ታሪክ ያላት ሀገር ያለመሪ ስትቀር (ታደለ መኩሪያ)
ታደለ መኩሪያ (April 29, 2008)
ለዘመናት በሕግ ሲተዳደር የኖረን ሕዝብ በየጊዜው ሀገር ወለድ አምባገነኖች እየተነሱ ሲጨቁኑት ብሩህ ራዕይ ያላቸውን ዜጎች ሲያጠፉ ታይቷል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ታደለ መኩሪያ (April 29, 2008)
ለዘመናት በሕግ ሲተዳደር የኖረን ሕዝብ በየጊዜው ሀገር ወለድ አምባገነኖች እየተነሱ ሲጨቁኑት ብሩህ ራዕይ ያላቸውን ዜጎች ሲያጠፉ ታይቷል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ቅዳሜ ሚያዝያ 11 ቀን 2000 ዓ.ም. (አፕሪል 19 ቀን 2008 እ.ኤ.አ.) በቶሮንቶ ከተማ ካናዳ ከኢትዮጵያውያኖች ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ "የሞራል እኩልነት ጥያቄዎችና የአመለካከት ችግራቸው፤ ምን ያህሉ ከተግባር ለመራቅ የሚደረግ እራስን የመሸንገያ መሣሪያ ነው?" በሚል ርዕስ ንግግር አድርገዋል። ሙሉ ንግግሩን በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ። (Read on PDF)
መስፍን ወልደማርያም (ፕ/ር) - ሚያዝያ 2000
ምርጫ የነፃ ሕዝቦች መግለጫ ነው፤ ነፃ ሕዝቦች የአገራቸውንና የመንግሥታቸው ባለቤቶች ናቸው፤ ስለዚህም ምርጫ የአገራቸውና የመንግሥታቸው ባለቤትነታቸውን የሚያረጋግጡበት ዘዴ ነው። በአንፃሩ ደግሞ ነፃ ላልሆኑ ሕዝቦች ምርጫ ለሕዝቡ ፋይዳ የሌለውና የገዢዎቹን ጅራፍ ለመጎንጎኛ የሚያገለግል እጅ መንሻ ነው፤ በአፍሪካ ምርጫ የሚባለው የሁለተኛው ዓይነት ነው።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ከዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማሪያም
1. መነሻው
አንድ ማኅበረሰብ እንደ ማኅበረሰብነቱ እንዲቀጥል ከተፈለገ በረቀቀ መልኩም ይሁን በግርድፉ የህዝብ መስተጋብሮችን የሚያስተናግዱ፣ የሥራ ኃላፊነትንና ድርሻን የሚያደላድሉ፣ መሠረታዊ ፍላጎቶችን የሚያሟሉ ሕጎች መኖር የግድ ይላል። በመሆኑም እንደ አንዳንድ ጥንታዊ የዳበረ ኅብረተሰብ ኢትዮጵያዊያን ያለ ሕግ የኖሩበት ጊዜ የለም ማለት ይቻላል። ከዚያም አልፎ ዛሬ ሕጎቻቸው ዳብረው፣ ፍትሕ ሰፍኖባቸው፣ ህዝቡ መብቱ ተከብሮለት፣ ነፃነቱ ተጠብቆለት የምናያቸው ብዙዎቹ የዓለም መንግሥታት ባልተፈጠሩበት ዘመን በኢትዮጵያ በጽሑፍ የሰፈሩ የህዝቡን መስተጋብር የሚያስተናግዱ፣ የነገሥታቱና የባላባቱ ሥልጣን ስፋትና ወርድ ዳር ድንበሩን የሚከልሉ፣ በዳይን የሚወቅሱ፣ ተበዳይን የሚክሱ ሕግጋት ነበሩ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ያሬድ ክንፈ ከስዊድን (ሀገር ቤት ላለ ወዳጅ የተጣፈ) ( This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. )
ጌትዬ! ከነመላው ቤተሰብህ መልካም የገና በዓል ይሆንልህ ዘንድ ከልቤ እመኛለሁ!
