የኢትዮጵያ ወታደሮች በባድሜ በኩል ድጋሚ ጥቃት ሰነዘሩ

Ethiopia Zare (ቅዳሜ መጋቢት 9 ቀን 2004 ዓ.ም. March 17, 2012) የኤርትራ መንግስት ኢትዮጵያ ድንበሬን ጥሳ ለፈጸመችበት ጥቃት ጠንካራ እርምጃ ሊወሰድባት ይገባል በማለት ለጸጥታው ምክር ቤት ክስ ባቀረበች በማግስቱ የኢትዮጵያ ወታደሮች ዛሬ አዲስ ጥቃት መሰንዘራቸውን ሮይተርስ ዘገበ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

“ኢትዮጵያችን ሁሉም አይነት ሴቶች ያስፈልጓታል” አቶ ኦባንግ ሜቶ

Obang Metho አቶ ኦባንግ ሜቶ Ethiopia Zare (መጋቢት 7 ቀን 2004 ዓ.ም. March 16, 2012)፦ የአገራችን ግማሽ ህዝብ የሚሆኑትን ሴት እህቶቻችን ያልተሳተፉበት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ ምስረታ ስኬቱ ያማረ እንደማይሆን፣ ቢሆንም ራሱን ለጥፋት እንደሚያጋልጥ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ተናገሩ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በቤይሩት ስቃይ የደረሰባት ወጣት ኢትዮጵያዊት ሞተች

አንዳንዶች ”ራሷን አጠፋች” የተባለው ለሽፋን ነው ይላሉ

Ethiopia Zare (ረቡዕ መጋቢት 5 ቀን 2004 ዓ.ም. March 14, 2012)፦ በሊባኖስ ዋና ከተማ ቤይሩት የኢትዮጵያ ቆንጽላ ፊት ለፊት በሊባኖሳውያኑ ዓሊ ማህፉዝና ግብረአበሮቹ ፀጉሯንና ክንዷን በመጎተት እያሰቃዩ በመኪና አፍነው የወሰዷት የ33 ዓመትዋ ወጣት ዓለም ደቻሳ ዛሬ ጠዋት ራስዋን እንዳጠፋች ተገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በቤይሩት ጎዳና በኢትዮጵያዊቷ ላይ የተፈጸመው ግፍ ክፉኛ ቁጣ አስነስቷል

Ali Mahfouz ወጣት ዓለም ደቻሳን አሰቃይቶና አንገላቶ በመኪና ያፈናት ዓሊ ማህፉዝ“አጥቂው ላይ ተገቢ ርምጃ እንዲወሰድበት ወስነናል” የሊባኖ የሥራ ሚኒስትር

Ethiopia Zare (ረቡዕ መጋቢት 5 ቀን 2004 ዓ.ም. March 14, 2012)፦ በሊባኖስ መዲና ቤይሩት ውስጥ ካለው የኢትዮጵያ ቆንጽላ ጽ/ቤት ፊት ለፊት በአንዲት ኢትዮጵያዊት ወጣት ላይ ድብደባና እንግልት ሲፈጽምባት የሚያሳይ ፊልም ከተሰራጨ ወዲህ በአለም ዙሪያ በሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ዘንድ ክፉኛ ቁጣ እንዳስነሳ የተለያዩ አለም አቀፍ የዜና አውታራት ዘገቡ።

 

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በጋምቤላ ሃያ ወንድ የኮሌጅ ተማሪዎች በጥይት ተገደሉ

አምስቱ ክፉኛ ቆስለዋል

Ethiopia Zare (ረቡዕ መጋቢት ቀን 2004 ዓ.ም. March 14, 2012)፦ ከትናንት በስቲያ ሰኞ መጋቢት 3 ቀን 2004 ዓ.ም. ከቀኑ 10 ሰዓት አካባቢ ከጎደሬ ወደ ጋምቤላ በሚጓዝ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ላይ ተሳፍው የነበሩ 25 ወንዶች ተማሪዎችና ወጣቶች ካርሚ በምትባል ስፍራ ላይ በጥይት ተደብድበው 20ዎቹ ሲሞቱ 5ቱ ደግሞ ክፉኛ ቆስለዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በኑሩንበርግ ከተማ (ጀርመን) የተካሄደው ህዝባዊ ስብሰባ

