በእስራኤል ያሉ ኢትዮጲያዊያን በፍርሀት ተውጠዋል

ጠ/ሚ/ር ቤንጃሚን ናታናሁ በድምሩ 25 ሺ አፍሪካዊ ስደተኞች ባስቸኳይ ወደመጡበት እንዲመለሱ አዘዋል!

(ልዩ ሪፖርታዥ)

Ethiopia Zare (እሁድ ሰኔ 3 ቀን 2004 ዓ.ም. june 10, 2012)፦ እስራኤል ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በአገሪቱ ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ እየተባባሰ በመጣው ዘረኝነትና የኀይል ርምጃ ሳቢያ በከፍተኛ ፍርሀት ውስጥ መውደቃቸውን የተለያዩ ዓለም አቀፋዊ የዜና አውታራት እየዘገቡ ነው። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የ‹‹አራት ኪሎው›› እና ‹‹የቃሊቲው መንግስት›› ወግ

ተመስገን ደሳለኝ (አዲስ አበባ)

ሲሳይ አጌና በቅርቡ በመጀመሪያ በጀርመን፣ ቀጥሎ በአሜሪካን ሀገር ‹‹የቃሊቲው መንግስት›› የሚል ርዕስ ያለው መፅሐፍ አሳትሟል። በእርግጥ መፅሐፉ እስከአሁን ሀገር ቤት መግባት አልቻለም (ምናልባት ወደፊትም ላይገባ ይችላል) ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና በኢትዮጵያ የነፃ ፕሬስ ታሪክ የጎላ አሻራ ካላቸው ጥቂት ጉምቱ እና ትንታግ ጋዜጠኞች አንዱ ነው። ከ1986 ዓ.ም. ጀምሮ በድህረ ምርጫ 97 በተነሳው አለመግባባት ስራ እስካቆመበት ዕለት ድረስ ‹‹ኢትኦጵ›› እና ‹‹አባይ›› የተባሉ ጋዜጦችን በባለቤትነት ይመራ ነበር። በተለይ ኢትኦጵ ጋዜጣ በእጅጉ ተወዳጅ ከመሆኗም ባሻግር በስርጭትም ግንባር ቀደም እንደነበረች ይታወሳል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የጠ/ሚ መለስ ባለቤት መሬት አላግባብ መውሰዳቸውን ያጋለጠው ሠራተኛ ታሰረ

W/o Azeb Mesfin ወ/ሮ አዜብ መስፍን (ማክሰኞ ግንቦት 21 ቀን 2004 ዓ.ም. May 29, 2012)፦ በቅርቡ በቡራዩ ከተማ በከንቲባ ኩማ ደመቅሳ በተመራው ሙሰኞችን የማጋለጥ ስብሰባ ላይ “ወ/ሮ አዜብ መስፍን ያለ አግባብ በወንድማቸው ስም መሬት ወስደዋል” ብሎ ያጋለጠው የማዘጋጃ ቤቱ ሠራተኛ መታሰር በከተማው መነጋገሪያ መሆኑን የከተማው ነዋሪዎች ለፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ሪፖርተር መግለጻቸውን ጋዜጣው ዘገበ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ልዑል ኤርሚያስ የኬንታኪ ስቴትን ዋና ከተማ የክብር ቁልፍ ተረከቡ

ልዑል ኤርሚያስ ሣህለሥላሴ ኃይለሥላሴ Princ Ermias Sahleselase Haileselaseልዑል ኤርሚያስ ሣህለሥላሴ ኃይለሥላሴ የአፍሪካ አህጉር የንጹህ መጠጥ ውሃ እጥረትና የልማት አጠቃቀም ጉድለት አስቸኳይ መፍትሄ የሚሻ መሰረታዊ ችግር መሆኑን በማሳሰብ፤ ኬንታኪና አለም አቀፍ የልማት ተቋማት ድጋፋቸውን እንዲያጠናከሩ ጥሪ አቀረቡ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ተወዳጁ የኢሳት ጋዜጠኛ ንጉሴ ጋማ አረፈ

Ethiopia Zare (እሁድ ግንቦት 17 ቀን 2004 ዓ.ም. May 26, 2012)፦ ተወዳጁ የኢሳት ጋዜጠኛ ንጉሴ ጋማ በደረሰበት ድንገተኛ ህመም በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ከትላንት በስቲያ ሀሙስ ግንቦት 16 ቀን 2004 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። ንጉሴ ጋማ በነጻው ፕሬስ ቀዳማይ ዓመታት ውስጥ በተለይም "ጧፍ" ትባል የነበረችው ተወዳጅ ጋዜጣን በዋና አዘጋጅነት፣ በኋላም "አዋሽ" ጋዜጣን በማኔጂንግ ኢዲተርነት ይመራ የነበረ ዕውቅ ጋዜጠኛ ሲሆን በወቅቱ ከፕሬስ ስራው ጋር በተገናኘ እስርና እንግልት የደረሰበት አይታክቴ ጋዜጠኛ ነበር። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ክርስቲያኑ ማህበረሰብ ከሙስሊሙ ጋር እንዲተባበር ጥሪ ቀረበ