እዚህ ስዊድን ውስጥ የኢትዮጵያን ገና ምክንያት በማድረግ ቅዳሜ ታህሳስ 19 ቀን 2000 ዓ.ም. (ዲሴምበር 29 ቀን 2007 ዓ.ም.) ፌሽታ ተደርጎ ነበር። ዋና ከተማዋ ስቶክሆልም ውስጥ ሊልሆልመን እተባለው ክፍለከተማ በኢድሮትስሐለን አዳራሽ ውስጥ ከምሽቱ አራት ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ (ለእሁድ አጥቢያ) 10 ሰዓት ድረስ ነበር ዝግጅቱ። መድረኩን ተቆጣጥሮት የነበረው ተወዳጁ ቴዲ አፍሮ (ቴድሮስ ካሣሁን) ነበር።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ከፕሮፌሠር መስፍን ወልደማርያም - መጋቢት 2000
በጥቅምት 1998 ዓ.ም. ላይ የሚያዝያ 1997 ዓ.ም. የህዝብ ስብሰባ እና ተከታትሎ የመጣው ምርጫ የኢትዮጵያ ህዝብ ለነፃነት ያለውን ቁርጠኛ ፍላጎት አሳየ፤ ተደላድለው የነበሩ ወንበሮችን አነቃነቀ፤ በትምክህት አብጠው የነበሩትን ሁሉ ልባቸውን በፍርሃት አርበደበደው፤ ከታች መሰረት፣ ከጎን ምሰሶ፣ ከላይ ጣሪያ የሌላቸው መሆናቸውን ያለጥርጥር እንዲገነዘቡ አደረጋቸው፤ ጭካኔ ከፍርሃት ተለወደ። የፍርሃት ልጅ ያስከተለው መዘዝ ወዳጅንና ጠላትን የመለየት ችሎታችንም እስከመንሳት ደረሰ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ከዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያም
Ethiopia Zare (ዓርብ መጋቢት 5 ቀን 2000 ዓ.ም. March 14,2008)፦ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 29፣ ግለሰቦችም ሆኑ ፕሬስ ወይንም ሌሎች መገናኛ ብዙኀን ሃሳባቸውን በነፃ የመግለጽ ተፈጥሮአዊ መብት ያረጋግጥላቸዋል። የአሜሪካ ሕገ መንግሥት እነዚህን መብቶች ከማረጋገጥ አልፎ እንዲያውም ኮንግሬስ ይህንን መብት ለመገደብ ሕግ ሊያወጣ እንደማይችል ይደነግጋል። ይህ የንግግርና የጽሁፍ ነፃነት ይህን ያህል ዋጋ የሚሰጠው ያለ ፕሬስ ነፃነት ዲሞክራሲና የተመጣጠነ ክብር ያለው ኑሮ ለመኖር የሚያስችል ልማት ፈጽሞ የማይታሰብ በመሆኑ ነው። የፕሬስ ነፃነት መዳበር ወይንም መቀጨጭ አንድ አገር በሥልጣኔ ምን ያህል ወደፊት እንደመጠቀ ወይንም ምን ያህል ወደ ኋላ እንደቀረ የሚጠቁም ነው።
ሙሉውን አስነብበኝ ...በእምነቱ ዘለቀ እና አንዳርጋቸው ጽጌ (የካቲት 2000)
አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እና አቶ በእምነቱ ዘለቀ በዚህ በተገባደደው የካቲት ወር 2000 ዓ.ም. ላይ በጋራ በመሆን "ለወደፊቱ ትግል ማመላከቻ የምርጫ 97 አጭር ግምገማ" በሚል ርዕስ ባለ 23 ገጽ ጽሑፍ አዘጋጅተው ህዝብ እንዲወያይበት በድረ ገጾች አሰራጭተዋል። የጽሁፉን ዓላማ አደገኛ አጣብቂኝ ውስጥ የወደቀውን በሀገራችን ተጀምሮ የነበረውን የዴሞክራሲ ትግል ከገባበት አጣብቂኝ የሚያወጣውን ሃሳብ ለመሰንዘር መሆኑን ፀሐፊዎቹ ገልጠዋል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ወደምዕራብ በሄድን ቁጥር ራዕያችንን እናጣለን
ማስታወሻ ከሰሜን አሜሪካ
ችግርና ምሬት እንደ መነሻ - አንደኛ
“በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ሀሳብህ አርፎ ከሆነ ብዙ ሥራ ይጠብቅሀል” ይላል ከሁለት ሣምንት በፊት የደረሰኝና በየቀኑ እንደዳዊት የምደግመው የምስኪኑ ጓደኛዬ ደብዳቤ። በጽሁፍና በድርሰት ታሪክ ውስጥ በዚህች አጭር ሕይወቴ እንደተረዳሁት ምሬትንና ችግርን እንደመጻፍ የሚቀል ዓለማቀፋዊ ነገር የለም። ለመጻፍም ለመናገርም የሚቀል ርዕስ - ችግር ነው። ባለጸጋዎቹም፣ ነዳያኑም አገራት የችግራቸው ዝርዝር ተዝቆ አያልቅም። አሁን ካናዳና አውስትራሊያ ችግር ያለባቸው ይመስላሉ? እንደውም እነዚህ ሰዎች ሥልጣኔን ብቻ ሳይሆን ችግርንም ነው እንዴ የሠሩት? እስክትሉ ድረስ ችግር ቤቱን የሠራበት ምድር እዚህ ነው። እንዲሁም ዜናዎቻቸውን ብትሰሙ፣ የሚጻፉትም የሚነገሩትም ምሬትና ችግር ይበዛባቸዋል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ፕሮፌሠር መስፍን ወልደማርያም - የካቲት 2000