በኢሕአዴግና በተፎካካሪዎቹ መካከል በሚደረገው ድርድር የዲያስፓራ ሚና ምን ይሁን?

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

Discussion on the role of the diaspora
የዲያስፖራው ተሳትፎ ምን ይሁን? በቀጥታስ ሆነ በተዘዋዋሪ መሳተፍ አለበት ወይ? ተጽዕኖስ ማስረግ አለበት ወይስ የለበትም? …

ገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ አገር ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር ለመደራደር ቅድመ ዝግጅት እያደረገ መሆኑ ይታወቃል። በዚህ ድርድር ላይ የዲያስፖራው ተሳትፎ ምን ይሁን? በቀጥታስ ሆነ በተዘዋዋሪ መሳተፍ አለበት ወይ? ተጽዕኖስ ማስረግ አለበት ወይስ የለበትም? ... በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ፎረም 65 ከአቶ እስራኤል ገደቡ እና ከአቶ ግርማ ካሳ ጋር ውይይት አድርጓል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዶ/ር ብርሃኑ መንግሥቱ ከፎረም ፷፭ ጋር ያደረጉት ቃለምልልስ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active
Dr. Berhanu Mengistu on Forum 65
ዶ/ር ብርሃኑ መንግሥቱ ከፎረም ፷፭ ጋር ያደረጉት ቃለምልልስ

የቅራኔ አፈታት ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር ብርሃኑ መንግሥቱ ከፎረም 65 (65 ፐርሰንት) ጋር ቅራኔ ምንድን ነው? ቅራኔ ለምን ይፈጠራል? እንዴት ይገለፃል? ቅራኔን ለመፍታት መነጋገር ጥቅሙ ምንድን ነው? በሚሉና በሌሎች ከቅራኔ ጋር የተያያዙ ነጥቦች ላይ ቃለምልልስ አድርገዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ፕሮፌሠር አለማየሁ ገብረማርያም ከአዲስ ድምፅ ጋር ያደረጉት ቃለምልልስ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active
Prof. Al Mariam

ፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም (አለ ማርያም) ከጋዜጠኛ አበበ በለው ጋር በአዲስ ድምፅ ራዲዮ ቃለምልልስ አድርገዋል። ቃለምልልሱ ያተኮረው፣ የህወሓት/ኢሕአዴግ መንግሥት ባለሥልጣናት አሜሪካን አገር ለሚገኝ ሎቢስት ወደ ሁለት ሚሊዮን ዶላር በመክፈሉ ዙሪያ ላይ ሲሆን፤ በተለይም በአሜሪካ ነዋሪ ከሆኑ ኢትዮጵያውያን ምን ማድረግ እንደሚጠበቅ ያብራራሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ በመጽሐፋቸው ዙሪያ በተነሱ ጉዳዮች ላይ ያደረጉት ቃለምልልስ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ በእስራኤል አገር ከሚገኘው ”መሬት ኢትዮ እስራኤል ድምፅ” ራዲዮ ጣቢያ ጋር በአዲሱ መጽሐፋቸው (የኦሮሞ እና የአማራ እውነተኛ የዘር ምንጭ) ዙሪያ ቃለምልልስ አድርገዋል።

በቃለምልልሱ ስለመጽሐፋቸው እና በመጽሐፉ ዙሪያ ተነስተው ለነበሩ ውዝግቦች ምላሽ ይሰጣሉ።

"የምንታገለው ሕዝባችን ዕጣ ፈንታውን በሬፈረንደም እንዲወስን ነው!" አቶ ቃሲም አባ ነሻ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

የኦሮሞ ነጻ አውጭ ግንባር ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ቃሲም አባ ነሻ፤ ሰሞኑን ላስ ቬጋስ ከሚገኘው ህሊና ራዲዮ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ፣ "የምንታገለው ሕዝባችን ዕጣ ፈንታውን በሬፈረንደም እንዲወስን ነው!" ከማለታቸውም ሌላ፤ ”በኦሮሚያ ያሉ ዞኖች ከፈለጉ ከኦሮሚያ የመውጣት መብት አላቸው” ሲሉ ተደምጠዋል።

[ቃለምልልስ] ”ገጣሚ መባል ያስፈራኛል!” ወለላዬ

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

Welelaye's yerob gitem y2 n52ወለላዬ በየሳምንቱ ረቡዕ ረቡዕ በኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገጽ ላይ ለሁለት ዓመታት ያህል ሳያቋርጥ 104 ግጥሞች በመጻፍ አስነብቦናል። በነዚህ ግጥሞቹ እኛን ሆኖ ውስጣችን ገብቶ ያልተናገርነውን ተናግሮልናል። ታዝበን ያለፍነውን ገልጾልናል። የሸሸግነው አጋልጦ አውጥቶብናል። የረሳነው አስታውሶ ወይ ጉድ አሰኝቶናል።

ግጥሞቹ ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊ አገራዊና ተፈጥሮዋዊ ነገሮችን ይዘው የሚያጠነጥኑ፤ ጭብጣቸው የተለያየ መልዕክት የሚያስተላልፍ በመሆኑ በአዲስ ረቡዕ አዲስ ነገር ለማንበብ በጉጉት ያስጠብቃሉ። ረቡዕ እንደሌላው ሁሉ ቀን ቢሆንም በወለላዬ ግጥም ምክንያት አንባቢዎቹ ዘንድ ደምቆ የሚታይ ሆኗል።

ደራሲና ገጣሚ አለማየሁ ታዬ ወለላዬ የአንድ ዓመቱን ረቡዕ ግጥም ሲያጠናቅቅ ስለ ግጥሞቹ አስተያየት ሲሰጥ፤ “የወለላዬ ግጥሞች አብዛኞቹ ባራት መስመር የተቋጠሩ እጥር ምጥን ያሉ የዘመናችን መዝሙሮች የየዕለት ሕይወታችን ሂሶች ናቸው። ግጥሞቹ ግልጽና ቀጥተኛ ስለሆኑ አደናጋሪነት አይታይባቸውም። የየስንኞቹን ሃሳብ ለመረዳትም ጥልቅ ምርምርና ተመላልሶ ማንበብን አይጠይቁም” በማለት ገልጾታል።

ኢትዮጵያ ዛሬም ይህን አስተያየት የምትጋራ ሲሆን፣ ወለላዬ በየሣምንቱ የሚያቀርበውን የረቡዕ ግጥም ሁለተኛ ዓመትን ከላይ በሰፈረችው ግጥም ስላጠናቀቀ ስለ ግጥም ሥራውና ስለ ገጣሚነቱ ምን ይላል ከሚለው ሃሳብ በመነሳት ጥያቄዎች አቅርበንለት ነበር። የሰጠንን መልስ እንዳለ አስፍረናል። መልካም ንባብ!!

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!