በጀርመኗ የኑሩንበርግ ከተማ ፌብሩዋሪ 17 እና 18 ቀን 2012 ዓ.ም. የከተማዋና የአካባቢው ነዋሪዎች ህዝባዊ ስብሰባ አካሂደዋል። ፌብሩዋሪ 17 ቀን ከሂዩማን ራይት ዎች ጋር በትብብር በተዘጋጀው ውይይት ላይ የሕግ ባለሙያዎች፣ የፖለቲካ ድርጅቶች ተወካዮች፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች፣ የበጎ አድራጎት ድርጅት ተወካዮች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የኢትዮጵያውያን ስደተኞች ተወካዮች ተገኝተዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የጨካኙና የአረመኔው ጆሴፍ ኮኒ አደን ኢንተርኔትን አጨናነቀ

ጆሴፍ ኮኒ በኡጋንዳ ከ60 ሺህ በላይ ሕፃናትን ጠልፏል

Ethiopia Zare (ዓርብ የካቲት 30 ቀን 2004 ዓ.ም. March 9, 2012)፦ የኡጋንዳው የጎሬላ ተዋጊዎችና "የጌታ ተጋዳይ ሠራዊት" (Lord’s Resistance Army - LRA) መሪ የሆነውን ጨካኙንና አረመኔውን ጆሴፍ ኮኒን ለማደን በኢንተርኔት የተሰራጨው የ30 ደቂቃ ቪዲዮ በአራት ቀን ውስጥ በዩቲዩብ ብቻ ወደ 60 ሚሊዮን ተመልካቾችን ማግኘቱ ታወቀ። የቪዲዮው ዓላማ ጨካኙን በዓለም ላይ ታዋቂ በማድረግ በቁጥጥር ስር ለማዋል ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የቀድሞ የዩኒቲ ኮሌጅ ባለቤት የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ ጠየቁ

“ነገሮች እዚህ ደረጃ ላይ እስኪደርሱ ዝም ብለን በመመልከታችን ይቅርታ ልጠይቅ እፈልጋለሁ” ዶ/ር ፍስሓ እሸቱ

Ethiopia Zare (ረቡዕ የካቲት 28 ቀን 2004 ዓ.ም. March 7, 2012)፦ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ባለቤት የነበሩት ዶ/ር ፍስሐ እሸቱ የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ይህ ሁሉ በደል ሲደርስ ዝም ብለው መመልከታቸው አግባብ እንዳልነበረ ገልጸው የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ ጠየቁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በጋምቤላ ሜካናይዝድ ኃይል ተሰማራ

ኃይለማርያም ደሳለኝና ኦሞት ኦባንግ ደቡብ ሱዳንን አስጠነቀቁ

ሦስት የጥበቃ ኃይሎች ተገድለዋል፣ አንድ ቆስሏል

በጋምቤላ ክልል የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ በርካታ ወታደሮችንና ብረት ለበስ የጦር መሳሪያ በማሰማራት አውጫጪኝ እያካሄደ እንደሆነ ተሰማ። የአገዛዙ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የክልሉ ፕሬዚዳንት ወደ ደቡብ ሱዳን አመሩ። ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች ጥቃት ሲፈጽሙ የኢታንግ ወረዳ መምህራን ስራ ማቆማቸው የክልሉን ውጥረት መባባስ እንደሚያሳይ ተዘገበ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

2ቱ ጀርመናዊያን ታጋቾች ተለቀቁ

"ያቆየኋቸው የኢትዮጵያ ወታደሮች መንገድ ዘግተውብኝ ነው" - አርዱፍ

Ethiopia Zare (ረቡዕ የካቲት 28 ቀን 2004 ዓ.ም. March 7 , 2012) የአፋር አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት ግንባር (አርዱፍ) ላለፉት 7 ሳምንታት ያህል አግቶ ያቆያቸውን ሁለት ጀርመናዊያን ጎብኚዎች ለአካባቢው ሽማግሌዎችና በኢትዮጲያ ለጀርመን ኤምባሲ ተወካዮች አሳልፎ እንደሰጠ ትላንት ማክሰኞ የካቲት 27 ቀን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