የወያኔ የጎሣ ፌደራሊዝም ሲፈተሽ

ተስፋዬ ገብረዮሐንስ (ከጀርመን)

Ethiopian federalism map. የወያኔ የጎሣ ፌደራሊዝም ሲፈተሽ

የወያኔ አስተዳደር የማዕከላዊውን የመንግሥት ሥልጣን ከተቆጣጠረ በኋላ በሀገሪቱ ተግባራዊ ያደረገው የፌደራል ሥርዓት ጎሣን መሠረት ማድረጉ የሚታወቅ ነው። እንደ ወያኔ አገላለጽ ይህ የጎሣ ፌደራሊዝም በኢትዮጵያ ደም መፋሰስን ያስቀረና ሀገሪቱንም ከመበታተን አደጋ የሚታደግ ነው ይላል። ይሁን እንጂ በተግባር እየተፈፀመ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ በጥልቀት ስንፈትሽ ይህ ወያኔ-ሰራሽ የሆነው የጎሣ ፌደራሊዝም ዓላማም ሆነ እያስከተለ ያለው ውጤት ከዚህ በተቃራኒ ሆኖ እናገኘዋለን።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የጎሣ ዘረኝነት (ክልላዊነት) በኢትዮጵያ

ፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም፣ ነጻነት ለሀገሬ)

Ethnic apartheid in Ethiopia. የጎሣ ዘረኝነት (ክልላዊነት) በኢትዮጵያ

የጸሐፊው ማስታወሻ፡- ይህ “የጎሣ ዘረኝነት/አፓርታይድ በኢትዮጵያ“ በሚል ርዕስ መደበኛ በሆነ መልኩ እያዘጋጀሁ የማወጣው ተከታታይ ትችት ሁለተኛው ክፍል ነው። የዚህ ተከታታይ ጽሑፍ ጥንድ ዓላማዎች የሚከተሉት ናቸው።

1ኛ) በአሁኑ ጊዜ በህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ (ዘ–ህወሓት) አድራጊ ፈጣሪነት ተመስርቶ እየተቀነቀነ ያለው አውዳሚ የፖለቲካ ሥርዓት በደቡብ አፍሪካ ውስጥ የሰፊው የጥቁሮች ህዝብ የበላይ አገዛዝ ሥርዓት ከመፈጠሩ በፊት በጥቂት ነጮች የዘረኝነት የበላይ አገዛዝ ከነበረው የአፓርታይድ ዘረኛ አገዛዝ ተሞክሮ ጋር አንድ ዓይነት መሆኑን ከምንም ጥርጣሬ በላይ ለማመላከት እና

2ኛ) ጥልቀት እና ስፋት ያለው ክርክር እና ውይይት በማካሄድ ከጎሣ ዘረኝነት የጸዳች አዲሲቷን ኢትዮጵያ የመገንባቱን አስፈላጊነት ለመፍጠር እንዲቻል የኢትዮጵያን የአቦ ሸማኔ ወጣት ትውልድ ተሳትፎ ከፍ ለማድረግ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የመተማመን መትነን

ገለታው ዘለቀ

በመጀመሪያ ደረጃ መተማመን (Trsut) ስንል የአንድ ሕብረተሰብ የጋራ ሀብት ወይም የማኅበራዊ ካፒታል ዋና አካል መሆኑን እናንሳ። በአጠቃላይ ማኅበራዊ ካፒታል ስንል ደግሞ ልክ እንደሌሎቹ የሰው ልጆች ካፒታል የሚታይ ነው። ለምሳሌ የገንዘብ ካፒታል፣ የሰው ካፒታል (Human capital) እንደምንለው ማኅበራዊ ካፒታልም ካፒታል ይባላል። ካፒታል ነው እንደንል የሚያስችለን ምክንያት አንድም ልክ እንደሌሎቹ ካፒታሎች የሚመረት (Produce የሚደረግ) መሆኑና ለተለያዩ የማኅበረሰብ ልማቶች ኢንቨስት የምናደርገው ሀብት በመሆኑ ነው። እነዚህ ተፈጥሮዎቹ ከሌሎች ካፒታሎቻችን ጋር ያመሳስሉታል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሰማያዊ ይድን ይሆን?

