የABC ንብረት ተወረሰ

ሦስት ሰዎች ታሰረዋል፤ ከግንቦት 7 ጋር ይጠረጠራል

Ethiopia Zare (እሁድ ግንቦት 23 ቀን 2001 ዓ.ም. May 31, 2009)፦ የአዲስ ብሮድካስቲንግ ኤጀንሲ ንብረት የነበረ የ7 ሚሊዮን ብር የራዲዮ ስቱዲዮ መሣሪያ ከትናንት በስቲያ በመንግሥት ኃይሎች ውርስ ተደረገ። ግንቦት 20 ማታ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በተሠራጨ ዜና ንብረቱ የተወረሰው “በሕገ ወጥ መንገድ የገባ በመሆኑ ነው” ተብሏል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

”የወያኔ መሪዎች የትግራይን ህዝብ አይወክሉም” ፕ/ት ኢሣያስ አፈወርቂ

ፕ/ት ኢሣያስ አፈወርቂ Presidant Isaias Afwerki70 ደቂቃ የፈጀውን የቲቪ ቃለምልልስ ይዘናል

Ethiopia Zare (ረቡዕ ግንቦት 19 ቀን 2001 ዓ.ም. May 27, 2009)፦ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሣያስ አፈወርቂ ለስዊድን ቴሌቭዥን በሰጡት ቃለምልልስ፤ ”የወያኔ/ኢህአዲግን መሪዎች ጥቂቶችና የየትኛውም የኢትዮጵያ ህዝብ/ብሔር ውክልና የሌላቸው ናቸው። የትግራይ ህዝብንም አይወክሉም።” ብለዋል። በዚሁ ቃለምልልስ ላይ ሲ.አይ.ኤ.ን፣ አሜሪካንን፣ ስዊድንን እና ወያኔ/ኢህአዲግን ወንጅለዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አንድነት ስብሰባ ለማካሄድ ችግር እንደገጠመው ገለጸ

Letter to UDJ from City Government of Addis Ababa Ethiopia Zare (ቅዳሜ ግንቦት 15 ቀን 2001 ዓ.ም. May 23, 2009)፦ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ህዝባዊ ስብሰባዎችን ለማካሄድ በተደጋጋሚ ቢሞክርም የስብሰባ አዳራሽ አከራዮች ከአዲስ አበባ መስተዳደር ፈቃድ እንዲያመጡ እንደሚጠይቋቸውና ፓርቲው የህዝባዊ ስብሰባውን በመስቀል አደባባይ እንዲያደርግ መገደዱን የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር ኢንጅነር ግዛቸው በተለይ ለኢትዮጵያ ዛሬ ገለጹ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አቶ ተመስገን ዘውዴ በፀና ታመዋል

Ato Temesgen Zewde አቶ ተመስገን ዘውዴውጭ ሀገር ሕክምና ካላገኙ ሕይወታቸው አስጊ ደረጃ ላይ ነው

Ethiopia Zare (አርብ ግንቦት 14 ቀን 2001 ዓ.ም. May 22, 2009)፦ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት እና በቅንጅት ስም ፖርላማ ገብተው አቋማቸውን በመግለጽ የህዝብን ድጋፍ ያገኙት አቶ ተመስገን ዘውዴ በጽኑ መታመማቸውንና ለከፍተኛ የሕክምና ዕርዳታ ወደ ውጭ መውጣት እንደሚኖርባቸው ሐኪሞች መወሰናቸውን የኢትዮጰያ ዛሬ ምንጮች አረጋገጡ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ አበባ እና አስመራ በመቋዲሾ ጉዳይ ተካረዋል

Ethiopia Zare (አርብ ግንቦት 14 ቀን 2001 ዓ.ም. May 22, 2009)፦ በሶማሊያ የአልሻባብ እና የሂዝቡ እስላም ተዋጊዎች፣ በሌላ መጠሪያ ስማቸው “የሶማሊያ ዳግማዊ ነፃነት ኃይል” ተፋላሚዎች፤ መቋዲሾን ዋነኛ ዒላማቸው አድርገው በመዋጋት ላይ ሲሆኑ አስመራንና አዲስ አበባ በሱማሊያ ጉዳይ በስተጀርባ መወነጃጀል መቀጠላቸው ተዘገበ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አንድነት ችግሮቹን በውይይት መፍታቱን ገለጸ

Ethiopia Zare (ረቡዕ ግንቦት 12 ቀን 2001 ዓ.ም. May 20, 2009)፦ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ባለፉት ጊዜያት በማዕከላዊ ምክር ቤት አባላት ለድርጅቱና ለህዝብ ይፋ በሆነው ሰነድ ላይ በመነሳት ለሁለት ቀናት ስብሰባ በማካሄድ እልባት ላይ መድረሱን የድርጀቱ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊና ምክትል ሊቀመንበር ዶ/ር ኃይሉ አርኣያ በተለይ ለኢትዮጵያ ዛሬ ገለጹ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አጨቃጫቂው የመያዶች ሕግ ታገደ

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ግንቦት 11 ቀን 2001 ዓ.ም. May 19, 2009)፦ ከአንድ ዓመት በፊት ተረቅቆ መንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶችና በተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ውግዘት የደረሰበትና ሲያጨቃጭቅ የቆየው የበጐ አድራጐት ድርጅቶች እና ማኅበራት ሕግ በፓርላማ ፀድቆ በነጋሪት ጋዜጣ ከታተመ በኋላ ሰሞኑን ታግዶ በቀድሞው ሕግ ምዝገባ እንዲካሄድ መደረጉ ተገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ግንቦት 7 ንቅናቄ በስዊድን ከኢትዮጵያውያን ጋር ውይይት አደረገ

Ato Chekol & Dr. Berhanu (080621 Stockholm)By Yonatan Tsegaye

Ethiopia Zare (ሰኞ ግንቦት 10 ቀን 2001 ዓ.ም. May 18, 2009)፦ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ የሚመሩት ”ግንቦት 7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ” በተለያዩ የአውሮፓ ከተሞች እየተዘዋወረ ህዝባዊ ስብሰባ እያካሄደ ሲሆን፣ የመጀመሪያውን ህዝባዊ ውይይት ባለፈው ቅዳሜ ግንቦት 8 ቀን 2001 ዓ.ም. ከሰዓት በኋላ በርካታ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት አደረገ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በዩሮቪዥን 2009 ኖርዌይ አሸነፈች

የአልባኒያዊቷ ተወዳዳሪ ስሟ ኢትዮጵያዊ ነው፣ ‘ኬይሲ ቶላ” ትባላለች

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ግንቦት 8 ቀን 2001 ዓ.ም. May 16, 2009)፦ ዛሬ ማምሻውን በተጠናቀቀው “ዮሮቪዥን” በመባል በሚታወቀውና በሞስኮ በተካሄደው 54ኛው የአውሮፓ ሀገሮች የሙዚቃ ውድድር ኖርዌይ አሸናፊ ሆነች። “ፌሪቴይልስ” በተሰኘው ዘፈኑ ኖርዌይን አሸናፊ እንድትሆን ያደረጋት የ23 ዓመቱ አሌክሳንደር ሪባክ የተሰኘው ድምፃዊ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...