ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ለመጀመሪያ ጊዜ በአደባባይ ልትናገር ነው

Ethiopia Zare (አርብ ሰኔ 24 ቀን 2011 .. July 1 , 2011):-  በዋሽንግተን ዲሲ በኢትዮጵያዊያን ውርስና ቅርስ አዘጋጅነት በሚካሄደው ታላቅ ፌስቲቫል ወ/ት ብርቱካን ሚዴቅሳ ለመጀመሪያ ጊዜ በአደባባይ ህዝብ ፊት ቀርባ ንግግር ልታደርግ መሆኑን ባልደረባችን ተክለሚካኤል አበበ ከስፍራው አስታወቀ። ዝርዝሩን እንደሚከተለው አቅርቦታል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በአዲስ አበባ "ለቡኤርቱ" የተባለ ሰፈር 1027 ቤቶች ፈረሱ

                    አንድ ነዋሪ ድልድይ ውስጥ ራሱን ወርውሯል ሁለቱ በጅብ ተበልተዋል

Ethiopia Zare (ሐሙስ ሰኔ 23 ቀን 2011 ዓ.ም. June 30, 2011):-  ለቡኤርቱ በተባለ ሰፈር ከ1994 ዓ.ም ጀምሮ የተገነቡ 1027 ቤቶች መፍረሳቸውንና ከቤቶቹ ባለቤቶች አራቱ ህይወታቸውን ማጥፋታቸውን የአዲስ አበባ ምንጮቻችን አስታወቁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አድባር የክርክር ክበብ የመጀመሪያውን መድረክ አዘጋጀ

ባህላችን በፖለቲካችን ያለው ገጽታ አዎንታዊ ወይንስ አሉታዊ?

Ethiopia Zare (አርብ ሰኔ 17 ቀን 2011 ዓ.ም. June 24, 2011):- በካናዳዋ ዋናየንግድ ከተማ ቶሮንቶ የተቋቋመው አድባር የክርክር ማህበር ለመጀመሪያ ጊዜ በሚያዘጋጀው መድረክ ጋዜጠኛና የህግ ተማሪ የሆነው ዳንኤል ጥላሁንና የሲቪል ኢንጂኒዬሪንግ ምሩቅ የሆነው ወጣት ኪሩቤል ፍሬው በሚያካሂዱት ክርክር እንደሚጀመር ተገለጸ። 

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአውራምባ ታይምስ ም/ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ታሰረ

”ጉዳዩ ከጋዜጣዋ ጋርም ሆነ ከሙያው ጋር ተያያዥነት የለውም” የመንግሥት የፀጥታ ተቋማት

”ጋዜጠኛው ለእስር የተዳረገበትን ምክንያትና የሚገኝበትን ሁኔታ መንግሥት ያሳውቀንአውራምባ ታይምስ

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ሰኔ 14 ቀን 2003 ዓ.ም. June 21, 2011)፦ የአውራምባ ታይምስ ም/ዋና አዘጋጅ የሆነው ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ እሁድ ሰኔ 12 ቀን 2003 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት አካባቢ በርካታ ቁጥር ባላቸው የፀጥታ ኃይሎች ተይዞ ከመኖሪያ ቤቱ መታሰሩን አውራምባ ታይምስ ከቤተሰቦቹ ማረጋገጡን ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በሕወሐት ወዳጅነት የሚታወቀው የሲ.አይ.ኤ ከፍተኛ ሰላይ በሞት ተለየ

  • አሜሪካዊው ሰላይ በለንደኑ ጉባኤ ቁልፍ ሰው ነበር
  • የደርግ ደህንነት ሹም ኮ/ል ተስፋዬ ቀብር ተፈጸመ

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ሰኔ 7 ቀን 2003 ዓ.ም. June 13, 2011)፦ የሕወሀት ጥብቅ ወዳጅና ከደርግ መንግስት ውድቀት በፊት የለንደኑ ጉባኤ አቀናባሪ ፖል ሄንዝ ህይወት ማለፉ ተሰማ። የደርግ የደህንነት ሹም ኮ/ል ተስፋዬ ወ/ስላሴ ቀብር ስነስርአት ተፈጸመ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

በኤርትራ የእሳተ ገሞራ ፈነዳ

ሂላሪ ክሊንተን የአዲስ አበባ ጉብኝታቸውን አቋረጡ

Ethiopia Zare (ሰኞ ሰኔ 6 ቀን 2003 ዓ.ም. June 13, 2011)፦ ትላንት እሁድ ምሽት ላይ በቀይ ባህር በስተደቡብ ክልል በተከሰተ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ምክንያት በአዲስ አበባ የነበሩት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ሂላሪ ክሊንተን በአፋጣኝ ሀገር መልቀቃቸው ተዘገበ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

አባይን ለመገደብ በሚል በመላ ሀገሪቱ የሚሰበሰብ ገንዘብ መጠን አልተገለጸም

ለሸቀጦች ዋጋ ከፍ ዝቅ ማለት ምክንያት ሆኗል ተባለ

Ethiopia Zare (ሰኞ ሰኔ 6 ቀን 2003 ዓ.ም. June 13, 2011)፦ አባይን ለመገደብ ከህዝብ የሚሰበሰበውንና ከቦንድ ሽያጭ የሚገኘውን ገንዘብ መንግስት ወደ ካዝና ማስገባቱ ለዋጋ ግሽበቱ ጠንቅ ሊሆን እንደሚችል የኢኮኖሚ ተንታኞች ስጋታቸውን ገለጹ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የዶ/ር ታዬ ወልደሰማያት ባለቤት ወ/ሮ አስቴር አረፉ

Ethiopia Zare (ሰኞ ሰኔ 6 ቀን 2003 ዓ.ም. June 13, 2011)፦ የአንጋፋው የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር መሪ የነበሩት የፖለቲካ ሳይንቲስት ዶ/ር ታዬ ወልደሰማያት ባለቤት ከዚህ አለም በሞት መለየታቸውንና የቀብር ስነ ስርአታቸውም በእስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን መፈጸሙን የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች ከአዲስ አበባ ገለጹ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከኖርዌይ ወደ ስዊድን ገቡ

በአዶልፍ ፍሬድሪክ ቤተክርስቲያን ተጠልለዋል

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ሰኔ 4 ቀን 2003 ዓ.ም. June 11, 2011)፦ ለረጅም ዓመታት በኖርዌይ ይኖሩ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የደረሰባቸውን በደል ለሌሎች መንግሥታት ለማሳወቅና ተቀባይ ሀገር ለመፈለግ ወደ ስዊድን ገብተው በአዶልፍ ፍሬድሪክ ቤተክርስቲያን መጠለላችውን የስደተኖቹ ተወካይ አቶ ልዑል ታደሰ ለኢትዮጵያ ዛሬ ገለጹ። 

ሙሉውን አስነብበኝ ...