ይገረም አለሙ

Blue party. ሰማያዊ ፓርቲ

የፖለቲከ ስህተትና የሳንባ ነቀርሳ ጠንቆች የተመሳሳይነት ባህርይ አላቸው። ሁለቱም ችግሮች በለጋነታቸው ወቅት ከተነቃባቸው ችግሮቹን የማስወገድ ዕድል ከፍተኛ ነው። ችግሮቹ ሥር ከሰደዱ በኋላ የሚደረገው መሯሯጥ ግን ፈውስ የማስገኘቱ ሁኔታ አስቸጋሪ ብቻ ሳይሆን የማይቻልም ሊሆን ይችላል። (ማርጋሪት ታቸር የእንግሊዝ ጠ/ሚ የነበሩ)

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዲያቆን ሙት!

አሊ ጓንጉል

Daniel Kibret. ዲያቆን ዳንኤል ክብረት

ይህ ጽሁፍ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በቅርቡ ‘“ሀገር ማለት ሰው ነው”! እስቲ ሙት በለኝ!’ ሲል ለለቀቀው ጽሁፍ መልስ ነው። ... እስካሁን ድረስ “ሀገር ማለት ሰው ነው” የሚባል ዘፈን መኖሩን ሰምቼም አይቼም አላውቅም። በዚህ ስም የሚጠራ ዘፈን ኖሮ እኔ ያላወቅሁ እንኳን ቢሆንም፣ “ሀገር ማለት ሰው መሆኑን” ሊያስክድ የሚችል አንዳችም ነገር ያለ አይመስለኝም። በዚህ ስም የሚጠራ ዘፈን ጨርሶ ሳይኖር፣ የበድሉ ዋቅጅራን “ሀገር ማለት የኔ ልጅ ... ሰው ነው ...” በሚል ርዕስ የሚታወቀውን ታላቅ ግጥም እንዲሁ “ዘፈን” በማለት ለመተቸት ወይም ለማውረድ ከሆነ ደግሞ፣ ዲያቆኑን የባሰ የታሪክ፣ የኃይማኖት እና ከሁሉም በላይ የስነ-ጽሁፍ ድህነቱን ይናገርበት ይመስለኛል። ምክንያቱም ሀገር ማለት ሰው ነው! ላስረዳ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

“ሀገር ማለት ሰው ነው”፤ እስኪ ሙት በለኝ!

ዳንኤል ክብረት

ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገርሙኝ ዘፈኖች አንዱ “ሀገር ማለት ሰው ነው” የሚለው ነው። እሥራኤላዊና ጂፕሲ ይህንን ቢሰሙ ምን ይሉ ይሆን? እላለሁ። አይሁድ በመላው ዓለም ለ1900 ዓመታት ያህል ተበታትነው ሲኖሩ በየአካባቢው ሰው ነበራቸው፤ያውም እንደ ብረት የጠነከረ ማኅበረሰብ፤ ሀገር ግን አልነበራቸውም። ሀገር ማለት ሰው ከሆነ አይሁድ ሀገር ፍለጋ ከሺ ዓመታት በላይ መኳተን አልነበረባቸውም። በአውሮፓ የሚኖሩት ጂፕሲዎች የታወቀ ማኅበረሰብ አላቸው። ነገር ግን ሀገር የላቸውም። ሀገር ማለት ሰው ቢሆን ኖሮ ጂፕሲ የሚባል ሕዝብ ብቻ ሳይሆን ጂፕሲ የሚባል ሀገርም ይኖር ነበር። ግን የለም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በ“የለውጥ ሐዋርያ” የተወጠረ ሲቪል ሰርቪስ

ነፃነት ዘለቀ

Panda

የታያቸውን አላውቅም ከምን ጊዜውም በላይ ወያኔዎች ሰሞኑን ክፉኛ ተጨንቀዋል። እነሱና እኔ ከጥንት ጀምሮ የተለዬ “ዝምድና” ያለን በመሆናችን ነገረ ሥራቸውን በደንብ አውቀዋለሁ። ሲጨነቁና ሲጠበቡ እንዴት እንደሚሆኑና ምን እንደሚያደርጉ በረሃ ሳሉ ጀምሮ በሚገባ እንተዋወቃለን። ከዱሮው ለማጣቀስ ያህል አንዳች አደጋ አንጃቦባቸው ሲጨነቁ ትላልቅ ባለሥልጣኖቻቸውን በቃለ-መጠይቅ መልክ እያቀረቡ ምንም እንዳልተፈጠረ ለማስመሰል ጀሌያቸውን ያጽናናሉ፤ ያበረታታሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ወያኔ መሞቻውን፤ እኛ መሰንበቻውን

