የኢሕአፓ መድፍ ተሰማ! (ተሰፋዬ ገብረአብ)

ኢህአፓ የተባለት ሰዎች የኮልኔሌ መንግስቱን መፅሃፍ ስካን አድርገው በድረገፅ ሲለቁት ከተቃወሙት አንዱ እኔ ነበርኩ። የተቃወምኩበት ምክንያት፣ “ለኮልኔሉ መብት ጥብቅና ለመቆም”፣ ወይም “አሳታሚውን ከኪሳራ ለማዳን” አይደለም። ከመርህ አንፃር ነበር። ባህሉ በጣም አደገኛ መሆኑን በመረዳት ነበር። ድርጊቱ ፀረ እውቀት ስለሆነ ነበር። ተራ የንግድ ጉዳይ አልነበረም። አምርሬ የተቃወምኩት በተለይም በቀጥታ እኔንም ስለሚመለከተኝ ነበር። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ)

የዳግማዊ አፄ ምኒልክን እና የእቴጌ ጣይቱ ብጡልን ታሪክ አዛብቶ ማቅረብ ለምን አስፈለገ?

ተድላ ሀይሉ

ሰላም ውድ አንባብያን። ሠሞኑን አንድ ጽሑፍ በአቶ ተስፋዬ ገብረአብ ተደርሶ በኢንተርኔት በየድረ-ገፆቹ ተበትኗል። የዚህ ጽሑፍ ትክክለኝነት ወይም ተዓማኒነት ሣይጣራ ልክ እንደ ቆላ ሠደድ እሣት በብዙ የኢትዮጵያውያን ድረ -ገፆች ላይ ተበትኗል። ነገር ግን 'ታሪክም' ይሁን 'ድርሠት' ሆን ተብሎ የሚታወቅ ሃቅን ለማስካድ የሚጻፍ ከሆነ አንባብያንን ማሣሣት ብቻ ሣይሆን በትውልድ ውስጥ የማያስፈልግ ውዝግብን ይተክላል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የቴዲ አፍሮ ፍቅረኛ (ከተስፋዬ ገብረአብ)

ያቺን የማትረሳ ቆንጆ ልጅ የተዋወቅሁዋት አስመራ ላይ ሲሆን፣ ከካቴድሪያል ወደ ቲራቮሎ በሚጓዘው ታክሲ ላይ ተሳፍሬ ነበር። ልጅቱ ፒኮክ የተባለችውን ወፍ ነበር የምትመስለው። ታክሲው ላይ ከሁዋላ አብረን ነበር የተቀመጥነው። “ላናግራት ወይስ ይቅርብኝ?” እያልኩ ሁለት ልብ ሆኜ እያመነታሁ ቆየሁ። እኔ ደጋግሜ ባያትም፣ እሷ አንድ ጊዜ እንኳ ዘወር ብላ አላየችኝም። ከሞባይል ቴሌፎኗ ጋር ተመስጣ እየተጫወተች ነበር። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የዘር ማጽዳት ዘመቻ በወልቃይትና በጠገዴ ማህበረሰብ ላይ

(ቻላቸው ዓባይ፣ ጎሹ ገብሩ፣ ዓባይ መንግሥቱ እና አብዩ በለው)

የተባበሩት መንግሥታት ም/ቤት በ1948ና በ1992 ዓ.ም. የዘር ማጥፋትንና የዘር ማጽዳትን ወንጀልች አስመልክቶ ያስተላለፈው ውሳኔ ለዚህ ጦማር እንደ መግቢያ ያገለግሉ ዘንድ የተመረጡ ናቸውና በቅድሚያ እነሱን ይመለከቱ ዘንድ በአክብሮት ተጋብዘዋል። ”ውሳኔ አንድ”፣ ... ”ውሳኔ ሁለት” ...


 

 

ውሳኔ አንድ www.preventgenocide.org/genocide/officialtext.htm

ውሳኔ ሁለት www.un.org/documents/ga/res/47/a47r080.htm

የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር ይህን ኢትዮጵያዊ ዘር ማፅዳት ለምን አስፈለገው?

ከዚህ ቀደም በተለያዩ መድረኮችና መጣጥፎች እንደተገለጠው ሁሉ ወያኔ በጎንደር ህዝብ ላይ በተለይም በወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ህዝብ ላይ የፈፀመው ወረራ በሁለት መሰረታዊና እኩይ ጭብጦች ላይ ይነሳል።

 

1ኛ. ለታለመው የ”ታላቋ ትግራይ” እና ለ”ትግሪያዊው ወርቅ” ህዝብ የምግብ ዋስትና የሚያረጋግጥ ለም መሬት በመፈለግ ሲሆን፣

 

2ኛ. ለወደፊት በ”ሀገርነት” ለታጨችው ለ”ታላቋ ትግራይ” ከቀሪው ዓለም ጋር የየብስ የመውጫና የመግቢያ በር ለማግኘት በመቋመጥ የተተለመ ነበር። ... (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!)

