“ከዚህ በላይ ምን ትሆናለህ? ክተት! አትነሳም እንዴ?” አለ ዘረኛው ኒዮ ፋሺስት ዶናልድ ትራምፕ በሪፑብልካኑ ጉባዬ ላይ

ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ)

Trump

በጁሊየስ ቄሳር ተውኔት ውስጥ የቄሳርን ሞት ተከትሎ ጣሊያንን ሽባ የሚያደደርግ የእርስ በእርስ ጦርነት ሊከሰት እንደሚችል ሸክስፒር የማርክ አንቶኒን ገጸ ባህሪነት በመላበስ እንዲህ በማለት አስጠንቅቀው ነበር፤

“…እናም አቴ በእርሱ በኩል ከጋነም እሳት ሆኖ በመምጣት የቄሳርን መንፈስ በመላበስ የንጉሱን ድምጽ በመያዝ ለበቀል ተዘጋጅቷል። እናም እናልቅስ፣ እናም እነዚህን የጦርነት ውሾች እናስወግድ“ ብለው ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የወያኔ “የመረጃና ማስረጃ” ድንፋታ

ይገረም አለሙ

ወያኔ የሙያ ማኅበርም ይሁን የፖለቲካ ፓርቲ መሪ ለሥልጣኑ አስጊ ሆኖ ሲታየው (ፕ/ር ዓሥራት ወ/የስ፤ ዶ/ር ታዬ ወልደሰማያት) በምርጫ ሲሸነፍ ወይንም ልሸነፍ እችላለሁ ብሎ ሲሰጋ (ምርጫ 97) የዜጎችን የመብት ጥያቄ ተከራክሮ መርታት ወይንም ተገቢውን ምላሽ መስጠት ሲያቅተው፣ (የሙስሊም ችግሮች መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ፤ የወልቃይት ኮሚቴ) ሃሳብን በሃሳብ መሞገት፣ ብዕርን በብዕር መርታት ሲሳነው (በየእስር ቤቱ ያሉ ጋዜጠኞች) ምን እንደሚያደርግ ትናንትን የመርሳት ችግራችን አስረስቶን ካልሆነ በስተቀር የሚታወቅ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አሜሪካንን እያሳደዳት ካለው ጣረ ሞት ተጠንቀቁ!

ፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ)

የትራምፕ ጣረ ሞት አሜሪካንን በማሳደድ ላይ ይገኛል

ዶናልድ ትራምፕ Trump Heil

ሁለት እምነተ ቢስ ፖሊሶች ሁለት አፍሪካ አሜሪካዊ ዜጎችን ከገደሉ እና አንድ መሳሪያ የታጠቀ ሰው አምስት የዳላስ ፖሊስ ኃላፊዎችን ከገደለ እና ሌሎች ሰባት ሰላማዊ ሰዎችን ካቆሰለ ከቀናት በኋላ ዶናልድ ትራምፕ እራሱን የሕግ እና የሥርዓት እጩ አድርጎ በመጥራት ይህንን አሰቃቂ ድርጊት ፖለቲካዊ እንደምታ ያለው ለማድረግ ሞክሯል። ትራምፕ እንዲህ በማለት አውጇል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ወያኔ ያልፋል፣ ጠንቁ ለትውልድ ይተርፋል

ወያኔ ያልፋል፣ ጠንቁ ለትውልድ ይተርፋል Weyane yalefal tenku leteweld yeterfalይገረም አለሙ

ዘለዓለማዊ የሚሆን ምድራዊ ኃይል የለም። የግዜ እንጂ የሰው ጀግናም የለም። በመሆኑም አንድ ቀን በወያኔ ላይ ፀሐይ ልትጠልቅበትና ከመኖር ወደ አለመኖር ሊሸጋገር፤ አለያም እንደ ዛሬው ከፊሉን በሆድ ገዝቶ፣ ከፊሉን ሥነ-ልቦናውን ሰልቦ፣ ወዘተ በአሽከርነት ያሰለፈበትን፤ ብዙኃኑን ደግሞ በጠመንጃ አፍኖ ለመግዛት የበቃበትን አቅም አጥቶ የእጁን የሚያገኝበት ግዜ የዘገይ እንደሁ እንጂ መምጣቱ አይቀሬ ነው። ዘላለማዊነት የለምና።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጦማር - ወልቃይት

ወልቃይት ፀገዴገለታው ከሩቅ ምስራቅ

ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደምትናፍቅ፤ ወልቃይትም ዘውጉን ናፈቀ

የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር አቶ መለስ ዜናዊ ደጋግመው ይናገሩ የነበሩት ስለ በግድ ምስለት ወይም በግድ እኔን መስለህ ኑር (forced cultural assimilation) ጉዳይ ነበር። እንደ አዲስ መገለጥ ነበር ይህን የሚሰብኩት። ህወሓት ገና ደርግን ሥልጣን ላይ ትንሽ ቆይቶ ሳያየው ወደ ጫካ ወሰደኝ የሚለው ጉዳይ ይሄው የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በነሱ ቋንቋ “መጨፍለቅ … መዳጥ” ጉዳይ ነው ይላሉ። ይህ ማለት ቡድኖች ሳይወዱ በግድ አማራውን እንዲመስሉ ተደርጓል በሚል ነው። በነሱ ቋንቋ “አማራይዜሽን” ይሉታል። እንዴው አማራው እንዲህ ባለፉት ስርአቶች ከተመቸው ስለምን ሃይለስላሴን ታገለ? ስለምን የወሎ እናት በነ አሊ ሙሳ ልጆቿን ተቀማች? ስለምን ሸዋ አመፀ? ስለምን ጎጃም ተነሳ … ስለምን ጎንደር ታገለ … ለዚህ ጥያቄ ወያኔ መልስ የለውም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አሃዳዊም ፌዴራላዊም ያልሆነው የወያኔ ሥርዓት

