በትምህርት (ውስጥ) እንደሚገኝ ያለ ድንቁርና የትም የለም!

Graduationተሻለ መንግሥቱ

ከኢትዮሚዲያ ድረገጽ ያገኘሁትን አንድ በፈረንጅ አፍ የተጻፈ መጣጥፍ ይዤ ሳነብ የንባብ ፍላቴን ማረከውና ዘለቅሁት። በዚያም አልበቃኝም። እዚያው መጣጥፍ ውስጥ በተጠቆመ ማስፈንጠሪያ (ሊንክ) ወደ ኢካድፎረም ድረገጽ አመራሁና በዶክተር ተድላ ወ/ዮሐንስ የተጠቀሰውን የፀጋየ አራ አርሳ ፌስቡካዊ ንግግር የተተቸበትን የራሱን የተድላን ትንሽ ቆየት ያለ የሚመስል ጽሑፍ አነበብኩ ... አነበብኩ እንኳን ሳይሆን በንዴት ተቃጠልኩ ነው ማለት ያለብኝ - ለነገሩ እንዲህ ዓይነት የታሪክና የትውልድ ጭንጋፎች በአነስተኛው የሚፈልጉት እንዲህ ዓይነቱን የዜጎችን በንዴት መንጨርጨር ነው። ወፍ ዘራሾች አዕምሯዊ ሥሪታቸው ወይም የአስተሳሰብ ቀመራቸውና ነገረ ሥራቸው ሁሉ ግራ በመሆኑ የሚያስደስታቸው የሚያሳዝን ነገር ነው። ያን ጽሑፍ ስጨርስ ነው እንግዲህ በመግቢያየ ባስቀመጥኩት ርዕስ የተሰማኝን እንደወረደ ለማስቀመጥ ብዕር ያሳሁት። ይህን ግን ያዙልኝ፡- እንደኢትዮጵያ የተረገመ አገር የለም!!!

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የመደራጀት መብት ግዴትም አለበት

ይገረም አለሙ

Colorful Ethiopia

ለማናቸውም ዓላማ ሰዎች ተሰባስበው ድርጅት የመፍጠር መብት አላቸው፤ በአንጻሩ ለድርጅታቸው የሚሰጡት መጠሪያ እናራምደዋለን የሚሉት ዓላማ እና እንደርስበታለን የሚሉት ግብ በተናጠል ግለሰብንም ሆነ በወል ማኅበረሰብንና አገርን ሊነካ ስለሚችል ከዚህ አንጻር ሊፈጽሙት የሚገባ ግዴት አለባቸው። በመሆኑም በሕገ መንግሥትም ሆነ በፓርቲዎች ማቋቋሚያ አዋጆች ውስጥ እነዚህ ከመደራጀት አንጻር ተግባራዊ የሚሆኑ መብቶችና ግዴታዎች ሰፍረው ይገኛሉ። ነገር ግን በፌስ ቡክ ድርጅት ሲመሰረት የመስራቾቹ ቅን ፍላጎትና ራስን ለሕግ የማስገዛት ሰውነት ከሌለ በስተቀር ለሕግም ለሞራልም ግዴታዎች እንዲገዙ የሚገደዱበት ሁኔታ አይኖርም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሰባት ነቃሽ እውነታዎች፣ ከገዥው እስከ ተቃዋሚው የምቀኝነት መንፈስ ያጸለመው የአገር ፖለቲካ

ሸንቁጥ አየለ

Ethiopia

፩ኛ- ወያኔዎች ለ25 ዓመታት በየሚዲያው፣ በየመጠጥ ቤቱ፣ በየጓዳቸው እና በየስርቻው የሚለፈልፉት አንድ የምቀኝነት ንግግር አለ። "እኛ ታግለን፣ እኛ ሞተን፤ ለማን ብለን ነው ሥልጣኑን በዲሞክራሲያዊ መንገድ ለተቃዋሚ የምናስረክበው?" የሚል ነው። ይሄም ሲፈታ ምን ማለት ነው? በኛ ደም ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ከምትገነባ፤ ኢትዮጵያ በመከራ ለዘመናት እየተሰቃየች ትኑር ማለት ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢትዮጵያን ፍላጎት ያልተረዳ መንግሥት ኢትዮጵያን ሊመራ አይችልም

