አባይ መወያያ ይሆናል

በቶሮንቶ ስብሰባ ጁዋር መሀመድ፣ ኦባንግ ሜቶ፣ አቶ መሐመድ ሐሰንና አበበ በለው ይናገራሉ

Ethiopia Zare (ሐሙስ ሚያዝያ 29 ቀን 2003 ዓ.ም May 5, 2011)፦ ብዙ ኢትዮጵያዊያኖች ይኖሩበታል በተባለለት ቶሮንቶ ከተማ የፖለቲካ ሳይንስ ተመራማሪው ወጣት ጁዋር መሐመድ፣ የሰብአዊ መብት ተከራካሪው ኦባንግ ሜቶ፣ አቶ መሀመድ ሀሰንና የአዲስ ድምጽ ራዲዮ አስተናጋጅ አበበ በለው የሚገኙበት ህዝባዊ ስብሰባ መሰናዳቱንና የአባይ ግድብን በሚመለከት ሰፊ ውይይት እንደሚደረግ አዘጋጆቹ በተለይ ለኢትዮጵያ ዛሬ ገለጹ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በኦታዋ ኢሳትን ለመርዳት ከ6500 ዶላር በላይ ተሰበሰበ

ዶ/ር ብርሀኑ ነጋ ተናጋሪ እንግዳ ነበሩ

Ethiopia Zare (ሰኞ ሚያዝያ 26 ቀን 2003 ዓ.ም May 2, 2011)፦ የኦታዋ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን፡ ከአርብ ኤፕሪል 29 እስከ ቅዳሜ ኤፕሪል 30 ባደረጉት የተሳካ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅት የወርሀዊ መዋጮ ቅጽ የሞሉትን ሳይጨምር ከስድስት ሺህ አምስት መቶ ብር መሰብሰባቸውንና ከዶ/ር ብርሀኑ ነጋ ጋርም የተሳካ ውይይት ማድረጋቸው ተገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በካናዳዋ መናገሻ ኦታዋ ለኢሳት ገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ተጧጡፏል

Ethiopia Zare (ሐሙስ ሚያዝያ 13 ቀን 2003 ዓ.ም April 21, 2011)፦ በካናዳ ዋና ከተማ ኦታዋ በያዝንው ወር ቅዳሜ ሚያዚያ 30 ቀን ለኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥን ማጠናከሪያ የሚሆን የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ አርቲስት ታማኝ በየነና የተለያዩ የካናዳ የፖለቲካ ሰዎች በተገኙበት እንደሚካሄድ ተገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የጋዜጠኞችና የጋዜጦች ህልውና አደጋ ላይ ነው

የአንድ ጋዜጣ ዋጋ 7ብር ገብቷል

Ethiopia Zare (ሐሙስ ሚያዝያ 13 ቀን 2003 ዓ.ም April 21, 2011)፦ ሰሞኑን በጋዜጦችና በጽሔቶች ላይ የተደረገው የዋጋ ጭማሪ በርካታ ጋዜጦችንና ጋዜጠኞችን ከስራ ውጭ እንደሚያደርጋቸው እና የህትመት ስራ በአጠቃላይ ከፍተኛ አደጋ ውስጥ መሆኑ ተገለጸ።

 

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ለኢሳት ገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በኦታዋ

Ethiopia Zare (ሐሙስ ሚያዝያ 13 ቀን 2003 ዓ.ም April 21, 2011)፦ በካናዳ ዋና ከተማ ኦታዋ በያዝንው ወር ቅዳሜ ሚያዚያ 30 ቀን ለኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥን ማጠናከሪያ የሚሆን የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ አርቲስት ታማኝ በየነና የተለያዩ የካናዳ የፖለቲካ ሰዎች በተገኙበት እንደሚካሄድ ተገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በቃ! ገዬ! በስ! አሎኒ! ጊደስ!

Beqa! Sweden, Stockholm April 08, 2011በስዊድን የኢትዮጵያውያን የሰልፍ ውሎ

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ሚያዝያ 1 ቀን 2003 ዓ.ም April 9, 2011)፦ ትናንት ዓርብ መጋቢት 30 ቀን 2003 ዓ.ም. ትንሽ ትንሽ፣ ብን ብን ከሚለው ዝናብ በስተቀር ይሄን ያህል ብርድ አልነበረም። የስዊድን ክረምት (ዊንተር) ከመቼውም በበለጠ ሁኔታ እንኳን ለስደተኛው ለዜጋውም አልገፋ ብሎ በረዶው በአንዳንድ ከተሞች ከመሬቱ አልላቀቅ ብሎ ሙጭጭ ያለበት ዓመት ነው - የአውሮጳውያኑ 2011። የአየሩ ፀባይ አፈር ሲሉት ውሃ እንደሆነ የሚያውቀው ኢትዮጵያዊ ግን የክረምት ልብሱን አልወጠም። በሻርፕ ተጠቅሏል፤ ኮፍያውንም አልጣለም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በአደስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተቃውሞ ሰልፍ ጥሪ ወረቀት ተበተነ

በኦሮሞ ተወላጆች ላይ እስራቱ ቀጥሏል

Ethiopia Zare (አርብ መጋቢት 16 ቀን 2003 ዓ.ም. March 25, 2011)፦ ከእረፍት በኋላ ወደ ትምህርት ገበታቸው ለተመለሱ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሰኞ ጠዋት የተቃውሞ ሰልፍ እንዲወጡ የሚጠይቅ በራሪ ጽሁፍ በግቢው ውስጥ መበተኑን ምንጮች ገለጹ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አመጽ ሊያስነሱ እንደሚችሉ ተነበየ

በእረፍት ላይ የሰነበቱት ተማሪዎች ወደግቢ እየተመለሱ ነው

ጠንካራ ፖለቲካዊ ጽሁፎችን በመጻፍና ድፍረት የተሞላባቸውን ሀሳቦች በማስተጋባት የሚታወቀው፡ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፡ ከእረፍት እየተመለሱ ያሉት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች እንደ ግብጽና ቱኒዚያ አጋሮቻቸው የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ ሁኔታ ሊቀይር የሚችል አመጽ ሊያስነሱ እንደሚችሉ ተነበየ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ማብራሪያ ሊሰጥ ነው

Ethiopia Zare ( ቅዳሜ መጋቢት 3 ቀን 2003 ዓ.ም. March 12, 2011)፦ ሚኒሊክ፣ አስኳልና ሳተናው በተባሉት ጋዜጦቹ የሚታወቀውና በአሁኑ ሰዓት በህትመት ስራ ላይ እንዳይሳተፍ የታገደው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፤ በተለይ ለአቶ መለስ ዜናዊ በጻፈው ግልጽ ደብዳቤና በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳዮች ዙሪያ በሬዲዮ ውይይት እንደሚያደርግ ተገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...