መኢአድ በአራተኛው ዙር የፓርቲዎች ክርክር ለመጀመሪያ ጊዜ ተሳተፈ

Ethiopia Zare (ዓርብ መጋቢት 10 ቀን 2002 ዓ.ም. March 19, 2010)፦ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሲካሄድበት የቆየው የፓርቲዎች ክርክር አራተኛው ክፍል ዛሬ ዓርብ መጋቢት 10 የተጀመረ ሲሆን፤ በቀደሙት ሦስት የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በክርክሩ ያልተሳተፈው የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ለመጀመሪያ ጊዜ ተሳታፊ ሆኗል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሃሳብን በነፃ የመግለጽ ሽልማት ሥነሥርዓት ተካሄደ

(ከግራ ወደ ቀኝ) አና ኦተርሆልም እና ወ/ሮ ሶፊያ ብርሃነ Ethiopia Zare (ረቡዕ መጋቢት 8 ቀን 2002 ዓ.ም. March 17, 2010)፦ ባለፈው እሁድ መጋቢት 5 ቀን 2002 ዓ.ም. (ማርች 14 ቀን 2010 እ.ኤ.አ.) በኖርዌይ ኦስሎ ከተማ በተካሄደው የኖርዌይ ደራሲያን ማኅበር ዓመታዊ ጉባዔ ላይ የእ.ኤ.አ. 2009 ሃሳብን በነፃ የመግለጽ ሽልማት ሥነሥርዓት ተካሄደ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

አርቲስት ሌ/ኮሎኔል ሣህሌ ደጋጎ በ79 ዓመቱ አረፈ፣ ሥርዓተ ቀብሩ ተፈፀመ

Artist Sahele Degago's Funeral, 15th March 2010“ሞተዋል” የተባሉት አትሌት ዋሚ ቢራቱ በሌ/ኮሎኔሉ ለቅሶ ላይ ተገኝተዋል

አርቲስት ሌ/ኮሎኔል ሳህሌ ደጋጎ, Sahle DegagoEthiopia Zare (ሰኞ መጋቢት 6 ቀን 2002 ዓ.ም. March 15, 2010)፦ አንጋፋው የሙዚቃ መሣሪያ ተጫዋች፣ ገጣሚ፣ የዜማ ደራሲ እና የሙዚቃ አቀናባሪ ሌተናል ኮሎኔል ሣfህሌ ደጋጎ የቀብር ሥነሥርዓት ዛሬ መጋቢት 6 ቀን 2002 ዓ.ም. ከቀኑ በዘጠኝ ሰዓት በአዲስ አበባ ከተማ ፈረንሣይ ለጋሲዮን በሚገኘው በገነተ-ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ዛሬ ተፈፀመ። ሌ/ኮሎኔል ሣህሌ በ79 ዓመቱ በትናንትናው ዕለት ነበር ያረፈው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢንጂንየር ግዛቸውና አቶ ስዬ ወደ መቀሌ ያመራሉ

‘ዘመቻው ተጧጡፎ ቢቀጥልም መድረኩም ሆነ ዓረና ከምርጫው አይወጡም’ አቶ ገብሩ አስራት

Ethiopia Zare (ረቡዕ መጋቢት 1 ቀን 2002 ዓ.ም. March 10, 2010)፦ ኢንጂንየር ግዛቸው እና አቶ ስየ አብርሃ ወደ መቀሌ የሚያመሩት እሁድ መጋቢት 5 ቀን 2002 ዓ.ም. መድረክ በትግራይ በሚያደርገው የምርጫ ቅስቀሳ ላይ ተሳትፎ ለማድረግና በትግራይ ክልል የድርጅታቸውን የምርጫ ሂደት ለመከታተል መሆኑን በአዲስ አበባ የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች ጠቆሙ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