ገለታው ዘለቀ

በቅርቡ ፋና ብሮድካስት ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ “ኢሕአዴግን” የወከሉት የኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናትና ምርምር ምክትል ኃላፊ አቶ በረከት ስምኦን ባቀረቡት ጥናታዊ ፅሁፍ ላይ ጥቂት ለመወያየት ነው የዛሬው አሳቤ። በዚህ የውይይት መድረክ ላይ እኚህ ሰው የተናገሩት ብዙው ነገር ከተለመደው የተለየ ባይሆንም በተለይ የኢትዮጵያን ፍላጎት በተመለከተ የፓርቲያቸው አመለካከትና ጥናትና ምርምር ምን መሰረታዊ ችግር እንዳለበት መመርመር የዚህን መንግሥት መሰረታዊ ችግሮች እንደገና ለማሳየት ይጠቅማል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

እባካችሁ አናሟርት፤ ማፍረስ በአፍ ይሄዳል

ተሻለ መንግሥቱ

Rebels

በግዕዝ “ትንቢትሰ ይቀድሞ ለነገር” ይባላል። አንድ ነገር በእውን ከመፈጸሙ በፊት በትንቢት እንደሚጠቆም ለማስገንዘብ ነው እንዲያ መባሉ። እናም እውነት ነው የብዙ ነገሮች አፈጻጸም በትንቢት መልክም እንበለው በንግርት ወይም በዘመናዊ ቋንቋ በስድስተኛው የስሜት ህዋስ (the sixth sense, telepathy, by intuition, etc.) እንደምንለው አስቀድሞ እየተጠቆመ ሁሉም ማለት ባንችል የተወሰነው በተግባር ሲታይ እናስተውላለን። ስለዚህም እባካችሁ ኢትዮጵያን የምትወዱ ወይም ቢያንስ እንድትፈርስ የማትፈልጉ ወገኖች በሆነ ባልሆነው ከመሬት እየተነሳችሁ “እንዲህ ከሆነ/ካልሆነ ኢትዮጵያ ትፈርሳለች!” እያላችሁ አታሟርቱባት። “ጥሩ ተመኝ ጥሩ እንድታገኝ” እንደሚባለው፣ ባይሆን ለዚህች ለበርካታ ዘመናት ለተጎሳቆለች አገር ደግ ደጉን ብትመኙላት ቢያንስ ኅሊናችሁ ይደሰታል። መገንባት ቀርቶ ማፍረስ ቀላል በሆነበት ዘመን እንዳመጣልን አናሟርት።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በዐረብ አገራት ያሉ ኤምባሲና ቆንስሎች ድክመት - የማለዳ ወግ

ነቢዩ ሲራክ

* የጎዳን የመብት አስከባሪ ማጣት እንጅ ዐረቦች ከፍተው አይደለም
* ዐረብ አሰሪዎች ግፍ ፈጽመው የሕግ የበላይ አይሆኑም
* ሦስት ዓመት ያለ ደመወዝ አሰሯት፣ የመብት አስከባሪ ተገኘና ተከፈላት

ከሦስት ዓመት በፊት ያኔ "ሕጋዊ" በተባለው የኮንትራት ሠራተኞች ወደ ሳውዲ ከጡት ዕድሜያቸው ለሥራ ካልደረሱት መካከል ስለአንዷ እኅታችን ነው ዛሬ የማወጋችሁ። ለሥራ በተሰማራችበት የምሥራቅ ሳውዲ አንድ ትንሽ መንደር ከሳውዲ አሰሪዎቿ ጋር ለሦስት ዓመታት ከሰራች በኋላ አሰሪዎቿ ደመዎዝ ሳይሰጡ ወደ አገር ለመላክ ወደ ጊዜያዊ መጠለያ እስር ቤት ያስገቧታል። ደማም ውስጥ ባረፈችበት ማቆያ እስር ቤት በተመሳሳይ ሁኔታ በኮንትራት መጥተው ወደ አገር ለመግባት የቆረጡ እኅቶችን ታገኝና እያነባች የደረሰባትን ድካምና ለዓመታት የሠራችበትን ደመወዝዋን አለመቀበሏን ላገኘቻቸው ሐበሻ እኅቶቿ ታጫውታቸዋለች። ይህን አሳዛኝ ታሪኳን የሰሙት እኅቶች መረጃውን ተቀባብለው "በዜጎች ጉዳይ ያገባኛል" ለሚሉ ወገኖች የደረሰባትን በደል ያደርሱታል ...

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በጅዳ ሽሜሲ በር ላይ ወድቃለች የተባለችው እኅት ጉዳይ! - የማለዳ ወግ

በጠና የታመመችነቢዩ ሲራክ

* በሳውዲ ለተቸገሩት ተወካዮቻችን በቀዳሚነት ሊደርሱልን ይገባል
* ከኢንባሲና ከቆንስላ ውጭ አማራጭ የለም
* የቆንስሉ ሹማምንትና ሠራተኞች ለፈጣሪ ብላችሁ እርዷት፣ ተለመኑን!