ይገረም አለሙ

"ወያኔ የራሱን መቃብር እየቆፈረ ሞቱን ሲያፋጥን፤ ተቃዋሚዎች ገንገንዘው ሳጥን ለመክተትም ሆነ ከቀብር ስፍራ አድርሰው አፈር ለመመለስ የሚችሉ አልሆኑም"

TPLF funeral. "ወያኔ የራሱን መቃብር እየቆፈረ ሞቱን ሲያፋጥን፤ ተቃዋሚዎች ገንገንዘው ሳጥን ለመክተትም ሆነ ከቀብር ስፍራ አድርሰው አፈር ለመመለስ የሚችሉ አልሆኑም"

እኔ ከምኑም የለሁበት ተቀዋሚም ደጋፊም አይደለሁም በሚል ጭንብል ተሸፍኖ የሚኖረው ክፍል ሲቀር ሌላው በሁለቱ ጎራ ይመደባል። በወያኔ ጎራ ያለው ወገን ለአባልነትም ይሁን ለደጋፊነት ያበቃው ምክንያት ምንም ይሁን ባለው አቅም በሚችለው መንገድ የወያኔን ዕድሜ ለማራዘም ያስችላል ብሎ ያመነበትን ይሠራል። እንደውም አንዳንዱ ያለ ወያኔ መኖር እንደማይቻል ራሱን አሳምኖ ሞቴን ከወያኔ ጋራ ያለ ነው የሚመስለው። በዚህ ጎራ የተሰለፉ ሰዎች ሆነ ብለው አቅደው ሊገኝ የሚችለውን ውጤት ናፍቀው የወያኔን ዕድሜ በሚያሳጥር ተግባር ላይ አይሰማሩም። የውስጥ አርበኞች ካልሆኑ በስተቀር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

“የልጄን ነገር አደራ! እባክህ ነፍሴን አሳርፋት" እናት ሎሜ ረጋስ

የማለዳ ወግ ...

* በኀዘን የሚላወስ እንስፍስፍ የእናት አንጀት

* የኮንትራት ሠራተኛዋን እህት ቤዛን አፋልጉኝ!

ነቢዩ ሲራክ

ሆዴን ያላወሰው የእማማ ሎሜ አደራ

Beza Ashenafi Engida and her mother Lome Regass. እህት ቤዛ አሸናፊ እንግዳ እና እናት ሎሜ ረጋስ

የእናትን መሪር ኀዘን ሰምቼ ሆዴ ተላውሷል፣ የእናትን ጥልቅ ጭንቀቷ፣ ያለ አባት በአሳር በመከራ ያሳደገቻት የእናትን ሎሜ መሪር ኀዘን ተረድቼ ሕመም መታመሜ እውነት ሳለ፤ በዝምታ እየቆሰልኩ ማስረጃና መረጃ ፍለጋ መዋተቴ ሕመሜን አክብዶታል። ከጉያዋ ወሽቃ፣ በትንፋሿ አሙቃ፣ ስታገኝ በደስታ፣ ስታጣ ተከፍታ፣ ድሃ አደግ ቤቷን አሟሙቃ፣ ነገ ልጆቿን ለወግ ለማዕረግ የማድረስ ምኞት ተስፋን ሰንቃ፤ ተስፋዋን የተነጠቀች እናት እንባ ውስጤን አድምቶ አቃጥሎታል። እናት ዛሬ ማለዳ በላኩልኝ መልዕክት እንዲህ ይላል “የልጄን ነገር አደራ! እባክህ ነፍሴን አሳርፋት" …

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያ ወዴት ነው የምትሄደው እና የማትሄደው?

ፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም፣ ነጻነት ለሀገሬ)

Quo Vadis Ethiopia: Where Are You (not) Going?

(እ.ኤ.አ መጋቢት 27/2016 በማሪዮት ጆርጅታዎን ከተማ (ዋሽንግተን ዲሲ) ቪዥን ኢትዮጵያ በተባለው ድርጅት አስተባባሪነት “ስለወደፊቷ ኢትዮጵያ፡ ሽግግር፣ ዴሞክራሲ እና ብሔራዊ አንድነት ጉባኤ” በሚል ርዕስ በእንግሊዝኛው ቅጅ ከቀረበው ንግግር የተወሰደ ነው።) …

“ስለወዲፊቷ ኢትዮጵያ፡ ሽግግር፣ ዴሞክራሲ እና ብሔራዊ አንድነት ጉባኤ” በሚል ርዕስ ስለተዘጋጀው ጉባኤ ቪዥን ኢትዮጵያን እና የጉባኤውን አስተባባሪዎች በሙሉ ለማመስገን እፈልጋለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