የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት በስዊድንና በኖርዌይ አፍቃሪዎቹን አደናገረ

Teddy Afro after his release“ቴዲ አፍሮ ኖቨምበር 28 ስዊድን ይመጣል” አቶ ሀብታሙ

“ቴዲ አፍሮ ኖቨምበር 28 ኖርዌይ ይመጣል” አቶ ደስታ

“ስዊድን የሚመጣው ዲሴምበር 5 ነው” አቶ ሙሉሰው (ኩኩሻ)

“ኖቨምበር 28 ኖርዌይ፣ ዲሴምበር 5 ስዊድን” አቶ ምትኩ ግርማ የቴዲ አፍሮ ፕሮሞተር

Ethiopia Zare (እሁድ ጥቅምት 1 ቀን 2002 ዓ.ም. October 11, 2009)፦ በቅርቡ ከእስር የተፈታው የአርቲስት ቴዎድሮስ ካሣሁን (ቴዲ አፍሮ) የአውሮፓ የኮንሰርት ጉዞ በስዊድን እና በኖርዌይ መቼ እንደሚካሄድ አፍቃሪዎቹን አደናግሮ ሰንብቷል። በተለይም በዚህ ባሳለፍነው ሣምንት ከሦስት ወገኖች የተለያዩ ማስታወቂያዎች በተለያየ መንገድ በመበተናቸውን የኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገጽ ተገንዝቧል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

መምህራን የኢህአዲግ አባልነት ፎርም በመሙላት ተወዛገቡ

ት/ቤቶች ከምርጫው በፊት ይዘጋሉ

Ethiopia Zare (እሁድ መስከረም 24 ቀን 2002 ዓ.ም. October 4, 2009)፦ ክረምቱን ሥልጠና ሲያደርጉ የሰነበቱ መምህራን ከሥልጠና በኋላ የገዥው ፓርቲ የአባልነት ፎርም እንዲሞሉ መጠየቃቸውን የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች ገለጹ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያ ውስጥ የዘር ቦምብ መጠመዱን አቶ ኦባንግ ገለጹ

Obang MethoEthiopia Zare (ሐሙስ መስከረም 21 ቀን 2002 ዓ.ም. October 1, 2009)፦ ባለፈው ዓርብ መስከረም 15 ቀን 2002 ዓ.ም. በስዊድንና አካባቢው ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር ህዝባዊ ውይይት ያደረጉት “ለአዲሲቱ ኢትዮጵያ የጋራ እንቅስቃሴ” የተሰኘው ድርጅት መሪ የሆኑት አቶ ኦባንግ ሜቶ፤ “ኢትዮጵያ ውስጥ ኢትዮጵያዊነት ሳይሆን፤ የዘር መለያ የሰፈነበት ቦምብ ተጠምዷል” ሲሉ ገለጹ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ቴዲ አፍሮ በአዲስ አበባ ስታዲየም ኮንሰርት ሊያቀርብ ነው

Teddy Afro- ገቢው ለምኖ አዳሪዎችን ራሳቸውን ለማስቻል ይሆናል

- የኮንሰርቱን ወጪ ስፖንሰሮች ሊሸፍኑት ይችላሉ

- አጥጋቢ ስፖንሰር ካልተገኘ የባንዶቹን ወጪ ቴዲ ይሸፍናል

- ቀሪውን አዲካ እና ኤም.ጂ. ፕሮሞሽን ይሸፍኑታል

- አበበች ጎበና ለተባለ ሀገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅት እርዳታም ይሠጣል

Ethiopia Zare (ሰኞ መስከረም 18 ቀን 2002 ዓ.ም. September 28, 2009)፦ ታዋቂው ድምፃዊ አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን ከእስር ከተፈታ ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ ስታዲየም ጥቅምት 1 ቀን 2002 ዓ.ም. የሙዚቃ ኮንሰርት ሊያቀርብ ነው። ከዝግጅቱ መግቢያ የሚገኘው ሙሉ ገቢ በልመና ላይ ለተሰማሩ ኢትዮጵያውያን ራሳቸውን ለማስቻል እንዲሆን ፈቅዷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በጐጃም የአንድነት አስተባባሪዎች ተደበደቡ፤ በደቡብ ኢትዮጵያ ለፓርቲው የሚሆን ቢሮ ያከራዩ ግለሰብ ታሰሩ

Ethiopia Zare (ሐሙስ መስከረም 14 ቀን 2002 ዓ.ም. September 24, 2009)፦ በምዕራብ ጐጃም የአንድነት ቅርንጫፍ ቢሮ አስተባባሪዎች ላይ መስከረም 11 ቀን 2002 ዓ.ም. ድብደባ ተፈጸመ። ወከባና ዛቻ የገጠማቸው የፓርቲው አስተባባሪዎች አንድነት ፓርቲን "ፀረ-ህዝብና ፀረ-ሠላም ነው" ብለው እንዲክዱት ከፍተኛ ጫና ተደርጎባቸዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...