ከኢትዮጵያ ቴሌቪዠንና ራዲዮ ድርጅት የኮበለሉ የስፖርት ጋዜጠኞች ቁጥር ሰባት ደረሰ

Ethiopia Zare (እሁድ መስከረም 10 ቀን 2002 ዓ.ም. September 20, 2009)፦ ብዙውን ጊዜ "ሙያዊ ነፃነትን በመጫን" ከሚታወቀው የኢትዮጵያ ቴሌቪዠንና ራዲዮ ድርጅት በተለያዩ አስተዳደራዊ፣ ፖለቲካዊና በዘመድ የቅጥር ጫናዎች ምክንያት ሥራቸውን እየለቀቁ ወደ ግሉ የሥራ መስክ የሚሠማሩ የመንግሥት ጋዜጠኞች ቁጥር ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ መሆኑ ታወቀ። ጥቂት የማይባሉትም ሀገር ለቀው መሰደዱን ምርጫቸው አድርገዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የ8ኛ እና የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች የኦህዲድ አባል እንዲሆኑ ተጠየቁ

ከጳጉሜን 3 ጀምሮ በኦሮሚያ ከ400 በላይ ሰዎች ታስረዋል

Ethiopia Zare (እሁድ መስከረም 10 ቀን 2002 ዓ.ም. September 20, 2009)፦ በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ የሚኖሩ የ8ኛ እና የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች "የኦህዲድ አባልነት መታወቂያ ካላመጣችሁ ለሁለተኛ ደረጃ እና ለመሰናዶ ትምህርት አትመዘገቡም" መባላቸውን የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች ገለጹ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዛሬ ኢድ አልፈጥር በኢትዮጵያውን ዘንድ ተከብሮ ይውላል

ፕ/ት ባራክ ሁሴን ኦባማ የመልካም ምኞት መግለጫ አስተላለፉ

23 ሚሊዮን ሙስሊሞች ረመዳንን በአስቸጋሪ ሁኔታ አሳለፉ

Ethiopia Zare (እሁድ መስከረም 10 ቀን 2002 ዓ.ም. September 20, 2009)፦ ኢትዮጵያውያን የእስልምና ኃይማኖት ተከታዮች የአንድ ሺህ አራት መቶ ሠላሳኛውን የኢድ አልፈጥር (ረመዳን) በዓል ዛሬ እሁድ መስከረም 10 ቀን 2002 ዓ.ም. ያከብራሉ። በመላው ዓለም ያሉ ሙስሊሞችም 1430ኛው የረመዳን በዓል ያከብራሉ። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ባራክ ሁሴን ኦባማና ባለቤታቸው የመልካም ምኞት መግለጫ ሰጥዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

መንበረ ፓትርያርኩ ከሩብ ሚሊዮን ብር በላይ ለደመራ መደበ

Letter from Patriarchate Head Officeየወጪው መብዛት ምዕመናንን አሳዝኗል

(ገንዘቡ የፀደቀበትን ደብዳቤ ይዘናል)

Ethiopia Zare (ኀሙስ መስከረም 7 ቀን 2001 ዓ.ም. September 17, 2009)፦ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የፊታችን መስከረም 16 ቀን 2002 ዓ.ም. ለሚከበረው የደመራ በዓል ከሩብ ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ አፀደቀ። የወጪው መብዛት ምዕመናኑን አሳዝኗል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የጀግኖች ምሽት በዋሽንግተን ዲ.ሲ.

ባለፈው ሴፕቴምበር 12 ቀን 2009 እ.ኤ.አ. (መስከረም 2 ቀን 2002 ዓ.ም.) በዋሽንግተን ዲ.ሲ. “የጀግኖች ምሽት” በሚል ለሁለተኛ ጊዜ በተዘጋጀው የሽልማት ሥነሥርዓት ላይ ለሦስት የኢትዮጵያ የጦር መኮንኖች ሽልማት ተሰጥቷል። ዝግጅቱን አስመልክቶ በፎቶግራፎችና በድምፅ በቪዲዮ ተቀናብሯል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአንድነት እነ ፕሮፌሠር መስፍንን ከአባልነት ማባረር አባላትን አስቆጣ

