ለአቶ ልደቱ የተፈቀደው ዋስትና ታገደ
አቶ ልደቱ አያሌው
ዋስትናውን ያገደው የኦሮሚያ ጠ/ፍ/ቤት ምሥራቅ ሸዋ ተዘዋዋሪ ምድብ ችሎት ነው
ኢዛ (ሐሙስ መስከረም ፲፬ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. September 24, 2020)፦ ያልተፈቀደ የጦር መሣሪያ በመያዝ ወንጀል በምሥራቅ ሸዋ ዞን ክስ የተመሠረተባቸውና ከትናንት በስቲያ (ማክሰኞ መስከረም 12 ቀን 2013 ዓ.ም.) በ100 ሺህ ብር ዋስትና እንዲለቀቁ የተፈቀደላቸው አቶ ልደቱ አያሌው የተሰጣቸው የዋስትና ፈቃድ ታገደ።
የአቶ ልደቱ አያሌውን የዋስትና ፈቃድ ያገደው የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የምሥራቅ ሸዋ ተዘዋዋሪ ችሎት መኾኑ ተነግሯል።
ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የእግድ ትእዛዙን የሰጠው የአዳማ ፍትሕ ቢሮ ዓቃቤ ሕግ ዋስትናው ላይ ይግባኝ በማለቱ እና ፍርድ ቤትቱም ይግባኝ ያስቀርባል ሲል ዋስትናውን በማገድ መስከረም 19 ቀን 2013 ዓ.ም. በቀጠሯቸው እንዲቀርቡ አዝዟል። (ኢዛ)



