‹‹መንግስት ሊያስጨርሰን ዝም ብሎ እያየን ነው›› የደብረሊባኖስ ገዳም መነኮሳት
በአካባቢው የጎሣ ችግር እንዳይከሰት ተሰግቷል
ልዩ ሪፖርታዥ
Ethiopia Zare (ማክሰኞ ጥር 27 ቀን 2000 ዓ.ም. February 5,2008):- ለ838 ዓመታት በታሪካዊ ገዳምነት የሚታወቀው የደብረ ሊባኖስ ገዳም አካባቢ ወደ ቀበሌነት መለወጥን የተቃወሙ መነኮሳት፤ የገዳሙ ወደ ቀበሌነት መለወጥ የኃይማኖታዊ ተግባሩ ጋር በፍጹም የሚቃረን ነው ሲሉ አቤቱታቸውን ለማሰማት ወደ ፓትሪያርኩ ቢሮ መምጣታቸውንና በእንግልት ላይ መሆናቸውን ከአዲስ አበባ የደረሰን ዘገባ ጠቆመ። ከአዲስ አበባ የደረሰን ሪፖርት እንዲህ ተዘግቧል፦
Ethiopia Zare (ቅዳሜ ጥር 24 ቀን 2000 ዓ.ም. February, 2,2008)፦ በወ/ት ብርቱካን የሚመራው ቅንጅት ሥራ አስፈፃሚ በተጓደሉት የላዕላይ ምክር ቤት አባላት ምትክ 16 አዳዲስ አባላትን የመረጠ ሲሆን፣ ከእነዚህም ውስጥ ፕሮፌሠር መስፍን ወልደማርያም አንዱ መሆናቸውን ከአዲስ አበባ ተደምጧል።
Ethiopia Zare (ቅዳሜ ጥር 24 ቀን 2000 ዓ.ም. February, 2,2008)፦ ልደታ የሚገኘው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ረቡዕ ጥር 21 ቀን 2000 ዓ.ም. በካሚላት መህዲ ላይ አሲድ በደፋው ደምሰው ዘሪሁን ላይ የሞት ቅጣት ሲወስንበት፤ በዚሁ መዝገብ ላይ በተባባሪነት በተከሰሰው ያዕቆብ ኃይለማርያም ደግሞ በ20 ዓመት ጽኑ እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፏል። ወ/ት ካሚላት በችሎቱ አዳራሽ ተገኝታ ነበር።
ዓቃቤ ሕግ ይግባኝ ሊጠይቅ ይችላል