እስላሙም ወገናችን ክርስቲያኑን በመደገፍ፤ ክርስቲያኑም ወገናችን እስላሙን በመደገፍ ሁሉም እንዲነሳና ድምጹን እንዲያሰማ ጥሪየን አቀርባለሁ” ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መልከጸዲቅ

33ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅዱስ ሲኖዶስ ጠቅላላ ጉባኤ

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ግንቦት 4 ቀን 2004 ዓ.ም. May 12, 2012)፦ በስደት የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሀፊ የሆኑት ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መልከጸዲቅ በእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ እደረሰ ያለውን አስከፊ ጭፍጨፋ በማውገዝ መላ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ተከታዮች ከሙስሊሙ ማህበረሰብ ጎን እንዲቆም ጥሪ አስተላለፉ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

መለስ ዜናዊ "የአፍሪካ መሪዎች ሙስና ውስጥ የምንገባው በስግብግብ ኩባንያዎች ጫና ነው" አሉ

Ethiopia Zare(ቅዳሜ ግንቦት 4 ቀን 2004 ዓ.ም. May 12, 2012)፦ ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ የአፍሪካ መሪዎች ሙስና ውስጥ የሚዘፈቁት በወጉ የተደራጁ የውጪ ኩባንያዎች የሚያደርሱትን ጫና ለመቋቋም ስለሚያዳግታቸው መሆኑን አመላከቱ። አቶ መለስ ይህን እምነታቸውን የገለጹት በአፍሪካ ጉዳዮች ላይ ለመምከር በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው ወርልድ ኢኮኖሚክ ፎረም ላይ ትላንት (ሐሙስ ግንቦት 2 ቀን) ከአንዲት የፎረሙ ተካፋይ ከሆነች ደቡብ አፍሪካዊት ለቀረበ ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በብራስልስ የአውሮፓ ኮሚሽን የተቃውሞ ሰልፍ ተጠራ

  • የኢትዮጵያ መንግሥት በዜጎቹ ላይ እያደረሰ ያለውን የመብት ረገጣ እና እስራት በአስቸኳይ ያቁም!!
  • በኃይማኖቶች ላይ ጣልቃ መግባቱን እና ዜጎችን ማፈናቀሉን ያቁም!!

Ethiopia Zare (ሐሙስ ግንቦት 2 ቀን 2004 ዓ.ም. May 10, 2012)፦”መብታችን ይከበር!” በሚል በኢትዮጵያ ሙስሊሞች የተጀመረውን እንቅስቃሴ በመደገፍና ”የኢህአዴግ መንግሥት በዜጎች ላይ እያደረሰ ያለውን የመብት ረገጣ፣ እስራት፣ በኃይማኖቶች ላይ ጣልቃ መግባቱንና ዜጎችን ማፈናቀሉን ያቁም!” በሚል መሪ መፈክር የፊታችን ሜይ 16 ቀን 2012 በብራስልስ የአውሮፓ ኮሚሽን ሕንፃ ፊት ለፊት የተቃውሞ ሰልፍ ተጠራ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በሙስሊሞች ጉዳይ ውጥረቱ እንዳየለ ነው

የፌደራል ጉዳዮች ሚ/ር አዲስ መግለጫ አወጣ

Ethiopia Zare (አርብ ሚያዚያ 26 ቀን 2004 ዓ.ም. May 4, 2012)፦ "መንግስት የሙስሊሙ ማህበረሰብ ውክልና የሌለውን የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ጉባዔን በመጠቀም 'አህባሽ' የተባለውን አስተምህሮ በግድጅ ሊጭንብን እየሞከረ ነው " በሚል በእስልምና ሀይማኖት ተከታዮች ዘንድ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ እንደቀጠለ ሲሆን መንግስት ዓላማውን ለማስፈጸም የሀይል እርምጃን መምረጡም ውጥረቱን ይበልጥ እያባባሰው መጥቷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጤነኛ ነኝ አሉ

ጥርጣሬው እስካሁን አልቆመም

Ethiopia Zare (እሁድ ሚያዚያ 21 ቀን 2004 ዓ.ም. April 29, 2012)፦ የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከአንድ ወር በላይ ለሆነ ጊዜ ከህዝብ ዕይታ ተሰውረው መቆየታቸውን ተከትሎ በከፍተኛ ሁኔታ ታመዋል በሚል በኤርትራዊያን ዘንድ በስፋት መነጋገሪያ ሆነው ቢቆዩም በትላንትናው ዕለት በኤርትራ ቴሌቪዚን ቀርበው "ያስወሩብኝ ጠላቶቼ ናቸው" ሲሉ አስተባብለዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