አንድ ሄክታር መሬት ከሃያ ብር ባነሰ

በኢትዮጵያ እየተካሄደ ስላለው የመሬት ነጠቃ የተዘጋጀ ልዩ ጥናታዊ ዘገባ

መንግሥት ከቀያቸው ያፈናቀላቸው ነዋሪዎች Government displace people

Ethiopia Zare (ዓርብ ሰኔ 3 ቀን 2003 ዓ.ም. June 10, 2011)፦ አንድ ሄክታር መሬት በአንድ ዶላር ከ19 ሣንቲም (በኢትዮጵያ ከሃያ ብር ባነሰ ገንዘብ) በ”ኢንቨስትመንት” ስም ለ99 ዓመታት በሚቆይ ሊዝ የኢህአዴግ መንግሥት የኢትዮጵያን መሬት እየቸበቸበ፤ ህዝቡን ለዘመናት ከኖረበት ቀዬ እያፈናቀለ መሆኑን የኦክላንድ ተቋም እና የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ በቅንጅት ባካሄዱት የጥናት ዘገባ ገለፁ። 

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በኦጋዴን አካባቢ ውጥረቱ ተባብሷል

'የአለም ምግብ ድርጅት ታጋቾችን ነጻ አውጥቻለሁ' ኦብነግ

Ethiopia Zare (ሐሙስ ግንቦት 25 ቀን 2003 ዓ.ም. June 2, 2011)፦ በኦጋዴን ክልል የትጥቅ ትግል የሚያካሂደው የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻነት ግንባር በቅርቡ ባደረገው ከፍተኛ የጥቃት እርምጃ ጂጂጋ አካባቢ የሚገኘውን የጋላሽ ከተማን ተቆጣጥሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ እስረኞችን ነጻ ማውጣቱንና ብዛት ያላቸው የጦር መሳሪያዎችን መማረኩን ገልጿል። 

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የደርግ ባለስልጣናት የሞት ፍርድ ወደ እድሜ ልክ ተቀየረ

የ23ቱን ስም ዝርዝር ይዘናል

Ethiopiaz Zare (ረቡዕ ግንቦት 24 ቀን 2003 ዓ.ም. June 1, 2011)፦ በመጥፎነቱ የሚታወቀው በቀድሞው የኢትዮጵያ መንግስት አመራሮች በእነ ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለምሪያም ክስ መዝገብ ስር በዘር ማጥፋት ወንጀል ተከሰው የሞት ፍርድ የተወሰነባቸው የደርግ ባለስልጣናት የቅጣት ውሳኔ ወደ እድሜ ልክ መለወጡ ተገለጸ። 

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአንድነት ኃይሎች ስብሰባ በቶሮንቶ

(ከግራ ወደ ቀኝ: ዶ/ር ወንድሙ መኮንን፤ ዶ/ር ቡሻ ታዓና አቶ መሥፍን ተፈራ)(ዘጋቢ፡ መላኩ አወቀ)

በኢሕአፓ(ዴ) የቶሮንቶና አካባቢው የድጋፍ ኮሚቴ አባላት አዘጋጅነትና በአንድነት ኃይሎች፤ በሲቪክ ማኅበራትና ታዋቂ ግለሰቦች ትብብርና ግምባር-ቀደምነት ወደፊት ሊመሠረት የታሰበውን ሕብረት እውን ለማድረግ ጥረት ሲያደርጉ በቆዩትና አሁን እያደረጉ ባሉት አሰባሳቢ የሲቪክ ማኅበራት፤ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮችና ግለሰቦች ትብብር ሜይ 14, 2011 (እ.ኤ.አ) በቶሮንቶ ዩኒቨርስቲ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ብዙ ሰዓት የወሰደና አወያይና ተወያይ ልብ ከልብ የተገናኙበት ስብሰባ ተደርጓል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአለም ምግብ ድርጅት ሰራተኛ መገደል እያወዛገበ ነው

ሁለት ሰራተኞች የደረሱበት አልታወቀም

Ethiopia Zare (ረቡዕ ግንቦት 10 ቀን 2003 ዓ.ም. May 18, 2011)፦ ባለፈው ሳምንት አርብ አንድ የአለም አቀፉ የምግብ ድርጅት ሰራተኛ ባልታወቁ ታጣቂዎች ከተገደለና ሁለት ተጨማሪ ሰራተኞች መጥፋታቸው ከተገለጸጸ ወዲህ ገዥው መንግስትና በተቃዋሚው የኦጋዴን ብሄራዊ ነጸጻነት ግንባር የተካረረ ሰጣ ገባ ጀምረዋል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ድርጅትን ለመርዳት 27ሺህ ዶላር ተሰበሰበ

Ethiopia Zare (ሰኞ ግንቦት 8 ቀን 2003 ዓ.ም. May 16, 2011)፦ የኢትዮጵያዊነት ውርስና ቅርስ ማህበርን ለመርዳት ከተለያዩ የአሜሪካና ካናዳ ግዛቶች የተሰባሰቡበት የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ላይ ከ27ሺህ የአሜሪካ ዶላር በላይ መሰብሰቡ ተገለጸ። በርካታ ኢትዮጵያዊያንና ተጋባዥ ተናጋሪዎችም በስፍራው ተገኝተው ለማህበሩ ያላቸውን ድጋፍ ገልጸዋል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

አቶ ስዬ አብርሓ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጡ

[ሊያነቡት የሚገባ!]

“አውቃቸዋለሁ! በዚህች ሰዓት ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ናቸው”

“90 በመቶ የሚሆኑት ጀኔራሎች ከትግራይ መሆናቸው ስህተት ነው”

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ግንቦት 3 ቀን 2003 ዓ.ም May 10, 2011)፦ የቀድሞው የመከላከያ ሚኒስትር የአሁኑ የአንድነት ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ስዬ አብርሃ በሀገሪቱ ወቅታዊና ተጨባጭ ሁናቴዎች ላይ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የቶሮንቶው ስብሰባ የተሳካ ነበር

“ሕወሀት/ኢህአዴግ በማሳ ውስጥ እንደበቀለና እህሎቹን እንደሚያቀጭጭ አንድ አላስፈላጊ ዛፍ ነው” አቶ አሎ አይደሂስ

“እድሜ ልካችንን በማይረቡ ነገሮች ስንጨቃጨቅ ከምንኖር የ“የምክንያት ወይንም የአላማ አንድነት እንፍጠር” አቶ መሀመድ ሀሰን

“ኢትዮጵያ ውስጥ ያንዱ ብሄር ችግር የዚያ ብሄር ብቻ ሳይሆን የሁሉም ኢትዮጵያዊ ችግር ነው” አቶ አበበ በለው

“ከብሄራችንም በፊት ሰውነታችን መቅደም አለበት” አቶ ኦባንግ ሜቶ

“የአንድነትም ይሁን የነጻነት አራማጆች ጽንፈኛነታቸውን ትተው ወደመሀል በመምጣትን ያዳብሩ” አቶ ጁዋር መሀመድ

Ethiopia Zare (እሁድ ግንቦት 2 ቀን 2003 ዓ.ም May 8, 2011)፦ ቅዳሜ ሜይ 7 ቀን በካናዳ የንግድ ከተማ ቶሮንቶ ከተለያዩ ማህበረሰብ የተወጣጡ ኢትዮጵያዊያን ተናጋሪዎችና ተሳታፊዎች የነበሩበት የተሳካ የበቃ ንቅናቄ ስብሰባ ተካሄደ። ተጋባዥ እንግዶቹም አብሮ የመስራትና የጋራ ዓላማን የሚያሳይ የአቋም መግለጫ አወጡ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...