“ሽፈራው - ሞሪንጋ”ን የሚመለከት አዲስ መጽሐፍ ወጣ
ጋዜጠኛ፣ ገጣሚና ደራሲ አበራ ለማ “ሽፈራው - ሞሪንጋ” የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ አሣተመ። ሞሪንጋ ወይም ባገራችን “ሽፈራው” እያልን በስፋት የምንጠራው ዕጽ፣ እጅግ እውቅናን አግኝቶ የኖረው በእስያ ውስጥ ነው። ሕንዶች ኦሊፌራ የተሰኘው ዝርያ ባለጸጎች በመሆናችው በብዙ መልኩ ሲጠቀሙበት ኖረዋል። ዛሬ ኦሊፌራ የተሰኘው ዝርያ፣ በሰሜንና ደቡብ አሜሪካ፣ በካሪቢያን ደሴቶች፣ በአፍሪካና በኦሴኒያ ውስጥ በብዛት እየለማና እየተስፋፋ ነው።