ማነው? አንዷለምንና አጋሮቹንየሚገርፋቸው?የሚያስገርፋቸው? ወያኔ ወይስ እኛ?

የጐንቻው

ገሃዱ እውነታ አንዷለምንና አጋሮቹን አሳልፈን ለግርፋት፤ ለውርደት፤ ለስቃይ፤ ‘ለቁም-ሞት’ የዳረግናቸው በለየለት ጠላት (ወያኔ) እናሳብ እንጅ፤ በደለኞች እኛ ቁጥራችን ያስደመመን ብዛታችን እንደ ሃይቅ ያሰጠመን፤ ግነነታችን ያንቀጠቀጠን፤ አንድነታችን ያናወጠን፤‘ [እኛ ከሰማንያ ሚሊዮን በላይ የምንሆን ኢትዮጵያውያን]፤ ነን። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኪነ-ጥበብና የከያኒ ፋይዳ በሃገር ጉዳይ (ከብርሃኑ ጃዝ)

ምንም እንኳን የዚህ ጽሁፍ አዘጋጅ የኪነጥበብ ሰዉ ቢሆንም በዚህ አጭር ጽሁፍ ሊያነሳ የፈለገዉ አጠቃላይ ስለ ኪነ-ጥበብና ስለከያኒዉ ሲሆን የኪነጥበብ ሰዎች በሃገራቸዉ ጉዳይ ላይ ስላላቸዉ ሚና በተለይም  ገርና ህዝብ በከባድ ፈተናላይ እያለች  ገሬ ወገኔ ብለዉ ስለሚያደርጉት ስላደረጉትና ማድረግ ስለሚገባቸዉ ከሞራልም/ከሰነ-ምግባርም/ ሆነ ከሙያ አኳያ አጭር ዳሰሳ ማድረግ ነዉ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የፍትህ መልዕክት ለህወሓት (ሊያነቡት የሚገባ)

በኢትዮጵያ ከ1966 ዓ.ም. ወዲህ በርካታ ድርጅቶች ተፈጥረው የፖለቲካ ትግል ሲያካሄዱ እንደነበረ ይታወቃል። ከእነዚህም አንዱ ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ /ህወሓት/ ነው። ይህ ድርጅት ከነገ በስቲያ የተመሰረተበትን ሰላሳ ሰባተኛ አመት ያከብራል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

አማራው የህወሓት ቼ ጉቬራ (ከህወሓት አስራ አንዱ መስራቾች አንዱ ጎንደሬ ነው)

ተመስገን ደሳለኝ (አዲስ አበባ)

አማራው የህወሓት ጉቬራ

ፋኖ ተሠማራ... ፋኖ ተሠማራ...

እንደ ሆቺሚኒ... እንደ ቼ ጉቬራ...

በዱር በገደሉ ታሪክ ልትሰራ

ዛሬ ፋኖ ወደ ዱርም፣ ወደ ገደልም አይሰማራም፡፡ አለመሰማራት ብቻ አይደለም፡-

‹‹ፋኖ፣ ፋኖ፣… ኧረ ፋኖ… ጥራኝ ጫካው፣ ጥራኝ ዱሩ

ለአንተም ይሻልሀል ብቻ ከማደሩ

ፋኖ፣ ፋኖ፣ ኧረ ፋኖ፣ ፋኖ… የሚል ዘፈንም አይዘፍንም፡፡ የቱንም ያህል መብትህ ቢገፈፍም፣ ድምፅ ቢጭበረበርም አንተም አታንጎራጉረው፡፡ ሌላው ቀርቶ እነዚህ መብቶች ቅንጦት ናቸው ብለን ብናልፋቸው እንኳ ቢርበህ እና ቢጠማህም ‹‹ፋኖ፣ ፋኖ፣ አረ ፋኖ…›› ብለህ አትዘፍንም፡፡ ሙሉውን አስነብበኝ ...

“አንድ አገር ራሷን የምታስተዋውቀው… በምታስታውሳቸው ሰዎች ጭምር ነው” (ሪፖርተር ጋዜጣ ርዕሰ አንቀጽ)

“አንድ አገር ራሷን የምታስተዋውቀው በምታፈራቸው ሰዎች ብቻ ሳይሆን በምታከብራቸውና በምታስታውሳቸው ሰዎች ጭምር ነው” ጆን ኦፍ ኬኔዲ

ትልቅ አባባል ነው! የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የነበሩት ጆን ኦፍ ኬኔዲ ናቸው ይህንን የተናገሩት። ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