“ኢትዮጵያ ለአልጀርሱ ስምምነት ያለመገዛት መብት አላት” ሜ. ጄነራል አበበ ተ/ኃይማኖት

Major General Abebe TeklehaymanotEthiopia Zare (ቅዳሜ መስከረም ፳፬-24 ቀን ፳፻፩-2001 ዓ.ም. October 4, 2008)፦ኤርትራ የደህንነት ቀጠናውን በመጣሷ የተነሳ የአልጀርስ ስምምነት በመፍረሱ የኢትዮጵያ መንግሥት ለስምምነት አልገዛም የማለት ሕጋዊ መብት እንዳለውና፣ ሀገሪቱ የባህር በር የማግኘት መብቷ ዓለም አቀፍ እውቅና እንዲያገኝ ጥያቄ መጠየቅ እንደምትችል አንድ የቀድሞ የኢፌዲሪ አየር ኃይል ጄኔራል ገለጹ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ንግድ ባንክና ዳሽን ባንክ ከአፍሪካ 100 ምርጥ ባንኮች ውስጥ ገብተዋል

Ethiopia Zare (ቅዳሜ መስከረም ፳፬-24 ቀን ፳፻፩-2001 ዓ.ም. October 4, 2008)፦ ሁለት የኢትዮጵያ ባንኮች ባላቸው ካፒታል ከአፍሪካ 100 ምርጥ ባንኮች ዝርዝር ውስጥ መግባታቸውን አፍሪካን ቢዝነስ መድሔት ዘገበ። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 57ኛ ደረጃን ሲይዝ፣ ዳሽን ባንክ 88ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዜጎች በሕገ-ወጥ መንገድ በኢትዮጵያ በእስር ቤት ታጉረዋል

Jennife DaskalEthiopia Zare (ቅዳሜ መስከረም ፳፬-24 ቀን ፳፻፩-2001 ዓ.ም. October 4, 2008)፦ ሽብርተኝነት ለመዋጋት በሚል ምክንያት ኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥታት በጥምር ኾነው ዜጎችን በእስር ቤት አጉረዋል፣ ሕገ-ወጥ ምርመራም አድርገዋል የሚል ሪፖርት ይፋ ኾነ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የቴዲ አፍሮን ጉዳይ የሚያዩት ዳኛ ተነሱ

Teddy Afroአዲሱ የቴዲ ጠበቃ የዳኛው ረዳት ነበሩ

ቴዲ የፊታችን ኀሙስ መከላከያ ይዞ ይቀርባል

Ethiopia Zare (ዓርብ መስከረም ፳፫-23 ቀን ፳፻፩-2001 ዓ.ም. October 3, 2008)፦ የዝነኛው አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮን) የክስ ሂደት ሲዳኙ የነበሩት ዳኛ ልዑል ገ/ማርያም "ለጊዜው" ከችሎት የተነሱ ሲሆን በምትካቸው ዳኛ መሐመድ ዑመር ተተክተዋል። በተያያዘ ለቴዲ አፍሮ አዲስ የተቀጠሩለት ሁለተኛው ጠበቃ የአቶ ልዑል ረዳት ዳኛ ሆነው ሠርተዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምረ

የቤት ጋዝ 5.75 የነበረው 8.59 ሆኗል

Ethiopia Zare (ዓርብ መስከረም ፳፫-23 ቀን ፳፻፩-2001 ዓ.ም. October 3, 2008)፦ ከዛሬ መስከረም 23 ቀን 2001 ዓ.ም. ጀምሮ የነዳጅ ዋካ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች አረጋገጡ። የላምባ ወይንም የቤት ጋዝ 8 ብር ከ59 ሣንቲም ገብቷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከጠ/ሚ/ር መለስ ጋር ኒው ዮርክ የሄደ ጋዜጠኛ ጥገኝነት ጠየቀ

Ethiopia Zare (ኀሙስ መስከረም ፳፪-22 ቀን ፳፻፩-2001 ዓ.ም. October 2, 2008)፦ ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጋር ወደ ኒው ዮርክ ስብሰባውን ለመዘገብ አብሮ የተጓዘ ካሜራ ቀራጭ ጋዜጠኛ ሸዋንግዛው ካሳሁን ጠ/ሚኒስትሩ ከኮንዶሊዛ ራይዝ ጋር ያደረጉትን የመጨረሻ ስብሰባ ሳይቀርጽ አሜሪካን ሀገር መጥፋቱንና ጥገኝነት መጠየቁ ታወቀ።

 

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢድ ሙባረክ!

Ethiopia Zare (ማክሰኞ መስከረም ፳-20 ቀን ፳፻፩-2001 ዓ.ም. September 30, 2008)፦ የሙስሊም እምነት ተከታዮች ላለፉት አራት ሣምንታት ሲጾሙት የነበረው የረመዳን ፆም ዛሬ ተፈትቷል። በዚህ አጋጣሚ የኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገጽ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች "ኢድ ሙባረክ!" ይላል።

በጅጅጋ አንድነት ሆቴል ቦምብ ፈነዳ

አራት ሰዎች ሞተዋል

Ethiopia Zare (ሰኞ መስከረም ፲፱-19 ቀን ፳፻፩-2001 ዓ.ም. September 29, 2008)፦ እሁድ ከጠዋቱ አራት ሰዓት ላይ በጅጅጋ ከተማ "አንድነት" በተባለ ሆቴል በተከሰተ ፍንዳታ አራት ሰዎች መሞታቸውንና አስር ሰዎች መቁሰላቸውን ኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች አረጋገጡ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...