ይገረም አለሙ

ስለ አሃዳዊና ፌዴረላዊ ሥርዓት ምንነትና እንዴትነት በአጭሩና በጥቅሉ የመጀመሪያው ሥልጣን የተማከለበት ሁለተኛው ሥልጣን የተከፋፈለበት ብሎ መግለጽ ይቻላል። ዛሬ በኢትዮጵያ ያለው ግን ሁለቱንም ያልሆነ ሥርዓት ነው። በወያኔ የትግል ብስራት ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ራስን በራስ የማስተዳደር መብት የተጎናጸፉበትን ፌዴራላዊ ሥርዓት ለማግኘት በቅተዋል ተብሎ ቢነገረንም መሬት ላይ የሚታየው እውነታ ግን ይህን አያሳያም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የማን መሬት?

አብርሃም በየነ

ሞት ለሰው ልጆች ፀጋም ዕዳም የሚሆንበት ጊዜ አለው። ዜጎች መብታቸው ሲደፈር፣ ነፃነታቸው ሲገፈፍ፤ ማንነታቸው ሲፋቅና የመኖራቸው ህልውና በሞት ጥላ ስር ሲወድቅ ሞት ዕዳውን ያከብድባቸዋል። የክፍያውንም ዋጋ በሕይወት ይመነዝረውና መተኪያ የሌለውን ሕይወት በሞት ወለድ አገድ ያስይዘዋል። ህዝብም የታገቱትን መብቶቹን ለማስፈታት ሞትን ይኖሩታል እንጂ አይሞቱትም ብሎ ይንቀሳቀሳል። ሰው የተፈጠረው ለመሞት ነውና ሞትን ሙቶ ሊያቸንፈው ዕምቢኝ ለሀገሬ ሲል በሞት ላይ ያምፃል። ብሎም ጅግና ይፀነሳል። ሰማዕት ይወለዳል። ህዝብም ከመቃብር በላይ የሚውል ስም በደሙ ጽፎ ለማለፍ ሆ ብሎ ይነሳል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጥላቻ ጥላቻን፣ ኃይል ኃይልን፣ ሕግ አልባነት ሥርዓተ አልበኝነትን ይወልዳል

“Hate Begets Hate; Violence Begets Violence” and Lawlessness Begets Anarchyፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ)

በዚህ ባለፈው ሳምንት አሜሪካውያን መንፈሳቸውን በሚፈታተን ክስተት ውስጥ ወድቀዋል። አሜሪካውያን አጅግ በጣም አዝነዋል። አሜሪካውያን በጥንቃቄ በማሰብ ስቃይ ውስጥ ተዘፍቀው ይገኛሉ።

ሁለት አፍሪካ አሜሪካውያን ዜጎች በሁለት እምነተ ቢስ የፖሊስ ኃላፊዎች ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ መገደላቸውን ተመልክተናል። እምነተ ቢስ የፖሊስ ኃላፊዎች የሚለውን ሀረግ ላሰምርበት እፈልጋለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአክሱም ሐውልት ለወላይታው ምኑ ነው?

TPLFተሻለ መንግሥቱ

በብሂለ ግዕዝ “ትንቢትሰ ይቀድሞ ለነገር” ይባላል። አንዳንድ ነገሮችን በአፍ ወለምታም ይሁን በቴሌፓቲክ የነገሮች አፈጻጸም ሂደት ቀድመው ይጠቀሳሉ። መለስ ዜናዊ ስለአክሱም ሐውልት የይገባኛል ጥያቄና የባለቤትነት ይዞታ ሲናገር መረንን በማያውቀው ስድ አንደበቱ በርዕሴ ላይ የጠቀስኩትን ከፋፋይ ሃሳብ በገሃድ ተናግሯል። ለነገሩ መለስ ያልተናገረው ጠያፍ ነገር የለም። የአንዲት ሀገር መሪ ሆኖ ራሱን ሾሞ ሲያበቃ ሌሎችን እንደጨርቅ እርሱ የወጣትበን ጎሣ ግን እንደወርቅ መመሰሉን በአደባባይ ገልጾ እርሱና እርሱን መሰሎች ሀፍረትን ባያውቁም እኛ ስለነሱ አፍረናል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዩንቨርስቲዎቻችን እባካችሁን አታሳፍሩን!

ታረቀኝ ሙጬ (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.)

“ልፋ ያለው በልሙ ዳውላ ሲሸከም ያድራል” እንዲሉ ሆኖብን ሰሚና አድማጭ ያለ እየመሰለን የምንጮህ ብዙዎች ነን። ግን ያው እነመምሩ “ነባይ ነባይነ ከምዘይባይነ ኮነ” (ጮህን፣ ጮህን ግና እንዳልጮህን ተቆጠርን (ሰሚ አጣን)” እንዳሉት ዘመናችን የጥንቶቹ ባቢሎናውያን ዓይነት የመደነቋቆሪያ ጊዜ ሆነና እንዲሁ በከንቱ እንደቁራ እንጮሃለን። ቢሆንም ካለመጮኽ መጮኽ ይሻላል - ዝምታም አንዳንዴ ከሞት አንድ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