ሥላሴ - በጆሃንስበርግ (ተክለማርያም)
ተክለማርያም ከጆሃንስበርግ (ደቡብ አፍሪካ)
በቤተክርስያናችን አውደምህረት ከጥር ሥላሴ ዋዜማ ጀምሮ ዘወትር በታላቁ መምህር የክርስቶስ ወንጌል ሐዋርያ በተወዳጁ አባታችን በአባ ወልዴ የሕይወት ብፌ ተዘርግቶልን ሰነባብቷል። ሙሉውን አስነብበኝ ...
ተክለማርያም ከጆሃንስበርግ (ደቡብ አፍሪካ)
በቤተክርስያናችን አውደምህረት ከጥር ሥላሴ ዋዜማ ጀምሮ ዘወትር በታላቁ መምህር የክርስቶስ ወንጌል ሐዋርያ በተወዳጁ አባታችን በአባ ወልዴ የሕይወት ብፌ ተዘርግቶልን ሰነባብቷል። ሙሉውን አስነብበኝ ...
ይኸይስ ሞረዳ - ከአዲስ አበባ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
እንደመንደርደሪያ
በኪነ ጥበብ ዓለም ቧልታይ ተውኔት (Farce) የሚባል የኮሜዲ ዘውግ አለ። የቧልታይ ተውኔት ዋና ተግባር የተጋነኑና በእውኑ ዓለም ከምናያቸው ሁነቶች ወጣ ያሉ፣ ከዕለት ተዕለት የኑሯችን ገጠመኞች የራቁ ጉዳዮችን ይሁነኝ ብሎ (deliberately) በመከሰት ተመልካችን ወይም አድማጭን ማሳቅ፣ ማዝናናትና ማስደሰት ነው። የኮሜዲ ዘር በመሆኑም ፍጻሜው በደስታ የሚደመደም ታሪክ ያለው ተውኔት ወይም ድራማ ነው። አድማጭም ሆነ ተመልካች ብዙ ቁምነገር የሚገበይበት አይደለም- ምንም እንኳ ሳቅና መዝናናት በራሱ አንዳች ፋይዳ ያለው ነገር ቢሆንም። ሙሉውን አስነብበኝ ...
ኩችዬ
ወዳጄ ልጅ አበራ!
ሲፈራ-ሲቸር ያደረ መንፈሴን እንደምንም አነቃቃሁና ቀያችን የተከመረውን በረዶ ለመዛቅ ጧቱ ላይ ብቅ ብዬ ነበር - “ላይቀርልኝ ዕዳ!” ተብሎ የለ። ታዲያ ያልጠበቅሁት ነገር ገጠመኝ። ባወራረድ ውበቱና በነጠረ ንጣቱ ትናንት ሲያማልለኝና እንደመፈላሰፍም ሲያደርገኝ የነበረ ገራ-ገር በረዶ ዛሬ ፍጹም ጠባዩን ቀይሮ፤ እብሪተኛ “በላ ልበልሃ!” የሚል ጉድ ሆኖ አገኘሁት። ሙሉውን አስነብበኝ ...
ሀብታሙ አሰፋ
የአቶ መለስ አስተዳደር ደጋግሞ እንደተናገረው የ97ቱ ምርጫ እንዳይደገም ቀዳዳዎችን ሁሉ ደፍኗል። እነዚህ ቀዳዳዎች የታወቁ ናቸው። ምርጫ እንዳይኖር የሚያደርጉ የአፈና እርምጃዎችን ነው። ይቃወሙኛል የሚላቸውን ሁሉ በሞትና በእድሜ ልክ እስራት የሚቀጣበት የፀረ-አሸባሪነት ሕግ አውጥቷል። ከዚህ አልፎም ሕጉ በነማን ላይ እንደሚሰራ እነ ጀነራል ተፈራ ማሞ በፈጠራ ወንጀል በዚሁ አዋጅ መሰረት ተፈረዶባቸዋል። በ97ቱ ምርጫ በገለልተኝነት የታዘቡ የሲቪል ማህበረሰቡን የሚወክሉ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ፀጥ የሚያደርግ አዋጅ ወጥቷል። የፕሬስ ነፃነት ተስፋ ጭምር እንዲጨልም የዘጋውን ዘግቷል። ያሰጉኛል የሚላቸውንም የቀሩትን ለይቶ ተራ በተራ ለመጨፍለቅ ዘመቻ ይዟል። ተቃዋሚዎችን ለመከፋፈል የጀመረው ዘመቻ ከቅንጅት ውህደት ተቃውሞ ተነስቶ አጋር ተቃዋሚዎች እስከማፍራት ሄዷል። ሙሉውን አስነብበኝ ...
ግርማ ካሣ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
ምርጫውን በተመለከተ ሀገር ቤት ያሉ ድርጅቶች የሚበጃቸውን እንደሚያውቁና በተለይም ውጭ ሀገር ያለን ብዙ ጫና ማብዛት እንደሌለብን የሚገልጽ ሃሳብ ከጥቂት ወራት በፊት፣ ጥቅምት 3 ቀን 2002 ዓ.ም. “ኢህአዲግ ብርቱካን ሚደቅሳን ለምን ይፈታታል?” በሚል አርዕስት በጻፍኩት ጽሁፍ ላይ አቅርቤ ነበር። ሙሉውን አስነብበኝ ...