Ethiopia Zare (ቅዳሜ መስከረም 2 ቀን 2002 ዓ.ም. September 12, 2009)፦ በቅርቡ ጠቅላላ ጉባዔ ሊጠራ ነው የሚባለው አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ነሐሴ 30 ቀን 2001 ዓ.ም. ባደረገው የም/ቤቱ ስብሰባ፤ እነ ፕሮፌሠር መስፍንን በድምፅ ብልጫ ከአባልነት ማባረሩ በአባላቶች ጥያቄ አስነሳ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የዓመቱ ታላቅ ሰው የሽልማት ሥነሥርዓት ተካሄደ

የብርቱካን የልጅነት ጓደኛ ሽልማቱን ተቀበለች

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ጳጉሜን 3 ቀን 2001 ዓ.ም. September 8, 2009)፦ በእስር ላይ የምትገኘው የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ የ2001 ዓ.ም. ድንቅ ሰው በመባል ተሸለመች። የሽልምት ሥነሥርዓቱም እሁድ ሴፕቴምበር 6 ቀን 2009 እ.ኤ.አ. በቫንኩቨር ካናዳ ተካሄደ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በስዊድን የአውሮፓ የውጪ ጉዳይ ሚንስትሮች በተሰበሰቡበት ሠላማዊ ሰልፍ ተደረገ

ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ እንድትፈታ ተጠየቀ

በስቶክሆልም ሴፕቴ. 5 ቀን 2009 ሠላማዊ ሰልፈኞች

በማትያስ ከተማ

Ethiopia Zare (ሰኞ ጳጉሜን 2 ቀን 2001 ዓ.ም. September 7, 2009)፦ ባለፈው ቅዳሜ ነሐሴ 30 ቀን 2001 ዓ.ም. (September 5, 2009) ”ሼፕስሆልመን” በሚባለውና በስቶኮልም ግራንድ ሆቴል አጠገብ በሚገኝ የስብሰባ ቦታ የአውሮፓ የውጪ ጉዳይ ሚንስትሮች ሰብሰባ ተጀምሯል። በስቶክሆልምና አካባቢው የሚገኙ በርካታ ኢትዮጵያውያን በስፍራው በመገኘት ሠላማዊ ሰልፍ ከማድረጋቸውም በላይ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ካለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ ትፈታ ዘንድ መልዕክታቸውን ለተሰብሳቢዎቹ አሰምተዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ቀነኒሳ በቀለ አንድ ሚሊዮን ዶላሩን ተቋደሰ

ገንዘቡን ከይሌና ኢሲንባዬቫ እና ከሳንያ ሪቻርድስ ጋር ይካፈላል

አትሌት ገለቴ ቡርቃ በ2000 ሜትር አንደኛ ወጣች

(ተጨማሪ ዘገባና ፎቶዎች የታከለበት)

Kenenisa Bekele crosses the finish line to win the men's 5000m race at the IAAF Golden League Memorial Van Damme athletics meeting in Brussels September 4, 2009.

Ethiopia Zare (ዓርብ ነሐሴ 29 ቀን 2001 ዓ.ም. September 4, 2009)፦ ከአስር ደቂቃ በፊት ዛሬ ዓርብ ነሐሴ 29 ቀን 2001 ዓ.ም. ማምሻውን በቤልጅየም ብራስልስ እየተደረገ ባለው የ2009ኙ የጎልደን ሊግ 6ኛና የመዝጊያው ውድድር ላይ ቀነኒሳ በቀለ በ5000 ሜትር በአንደኝነት በማጠናቀቅ የአንድ ሚሊዮን ዶላሩ ጃክ ፖት ተቋዳሽነቱን አረጋገጠ። ውድድሩን በ12 ደቂቃ ከ55፡31 ሰከንድ ነው የጨረሰው። አንድ ሚሊዮን ዶላሩን ከራሺያዊቷ የምርኩዝ ዘላይዋ ይሌና ኢሲንባዬቫ እና ከአሜሪካዊቷ የ400 ሯጭ ሳንያ ሪቻርድስ ጋር ይካፈላል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...