ከትናንት ጅዳ ውስጥ በጠና ታማ እሷና ልጇ አደጋ ላይ አሉ ስለተባለችው እኅት እየተሰራጨ ያለው መረጃ ደርሶኛል። መረጃውን በዝርዝር ያገኘሁት ከሊያ ሾው ነበር፣ ታመመች የተባለችውን እኅት በቪዲዮ የተደገፈ መረጃ እንደደረሰኝ ወደ ጅዳ ቆንስል ደውዬ ለማጣራት ሞክሬ ነበር! በጅዳ ቆንስላ መረጃ ለማግኘት ከባድ እየሆነ መጥቷል፣ አንዳንዶች ኃላፊዎች ከዚህ ቀደም በማቀርባቸው ተጨባጭ ሂሶች አኩርፈው መረጃ ላለመስጠት ስልካቸውን ይዘጉብኛል፣ አንዳንዶች ደግሞ መረጃም ሆነ ጥያቄ ለመመለስ ፈቃደኛ አይደሉም! እጅ አዙር በሆነ መንገድ የጅዳ ቆንስል መረጃው እንዳልደረሰው ተነግሮኛል!

ሙሉውን አስነብበኝ ...

መካሪ ልቦናስ አለ! ተመካሪ ሰው ግን ከወዴት አለ?

ሸንቁጥ አየለ

ሸዋ ውስጥ ደብር ዜና ማርቆስ የሚባል ገዳም አለ። በ1986 ዓ.ም. የ12ኛ ክፍል ፈተና ስጨርስ ወደ አንድ መነኩሴ አጎቴ ካንድ ጓደኛዬ ጋር ወደ እዚህ ገዳም ሄድን። ይሄን ጓደኛዬን ለማስመከር መሆኑ ነው። በወቅቱ ይሄ ጓደኛዬ ነገር ክርስቶስ ላይ ጥርጣሬ ቢያበዛ እስኪ ከኝህ አጎቴ ምክር ስማ ብዬ ነበር ይዤው የሄድኩት። እናም መነኩሴው አጎቴ ልንጠይቃቸው እንደመጣን ሲያውቁ ደስ አላቸው። ፈገግ ብለውም ተቀበሉን።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የ“ዓለም አቀፍ አማራ ተራድኦ ድርጅት” ምሥረታ አስፈላጊነትን በሚመለከት ለውይይት የቀረበ

ዮፍታሔ

ባለፈው 40 ዓመት፣ ይልቁንም ባለፉት 26 ዓመታት አማራውን ያጋጠሙትና አሁንም እንደቀጠሉ ያሉት ችግሮች ከፍ ያሉና ዘርፈ ብዙ ናቸው። ከፍ ያለ ችግር ከፍ ያለ መፍትሔ ያስፈልገዋል።

አማራው በአገር ቤት የደረሰበትና እየደረሰበት ያለው ዘርፈ ብዙ ጥቃት፣ ችግርና መከራ የታወቀ፣ እየታወቀ ያለ፤ በአብዛኛው የተመዘገበና እየተመዘገበም ያለ ነው። ይህም ተጠናክሮ ይቀጥላል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ቀበጥ አማት ሲሦ ብትር አላት!

Dulaምሕረቱ ዘገዬ

“የአገሬን ሕዝብ ለጣሊያን ቅኝ ገዢ አድረህ ተገዛ ከምል ሞቴን እመርጣለሁ” በማለታቸው በመትረየስ ተደብድበው የሞቱ አባት (አቡነ ጴጥሮስ) በተፈጠሩባት ምድር፤ “መሣሪያችሁን በሰላም አስረክባችሁ ‹እግዜር ከሾመው መንግሥት› ከወያኔ ጋር በሰላም እየኖራችሁ ልጆቻችሁን አሳድጉ” የሚሉ ካህናትን ማየት በጣም ያምማል። ከሰሜን ምዕራብ የአገራችን ክፍል ሰሞኑን እየሰማነው ያለው አስነዋሪና አሣዛኝ ነገር ይህን የሚመስል ነው። ይህ ክስተት ሊሰሙትም እጅግ የሚሰቀጥጥ በመሆኑ በዚህ ዓይነት ቅሌት ውስጥ የሚገኙ የአገር ሽማግሌዎችና የኃይማኖት አባት ተብዬዎችን በተቻላችሁ ሁሉ አስጠንቅቁ - ለፈርሳቸው ሲሉ ዕድሜያቸውንና ማተባቸውን ይህን ያህል አያዋርዱ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