የብርቱካንን ምስል በቲሸርት ማሠራት ያስቀጣል

ቲሸርት የለበሱ ወጣቶች ለአንድ ቀን ታሰሩ

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ታህሳስ 24 ቀን 2002 ዓ.ም. January 2, 2010)፦ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ፕሬዝደንት ወ/ት ብርቱካን ሚዳቅሳን ምስል በቲሸርትም ሆነ በሌላ መንገድ ይዞ መንቀሳቀስ እንደሚያስቀጣ ተገለጸ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

በቫንኩቨር ብርቱካን ሚደቅሳ የታሰረችበት አንደኛ አመት ተከበረ

በተክለሚካኤል አበበ

ሰፊ ውይይትም ተደረገ

በቫንኩቨር የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በታህሳስ 20 2001 ዓ.ም. በወያኔ ወታደሮች ያለአግባብ ተይዛ ቃሊቲ እስር ቤት የተወረወረችውን የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ መሪ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ የታሰረችበትን አንደኛ ዓመት አክብረው ዋሉ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ፖሊስ የአንድነትን ክስ ዘጋ

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ታህሳስ 17 ቀን 2002 ዓ.ም. December 26, 2009)፦ “የፓርቲውን እንቅስቃሴ በተደጋጋሚ አውከዋል” የተባሉት የእነፕሮፌሠር መስፍንን ቡድን ለገርጂ ፖሊስ ጣቢያ ክስ መስርቶ የነበረው አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲን ክስ ፖሊስ ማቋረጡ ተሰማ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዶ/ር ብርሃኑንና አቶ አንዳርጋቸውን ጨምሮ አምስት ሰዎች ሞት ተፈረደባቸው

Dr. Berhanu Nega & Ato Andargachew Tsege (From L to R)33ቱ ተከሳሾች የዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት፣ ሁለቱ የ10 ዓመት ጽኑ እስራት ተፈረደባቸው

የአምስቱ ንብረት እንዲወረስ ተወሰነ

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ታህሳስ 13 ቀን 2002 ዓ.ም. December 22, 2009)፦ ከግንቦት ሰባት ንቅናቄ ጋር በተያያዘ “ሕገመንግሥቱንና ሕገመንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይልና በትጥቅ አመጽ ለመጣል ሲንቀሳቀሱ ተደርሶባቸዋል” በሚል በፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ከተከሰሱትና በአምስቱም ክሶች ጥፋተኛ ከተባሉት 40 ግለሰቦች ውስጥ የግንቦት ሰባት መሥራቾችና አመራሮች ውስጥ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ፣ አቶ መስፍን አማን እና አቶ ሙሉነህ እዩኤል፤ እንዲሁም በእስር ቤት የሚገኙት አቶ መላኩ ተፈራ በዛሬው ዕለት የሞት ቅጣት ተፈረደባቸው። የሞት ቅጣቱን የወሰነው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሁለተኛ ወንጀል ችሎት ነው። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በግል ፕሬሶች ላይ ዘመቻ ጀመረ

ነፃ ፕሬሶች ምላሽ እየሰጡ ነው

Ethiopia Zare (አርብ ታህሳስ 9 ቀን 2002 ዓ.ም. December 18, 2009)፦ በኢትዮጵያ ነፃ ፕሬስ ላይ እንደሚዘምት ከሣምንት በላይ ነጋሪት ሲያስመታና ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በየዜናዎቹ መሃል ሳይቀር ማስታወቂያ ሲያስነግር የሰነበተው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን፤ ለሦስት ቀናት የቀድሞ ነፃ ጋዜጦችንና ከ97 ወዲህ የተፈጠሩትን ጨምሮ በዩኒቨርሲቲ ምሁራንና በተለጣፊ የጋዜጣ ማኅበር አመራሮች በመጠቀም አብጠለጠለ። በተለያዩ ፕሬሶች ምላሽ እየተሰጠው መሆኑ ታወቀ። ሙሉውን አስነብበኝ ...