አማኑዔል ዘሠላም This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
ኢህአዲግ ስልጣን በጨበጠ በአሥራ ስድስት ወራቱ ነው ሀገሬን ለቅቄ የስደት ኑሮ የጀመርኩት። በማውቃቸው የአሥራ ስድስት ወራቱ የኢህአዲግና የኦነግ የጋራ አገዛዝ፣ የባንክ ሰራተኞች ያለምንም ርህራሄ ሲባረሩ፣ በበደኖና በአርባ ጉጉ “ነፍጠኞች” እየተባሉ ኢትዮጵያውያን በግፍና በጭካኔ ሲገደሉ አስታወሳለሁ። በድሬደዋ ከተማም ለሶስት ቀናት ተቀስቅሶ የነበረው የዘር ግጭት በዚያ ወቅት ነበር የተከሰተው። ሙሉውን አስነብበኝ ...
- በኦስሎ የኢ.ኦ. የቅ/ገብርዔልና ያቡነ ተ/ኃይማኖት ቤ/ክ. ምዕመናን መሪ መዝሙር
አበራ ለማ (ከኦስሎ)
“መስክሩ … ድንቅ ሥራ መስክሩ
ለዓለም ሁሉ ንገሩ” መጽሓፉ እንዲል፣ እናም ያየነውን ሁሉ በእውነት ስለእውነት እንዲህ እንመሰክር ዘንድ አዶናይ አዘዘነ … ተቤጀነ። ሙሉውን አስነብበኝ ...
ሣሙኤል ይሄነው This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
አብዛኛው ለውጥ ፈላጊ ኢትዮጵያዊ የሚስማማበት ጉዳይ ቢኖር የችግሮቻችን መጠን፣ አይነቶችና ምንጮቻቸው ቢለያይም ቅሉ፤ ችግሩ ግን በዘር፣ በቀለም፣ በጎሣ፣ በጾታ፣ በዕድሜ፣ … ወዘተ ሳይለይ የእያንዳንዱን ቤት በየተራ ማንኳኳቱ ነው። ኑሮ የከበደው፤ ነፃነቱን ተገፍፎና ተረግጦ ያለው፤ የተራበው፤ ፍትህ የተጠማው፤ … እከሌ ተከሌ ሳይባል አብዛኛው ኢትዮጵያዊ እንደሆነ ይታወቃል። ይሄ እውነት ከሆነ ታዲያ ለውጥ ማምጣት እንዴት ከበደን? የምር የተገፋና የመረረው ህዝብ እንዴት ዝም ይላል? ሙሉውን አስነብበኝ ...
መርስኤ ኪዲን This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
ሰሞኑን የአንድነት ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት ኢንጂነር ግዛቸው ሺፈራሁ “አንድነት ችግር ላይ ተጋርጧል … ሊዘጋ ይችላል” ሲሉ ዴይሊ ኔሽን ለሚባለው የኬንያ ጋዜጣ መግለጻቸውን ሰንደቅ ጋዜጣ ታህሳስ 28 ቀን 2002 ዓ.ም. ባወጣው ዕትሙ አስፍሯል። የኢትዮጵያን ፖለቲካ በአንክሮ ለሚከታተል ሰው ይህ ዜና ብዙም አስገራሚ አይሆንበትም። ለምን? ቢባል አንድነት መድረክ የተባለውን “የእንቧይ ካብ” የተቀላቀለ ጊዜ እንዳበቃለት ግልጽ ነውና። ሙሉውን አስነብበኝ ...
ብሩክ ለማ ከስድስት ኪሎ bThis email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
በግንቦት 2002ቱ ምርጫ የ1997ቱን ያህል የሕዝብ ተሳትፎን መጠበቅና የለውጥ ተስፋን መሰነቅ ከምኞት ባያልፍም፣ አጋጣሚውን ተጠቅሞ የግፈኛ ስርዓቱን እድሜ ለማሳጠር መትጋት ግን ተገቢ ነው። መላው ሕዝብም ሆነ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚጠበቅባቸውን ከተወጡ ቀዳዳ አይጠፋምና የምንጠብቀው ድል ላይርቅ ይችላል። በምርጫ መሳተፉ ዋና ግቡ የፖለቲካ ስልጣንን በሕዝብ ይሁንታ መቆጣጠር ቢሆንም በምርጫ ሂደት የተፈጠረ ደባና ሴራን አጋልጦ የአሸነፍኩ ባይን ህጋዊነት መንፈግና እንዲነፈግ በማድረግ ቀጣይ ትግልን ማፋፋም ሌላኛው ግብ ተደርጎ መወሰድ ይኖርበታል። የሕዝብን ስሜት በአግባቡ ተረድቶ፣ ከወያኔ የአፈና ስርዓት ጋር አገናዝቦ ትክክለኛ ስትራተጂን መቀየስ ወደ ተጠቀሰው ድል ያደርሳል። የዚህ ፅሁፍ ዓላማም በዚሁ ዙሪያ ያጠነጠነ ሲሆን በምርጫው ለመሳተፍ ሽር ጉድ የሚሉት ተቃዋሚ ፓርቲዎችና ምረጠኝ የሚባለው ሕዝብ ቢያጤኗቸው ወደ ተሻለ ውጤት ሊመሩ ይችላሉ የሚባሉትን ይጠቁማል። ሙሉውን አስነብበኝ ...