን የፖለቲካ እምነቱን አይደለም የቀየረው፤ ማለትም በተወሰነ አካባቢ (በትግራይ) የነበረውን ይዞታ አስፍቶ በመላ ኢትዮጵያ መዘርጋት መቻሉ ብቻ ነው ልዩነቱ። ስለሆነም ከ”እነሱና እኛ” ፖለቲካዊ ጎጠኝና ጎሠኛ ጠባብ እምነቱ በመነጨ ፍልሥፍናው መሰረት ሲሠራበት የቆየውን ጠባብና ኢ-ዲሞክራሲያዊ አሠራር ቦታ ስለቀየረ ወይም ይዞታውን ስላሰፋ ሊቀይር አይችልም። ...” በማለት ሰፋ ያል የግል አስተያየታቸውን ያደረሱን አያልሰው ደሴ ናቸው። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ስለመድረክ መለስተኛ ፕሮግራም ጥቂት አስተያየት (አሸብር)

አሸብር ከጀርመን This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

በቅድሚያ ስለመለስተኛ ፕሮግራሙ አስተያየት ለመስጠት ጉዞ ስጀምር፤ መንግድ ላይ ያገጠመኝን ከዚሁ ፐሮግራም ጋር ዝምድና ያለው ዶ/ር ማራራ ጉዲና የመድረክ ሊቀመንበር ከሪፖርተር ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ውስጥ ስለጥምር መንግሥት አመሰራረት ከመድረክ ጋር ለማነጻጸር እንደምሳሌ አድርገው ስላቀረቡት የጀርመን ፌዴራል ሪፑብሊክ ጥምር መንግሥትን በተመለከተ ንጽጽሩ ጉድለት ስላለው ለማስተካከል ይረዳል የምለውን ልበል፤ ሙሉውን አስነብበኝ ...

የግብዞች ግብዣና የቀማኞች ይቅርታ

ከቀብር መልስ

 በቁሜ ያሳደደኝ፤ በሕይወት የገፋኝ፡

ሳልሞት የቀበረኝ፤ ስሞትም ሊገድለኝ

የመውደዱ ጽናት፤ ለቀብር ጋበዘኝ።

                ሊቀ ጳጳስ፤ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ዜና ማርቆስን ብሆን የምቀኘው።

 

አለቃ ተክሌ - ቫንኩቨር (ካናዳ)

እንባና ሳቅ፣ ሀዘንና ደስታ፤ ሞትና ሕይወት፣ ልጅና አዋቂ

ብዙ ግዜ ደረቅ ነኝ። አይኔ በግድ ነው እንባ የሚያወጣው። ፊቴ ጨካኝም ነው። አንዱ ስደት ያዘጋጀኝ ነገር እናትም ብትሞት ላለማልቀስ ነው። እነሆ ሲያትል ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክርስቲያን ተገኝቼ የሚረጨውን እንባና የሚነገረውን ምስክርነት በሰማሁ ጊዜ እንደባዬ ወረደ።

 

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አቶ መለስና ወ/ት ብርቱካን ሲነፃፀሩ (ግርማ ካሣ)

ግርማ ካሣ (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.)

ሁለቱም በኢትዮጵያ እየተፋፈመ በመጣው የፖለቲካ ሂደት ውስጥ ትልቅ ስፍራ አላቸው። ሁለቱም አባል የሆኑበት ድርጅት ሊቀመንበር ናቸው። ሁለቱም በደጋፊዎቻቸው ይደነቃሉ። ሁለቱም የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ የነበሩ ጊዜ ጎበዝ ተማሪዎች ነበሩ። ሁለቱም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ነበሩ። ሁለቱም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁት በአዲስ አበባ ነው። ሁለቱም ወላጆች እንደመሆናቸው የልጅን ፍቅር ያውቃሉ። ሁለቱም ኢትዮጵያውያን ናቸው። ሙሉውን አስነብበኝ ...