አፋኝ የሲቪል ማኅበረሰብ ረቂቅ አዋጅ ወጣ
የሕግ ባለሙያዎች እያወገዙት ነው
Ethiopia Zare (እሁድ የካቲት 16 ቀን 2000 ዓ.ም. February 24,2008)፦ በተለያዩ ድረ-ገጾች ላይ ሰሞኑን የተለቀቀው የሲቪል ማኅበረሰብ ረቂቅ አዋጅ አፋኝ ይዘት ያለው ነው ሲሉ አንዳንድ የሕግ ባለሙያዎች አስተያየት ሰጡ።
የሕግ ባለሞያና የሲቪል ማኅበረሰብ አባል እንደገለጹት፤ በሕግ ማርቀቅ ሂደት የሲቪል ማኅበረሰቡና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት እንዲሳተፉ በመንግሥት በኩል ፈቃደኝነት እንዳልነበረ ገልጸው፤ አሁንም ቢሆን ወጣ የተባለውን ረቂቅ አዋጅ ከድረ-ገጽ ላይ ወስዶ ከማየት ውጭ በመንግስት በኩል የተገለጸ ምንም ነገር እንደሌለ ተናግረዋል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...