አቶ ስየ አብርሃ ለቢቢሲው ዘገባ ምላሽ ሰጡ - ‘ዝም ብዬ አልቀመጥም’ ሲሉ ተደምጠዋል

“ባይጫኑን! ባይገፉን! ጥሩ ነው፤ ከተጫኑን ግን ሁሉን ነገር ይፋ እናወጣዋለን!” አቶ ስየ አብርሃ

Ethiopia Zare (ረቡዕ መጋቢት 1 ቀን 2002 ዓ.ም. March 10, 2010)፦ አቶ ስየ አብርሃ እና ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ አሁንም በመከላከያ ሚኒስትርነትና በፕሬዝዳንትነት ሲያገለግሉት የነበረውን የህወሓት/ኢህአዲግ አገዛዝ ከመንቀፋቸውም በላይ አቶ ስየ አብርሃ ከፍተኛ ትኩረት ለሳበው የቢቢሲ ዘገባ ምላሽ ሰጥተዋል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

መድረክ ህዝባዊ ስብሰባውን እያካሄደ ነው

የመድረክ የካቲት 28 ቀን 2002 ዓ.ም. ህዝባዊ ስብሰባ“ህዝቡ ፈርቶና ተሸማቆ መኖር የለበትም” የመድረኩ አመራር

Ethiopia Zare (ረቡዕ መጋቢት 1 ቀን 2002 ዓ.ም. March 10, 2010)፦ ህዝቡ ለነፃነቱ መስዋዕትነት መክፈል እንደሚኖርበት እና ፈርቶና ተሸማቆ መኖር እንደሌለበት የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች አንድነት መድረክ (መድረክ) የካቲት 28 ቀን ከቀትር በኋላ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ባካሄደው ህዝባዊ ስብሰባ ላይ ገለጸ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኖርዌይ ደራስያን ማኅበር ደራሲና ጋዜጠኛ ዳዊት ይስኃቅን የ2009 ዓ.ም. ተሸላሚ አደረገ

Playwright, writer & journalist Dawit Issak ፀሐፊ ተውኔት፣ ደራሲና ጋዜጠኛ ዳዊት ይስኃቅማትያስ ከተማ ከስቶክሆልም

Ethiopia Zare (ዓርብ የካቲት 26 ቀን 2002 ዓ.ም. March 5, 2010)፦ ከተመሰረተ ከመቶ ዓመት ዕድሜ በላይ ያስቆጠረውና ብዙ እውቅ ደራስያንና ጋዜጠኞችን በላቀ የሥራ ውጤታቸው ሲሸልም የቆየው የኖርዌይ ደራስያን ማኅበር፤ የ2009 (እ.ኤ.አ.) ሃሳብን በነፃ የመግለጽ ሽልማቱን ስዊዲሽ-ኤርትራዊ ለሆነውና በኤርትራ በእስር ላይ ለሚገኘው ፀሐፊ ተውኔት፣ ደራሲና ጋዜጠኛ ዳዊት ይስኃቅ ሰጠ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ዜና ማርቆስ ጊዜያዊ የቀብር ሥነሥርዓት ተፈጸመ

የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ዜና ማርቆስ ጊዜያዊ የቀብር ሥነሥርዓት ዋና ቀብራቸው ቴክሳስ በሚቋቋመው ታላቅ ገዳም ይደረጋል

Ethiopia Zare (ሰኞ የካቲት 15 ቀን 2002 ዓ.ም. February 22, 2010)፦ የሕይወት ዘመናቸውን በሙሉ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሰጥተው፤ በመማር በማስተማርና ከትንሽ እስከ ታላላቅ የአገልግሎት ክፍሎች በማገልገል ያሳለፉት አቡነ ዜና ማርቆስ በስደት ባቋቋሙት የሲያትል ቅ/ገብርኤል ቤተክርስቲያን የፍታት ሥነሥርዓታቸው ተካሂዶ በጊዜያዊ ማረፊያ ቦታ የቀብራቸው ሥነሥርዓት ተፈጸመ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...